ክፍያዎትን በቀላሉ ይክፈሉ ክቡራን ደንበኞቻችን ብሪቲሽ ካውንስል እንደተለመደው ፍላጎትዎን ለማሟላት ቀልጣፋ የክፍያ መንገድ አዘጋጅቶልዎታል።

ምን ማድረግ ይኖርብዎታል ? ቀላል ነው! በአቅራቢያዎ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያዎን ገቢ ማድረግ ብቻ ይጠበቅብዎታል። ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተዘረዘሩትን የክፍያ መመሪያዎች ያንብቡ።

ከIELTS እና ሌሎች ፈተናዎች (Exams) ጋር የተያያዙ ክፍያዎች

ወድ ደንበኛችን በአዲሱ መመሪያችን መሰረት ክፍያዎትን በቀላሉ በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታችን ገቢ ማድረግ ይችላሉ። ቀጥሎ የተገለጸውን የባንክ አካውንት ቁጥር ይጠቀሙ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር: 1000004548446

ያስታውሱ :- በET001የሚጀምረውን ልዩ የIELTS ፈተና ማመሳከሪያ ቁጥርዎን በገንዘብ ገቢ ማድረጊያ ቅጹ ላይ በትክክል መጻፍዎን ያረጋግጡ። የIELTS ማመሳከሪያ ቁጥርዎን በገቢ ደረሰኝ ላይ በትክክል አለማስቀመጥ የምዝገባዎን ሂደት ሊያዘገይብዎት ይችላል። ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ክፍያዎን ካልፈጸሙ ምዝገባዎ ሊሰረዝ ይችላል። በተጨማሪም ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ክፍያዎን ከፈጸሙ በኃላ ገንዘብዎ ተመላሽ እንዲሆንልዎ ከፈለጉ ጠይቀው የIELTS ደንብና ሁኔታዎችን በሚከተል መልኩ ተመላሽ ሊደረግልዎ ይችላል። ተመላሽ ስለሚሆኑ ክፍያዎች የበለጠ ለመረዳት ድረ ገጻችንን ይጎብኙ https://ethiopia.britishcouncil.org/am/exam/ielts/terms-and-conditions እባክዎን የገንዘብ ገቢ ደረሰኝዎን በመያዝ ምዝገባዎን በሚያጠናቅቁበት ጊዜ ለብሪቲሽ ካውንስል የደንበኞች አገልግሎት ዴስክ ያቅርቡ።

ሌላ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካለዎት እባክዎን በ +251 (0)911 512835 ወይም +251 (0)11 617 4300 ይደውሉልን።

እናመሰግናለን

የብሪቲሽ ካውንስል ኤግዛምስ ክፍል

IELTS ወይም ሌሎች ፈተና ነክ ያልሆኑ ክፍያዎች

ወድ ደንበኛችን በአዲሱ መመሪያችን መሰረት ክፍያዎትን በቀላሉ በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታችን ገቢ ማድረግ ይችላሉ። ቀጥሎ የተገለጸውን የባንክ አካውንት ቁጥር ይጠቀሙ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር: 1000004548446

ያስታውሱ: በገንዘብ ገቢ ደረሰኙ ላይ ሙሉ ስምዎን እስከ አያት ስም የአስገቢው ስም በሚለው ክፍል ስር በትክክል መጻፍ ይኖርብዎታል። ሙሉ ስምዎን በትክክል በደረሰኙ ላይ አለማስቀመጥ መጽሃፍ የሚቀበሉበትን ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን ጊዜ ሊያራዝመው ይችላል። እባክዎን ገንዘብዎን በ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ካደረጉ በኋላ መጽሓፍ ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ብሪቲሽ ካውንስል በመጡ ጊዜ የገቢ ደረሰኝዎን ለደንበኞች አገልግሎት ዴስክ ያቅርቡ።

ሌላ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካለዎት እባክዎን በ +251 (0)911 512835 ወይም +251 (0)11 617 4300 ይደውሉልን።

እናመሰግናለን

የብሪቲሽ ካውንስል የትምህርት ማዕከል

ከትምህርት ማዕከል (Teaching Centre) ጋር የተያያዙ ክፍያዎች

ወድ ደንበኛችን በአዲሱ መመሪያችን መሰረት ክፍያዎትን በቀላሉ በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታችን ገቢ ማድረግ ይችላሉ። ቀጥሎ የተገለጸውን የባንክ አካውንት ቁጥር ይጠቀሙ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር: 1000004548446

ያስታውሱ: በገንዘብ ገቢ ደረሰኙ ላይ የምዝገባ መለያ ቁጥርዎን በትክክል መጻፍ ይኖርብዎታል። የምዝገባ ቁጥርዎን ከብሪቲሽ ካውንስል የደንበኞች አገልግሎት ዴስክ ያገኛሉ። የምዝገባ መለያ ቁጥርዎን በትክክል በገቢ ደረሰኝ ላይ አለማስቀመጥ የምዝገባዎን ሂደት ሊያዘገይብዎት ይችላል። እባክዎን የገንዘብ ገቢ ደረሰኝዎን በመያዝ ምዝገባዎን በሚያጠናቅቁበት ጊዜ ለብሪቲሽ ካውንስል የደንበኞች አገልግሎት ዴስክ ያቅርቡ። ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ በ48 ሰዓት ውስጥ ክፍያዎን ካልፈጸሙ ምዝገባዎ ሊሰረዝ ይችላል:: እንዲሁም የምዝገባ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ገቢ የሚደረጉ ክፍያዎች ተመላሽ ሊሆኑ ይችላሉ:: ይህ የብሪቲሽ ካውንስል የትምህርት ማዕከልን ክፍያን የመመለስ እና የመሰረዝ ደንብና ሁኔታዎችን የሚከተል ይሆናል :: ተመላሽ ስለሚሆኑ ክፍያዎች የበለጠ ለመረዳት ድረ ገጻችንን ይጎብኙ:- https://ethiopia.britishcouncil.org/am/english/courses-adults/general

እናመሰግናለን

የብሪቲሽ ካውንስል የትምህርት ማዕከል