እንግሊዝኛ በራዲዮ ይማሩ
ሚድልቶን ሆል የሚተላለፍበትን ጣቢያ ይክፈቱ
ሚድል ቶን ሆል በራዲዮ የሚተላለፍ ተከታታይ ድራማ ሲሆን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የእንግሊዝኛ ተማሪዎች ለማኅበራዊ ግንኙነቶች የሚጠቅም እንግሊዝኛ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው።
የታሪኩ ዳራ፦ ሚድልቶን ሆል ከለንደን ወጣ ብሎ የሚገኝ አነስተኛ ሆቴል ነው። ባለቤቶቹ ቻርልስ ሚድል ቶንና ባለቤቱ ጃኔት ናቸው። እነዚህ ባልና ሚስት ዓለማዊ ነገር ብዙም የማይስባቸው ሰዎች ሲሆኑ የሆቴሉን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለሥራ አስኪያጁ ለሲትዌል ትተውለታል፤ ሲትዌል ሠራተኞቹ ላይ አምባገነን ነው።
የራዲዮ ፕሮግራሙ
አፍሮ ኤፍ ኤም ራዲዮ (FM 105.3) – ረቡዕ በ11፡45 እና ዓርብ በተመሳሳይ ሰዓት በድጋሚ ይቀርባል።
በጋዜጣ እንግሊዝኛ መማር
እንግሊዝኛ በጽሑፍ መማር
በኢትዮጵያ ያለው ብሪቲሽ ካውንስል፣ በአገሪቱ በሚታተመውና ከፍተኛ ስርጭት ባለው ሪፖርተር የአማርኛ ጋዜጣ ላይ እንግሊዝኛ በጽሑፍ መማር የሚል ጽሑፍ በየሳምንቱ እሁድ እያሳተመ ማውጣት ጀምሯል። በአሁኑ ጊዜ ጠቃሚ የሆኑ ተከታታይ ሙያዊ ዓምዶችን እያወጣን ሲሆን ጽሑፉ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታውቂያ ገፆች ጎን ይገኛል። ተከታታይ ዓምዶቹ የሚያተኩሩት በሥራ ቦታቸው እንግሊዝኛ ለሚናገሩ ባለሙያዎች ነው።
የራዲዮ ጣቢያ ባለቤቶችና ጽሑፍ አታሚዎች
በተከታታይ ከሚቀርቡት የራዲዮ ፕሮግራሞቻችንን አንዱን ማሰራጨት ወይም እንግሊዝኛ በጽሑፍ መማር ከተባለው ተከታታይ ዓምድ መካከል አንዱን በሚያሳትሙት ጋዜጣ ወይም ጽሑፍ ላይ ማውጣት ከፈለጉ እባክዎ መጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን።