በብሪቲሽ ካውንስል እንግሊዝኛ ለመማር የአገልግሎት ሽያጭ ሁኔታዎች

እነዚህ ሁኔታዎች ብሪቲሽ ካውንስል የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች (የእንግሊዝኛ ችሎታ ደረጃ መወሰን፣ የእንግሊኛ ቋንቋን በሚመለከት የሚሰጡ የማማከር ስራዎችን እና ቋንቋውን በመማሪያ ክፍል ውስጥ በቀጥታ፣ በድረ-ገፅ ወይም በሁለቱም ዘዴዎች ለመማር) ለሚጠቀሙ ሁሉ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡

ክፍል 1፡ አጠቃላይ ደንብና ሁኔታዎች

1.1 እነዚህ የሽያጭ ደንብና ሁኔታዎች በእርስዎና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለመማር (ፊት-ለፊትም ይሁን በድረ-ገፅ ወይም በሁለቱም ዘዴዎች በሚሰጥ) ወይም የእንግሊዘኛ ችሎታ ደረጃን ለመወሰን በሚደረግ ምዘና ወይም ቋንቋውን በሚመለከት በሚሰጥ ማንኛውም አይነት የማማከር ስራ በሚፈረሙ ውሎች ላይ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህ የደረጃ ምዘናዎች፣ የማማከር ስራዎች እና/ወይም የማስተማር ስራዎች (ፊት-ለፊትም ይሁን በድረ-ገፅ ወይም በሁለቱም ዘዴዎች) - ከነዚህ ጋር አብረው የሚሄዱ በእጅ የሚሰጡ ወይም በድረ-ገፅ የሚላኩ መርጃ ግብዓቶችን ጨምሮ - ሁሉም አንድ ላይ “የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርቶች” ተብለው ይጠራሉ። እነዚህ ምርቶች በድረ-ገፅ ወይም በሁለቱም ዘዴዎች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ እርስዎ የሚፈልጉት አገልግሎት እንዴት እንደሚቀርብ ተጨማሪ መረጃ (ኮምፒውተርዎ ወይም ሞባይልዎ ስለሚያስፈልገው ልዩ ቴክኒካዊ ዝግጅት ጭምር) ከድረ-ገጻችን መግቢያ (ፖርታል) ወይም ከሌሎች ተዛማጅ የሽያጭ ማስታወቂያዎቻችን ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

1.2 ማንኛውንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርት ከመግዛትዎ ወይም ለመግዛት ከማመልከትዎ በፊት እባክዎ ስለ ሽያጭ ሁኔታዎች ከብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ (ፖርታል) ላይ ያንብቡ ወይም በአካል ቀርበው ይጠይቁ።

1.3 እነዚህ አጠቃላይ ደንብና ሁኔታዎች ብሪቲሽ ካውንስል በሚሰራባቸው በተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ ባሉ ልዩ ሁኔታዎች እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግባቸው ይችላል፡፡ ይህም ከታች በክፍል 3 (ልዩ ደንብና ሁኔታዎች) በሚለው ስር ተዘርዝሯል፤ እንዲሁም አንድ የተለዬ ምርት፣ የአገልግሎት ወይም በድረ-ገፅ የሚላክ መርጃ ግብአት ካለ በክፍል 2 (በድረ-ገፅ ስለሚሰጡ አልግሎቶች አጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎች) በሚለውና በክፍል 4 (ተጨማሪ ደንብና ሁኔታዎች) በሚለው ስር ተዘርዝሯል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት (አጠቃላይ ደንብና ሁኔታዎች፣ በድረ-ገጽ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች አጠቃቀም ደንብ፣ ልዩ ደንብና ሁኔታዎች፣ እና ተጨማሪ ደንብና ሁኔታዎች) አንድ ላይ የሽያጭ ሁኔታዎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ በአራቱ መካከል ልዩነት/አለመጣጠም ቢኖር በቅደም ተከተል የሚከተለው ተፈፃሚ ይሆናል፤ (i) ተጨማሪ ደንብና ሁኔታዎች፣ (ii) ልዩ ደንብና ሁኔታዎች፣ (iii) በድረ-ገፅ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች አጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎች፤ እና (iv) አጠቃላይ ደንብና ሁኔታዎች።

1.4 በድረ-ገጻችን በኩል ወይም በሌላ መንገድ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት ከመግዛትዎ ወይም ለመግዛት ከማመልከትዎ በፊት የሽያጭ ሁኔታዎችን መቀበልዎን (በድረ-ገጻችን በኩል ወይም በአካል ቀርበው) እንዲያረጋግጡ የሚጠየቁ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ በድረ-ገጻችን በኩል ማመልከቻ የሚያስገቡ ከሆነ “እቀበላለሁ” ወይም “ተቀበልና ክፈል” የሚለውን ሳጥን (እንደሁኔታው) ሲጫኑ፤ በአካል ቀርበው የሚያመለክቱ ከሆነ ደግሞ የሽያጭ ሁኔታዎች ቅጂ እትም ላይ ሲፈርሙ በሽያጩ ሁኔታዎች ላይ መስማማትዎን ገለፁ ማለት ነው፡፡ የሽያጭ ሁኔታዎችን መቀበል ካልፈለጉ በብሪቲሽ ካውንስል የሚሰጠውን አገልግሎት በአካል ቀርበው ወይም በድረ-ገጻችን ሊከታተሉ አይችሉም፡፡

2. ስለ ብሪቲሽ ካውንስልና ስለ ኮንትራትዎ

2.1. በልዩ ደንብና ሁኔታዎች ስር በተለዬ ሁኔታ እስካልተደነገገ ድረስ ይህ ኮንትራት ህጋዊ መሰረት አለው፡፡ ይህም በእንግሊዝና በዌልስ በሮያል ቻርተሩ የተካተተ ሲሆን በነዚሁ አገሮች በቁጥር 2ዐ913 በ ስኮትላንድ ደግሞ በቁጥር SC03773 በበጎ አድራጎት ድርጅትነት ተመዝግቧል፤ የተመዘገበበት ቢሮ አድራሻም 1ዐ Spring Gardens ፣ London SW1A 2BN ነው፡፡ ብሪቲሽ ካውንስል በተለያዩ አገሮች ቅርንጫፎች በመክፈትና ተመሳሳይ ስራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጭምር ይሰራል፡፡ ልዩ ደንብና ሁኔታዎች እና/ወይም ተጨማሪ ደንብና ሁኔታዎች ይህንን ጉዳይ በሚመለከትና ከእርስዎ ሁኔታ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ)፡፡ እነዚህ የሽያጭ ሁኔታዎች ወደ ሌላ ቋንቋ ሊተረጎሙ ይችላሉ። በዚህ ሁኔታ የሚዘጋጁ ትርጉሞች የሚያገለግሉት መምሪያ እንዲሆኑ ብቻ ነው (ልዩ ሁኔታዎች ከዚህ በተለዬ ካልተደነገጉ በስተቀር)፡፡ በእንግሊዘኛውና በትርጉሙ መካከል ግጪት/ልዩነት የተፈጠረ እንደሆነ በእንግሊዝኛ የሚሰጠው ትርጉም ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

2.2 በነዚህ የሽያጭ ሁኔታዎች የሚገቡት ውል በግል እርስዎን ይመለከታል፤ ስለዚህ የውሉን መብቶችና ግዴታዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ ብሪቲሽ ካውንስል በፅሁፍ ስምምነቱን ሳይገልፅ ለሌላ አካል ማስተላለፍ አይችሉም፡፡

2.3. ብሪቲሽ ካውንስል በመሰለው መንገድ ኮንትራቱን በከፊልም ሆነ በሞላ ሌላ አካል የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርቱን እንዲሰራው ማድረግ ወይም ከሌላ አካል ጋር ኮንትራት ለመፈራረም ወይም ለመወከል ይችላል፡፡ እነዚህ አካላት የሚከተሉት ናቸው፡ (i) ማንኛውም የራሱ ህጋዊ ሰውነት ያለው ሆኖ በብራቲሽ ካውንስል ቁጥጥር ስር ያለ አካል ወይም የብሪቲሽ ካውንስል አካል የሆነ፣ (ii) ማንኛውም የብሪቲሽ ካውንስል ስራዎችን ከውጪ ሆኖ እየተቀበለ የሚሰራ ሶስተኛ ወገን፡፡

2.4. በነዚህ የሽያጭ ሁኔታዎች ውስጥ “እርስዎ” ማለት አንድን በብሪቲሽ ካውንስል የቀረበ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት ለመጠቀም (በክፍል ውስጥም ሆነ በድረ-ገፅ ለመከታተል) ያመለከተ ማለት ነው፣

3. አንድን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርት ለመግዛት ስለሚደረግ ምዝገባ ወይም ክፍያ

3.1. እርስዎ የምዝገባ ጥያቄ ማቅረብዎ የሚረጋገጠው፡ i. አንድን የእንግሊዚኛ ቋንቋ ምርት በአካል ቀርበው በአንድ የተወሰነ ቦታ ወይም ግዛት ውስጥ፣ በተወሰነ ቀን እና/ወይም ጊዜ (እንደሁኔታው) እና/ወይም በድረ-ገፅ ለመከታተል ሲያመለክቱ፣ ii. በነዚህ የሽያጭ ሁኔታዎች ሲስማሙ፣ እና iii. ብሪቲሽ ካውንስል ወይም ድርጂቱ የወከለው ሶስተኛ ወገን አቅራቢ (ከሁለቱ የቀደመው) በባንክ ቁጥሩ ክፍያው መግባቱን ሲያረጋግጥ፣ ወይም ብሪቲሽ ካውንስል እንዲህ አይነት ክፍያዎችን በጥሬ ገንዘብ ወይም ከሌላ ባንክ ሂሳብ ላይ ተቀናሽ ሆኖ ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቱ ክፍያ ሲተላለፍ ነው፡፡

3.2 የምዝገባ ማመልከቻ ሲያስገቡ፡ i የሽያጭ ሁኔታዎችን ተቀብለው አንድን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት በአካል ወይም በድረ-ገፅ ለመከታተል ጥያቄ አቅርበዋል ማለት ነው፤ እንዲሁም ii. ቢያንስ 18 ዓመት የሞላዎ መሆኑን አረጋግጠዋል ማለት ነው፡፡

3.3. የምዝገባ ማመልከቻ ማቅረብ የሚችሉት ቢያንስ 18 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ አመልካቾች ወላጆቻቸው ወይም አሳዳጊዎቻቸው ስለነሱ እንዲያመለክቱላቸው መጠየቅና በሽያጭ ሁኔታዎች እንደሚስማሙ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

3.4. የምዝገባ ማመልከቻዎን ሲያስገቡ፡ -i. በድረ-ገፃችን (ፖርታል) ከሆነ በንዑስ አንቀፅ 3.1 (i) እና 3.1 (ii) ስር ስለእርስዎ የምዝገባ ማመልከቻ በተሰጠው መረጃ መሰረት ብሪቲሽ ካውንስል ክፍያ መፈፀሙን አረጋግጦ ማመልከቻው የደረሰው ስለመሆኑና ስለእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርቱ በዝርዝር ያሳውቃል - (“እውቅና”)። ክፍያው በንዑስ አንቀጽ 3.1 (iii) መሰረት በቅድሚያ ተፈፅሞ ከሆነ ደረሰኙ በስልክዎ/በኮምፒውተርዎ ላይ ወዲያውኑ በሚታይ መልዕክት (pop-up) ወይም በኢሜል ወይም በመሰል ሊታተም በሚችል ኤሌክትሮኒክ ማስታወቂያ መንገድ ይላካል - “የምዝገባ ማረጋገጫ”። የዚህ አይነቱ የምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድ የሽያጭ ሁኔታዎችን ያካተተ ቅጂ ይጨምራል፡፡ ii. በአካል ከሆነ በንዑስ አንቀፅ 3.1 (iii) መሰረት ክፍያ መፈፀሙን ካረጋገጠ በኋላ የብሪቲሽ ካውንስል ተወካይ የሚወስዱትን የእንግሊዘኛ ምርት በዝርዝር ይገልፃል - “እውቅና”። የምዝገባው ማረጋገጫ የሚሰጥዎ በንዑስ አንቀጽ 3.1 (iii) መሰረት ክፍያ ሲፈፀም ነው፡፡ የሽያጭ ሁኔታዎች ቅጂ የእውቅናው ወይም የምዝግባ ማረጋገጫው አካል ሆኖ በእጅዎ ይሰጥዎታል፡፡

3.5 ጥርጣሬን ለማስወገድ ሲባል፣ ምዝገባውን ያደረጉት በድረ-ገፅ አማካኝነት ከሆነ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቱ ውል ህጋዊ መሆኑ የሚረጋገጠው የምዝገባ ማረጋገጫው በኮምፒውተር/ሞባይል ላይ ወዲያውኑ የሚታይ መልዕክት፣ ኢሜል፣ ወይም ሌላ አይነት ኤሌክትሮኒክ ማስታወቂያ ሲደርስዎ ነው፡፡

3.6 የምዝገባ ማረጋገጫው የተመዘገቡበት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርት በብርቲሽ ካውንስል ተቀባይነት ማግኘቱን ያረጋግጣል፡፡ ይህም እርስዎ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር የገቡትን ውል በሽያጭ ሁኔታዎች መሰረት እውን ያደርገዋል - “ውል”።

3.7 በሽያጭ ሁኔታዎች መሰረት ቀደም ብሎ ተሰርዞ ካልሆነ በስተቀር ኮንትራቱ የሚቋረጠው የእንግሊዘኛው ምርት ሙሉ በሙሉ ተሰጥቶ ሲያልቅ ነው፤ ይህም ሲሆን በሽያጭ ሁኔታዎች ላይ የተዘረዘሩት ግዴታዎች ያበቃሉ (በአንቀጽ 11 ከተጠቀሱት የትምህርት መርጃ ግብዓቶች አጠቃቀም እገዳዎች በስተቀር፡፡ እነዚህ ምን ጊዜም አይቋረጡም)።

3.8 የምዝገባ ማመልከቻዎን ካስገቡ ከ72 ሰዓታት በኋላ የምዝገባ ማረጋገጫዎን ካላገኙ ለብሪቲሽ ካውንስል በ information@et.britishcouncil.org አድራሻ ኢሜል በመላክ ያሳውቁ፡፡ የምዝገባ ማረጋገጫ ሳይደርስዎ ለአመለከቱበት የትምህርት አይነት ቦታ ሊያዝልዎ አይችልም፡፡ ስለትምህርቱ ዝርዝር ጉዳይ በሙሉ ወይም በከፊል በድረ-ገፅ የሚላክልዎት ከምዝገባ ማረጋገጫው ጋር ወይም ደግሞ ለብቻው በኢሜል ወይም በሌላ የኤሌክትሮኒክ ማስታወቂያ መንገድ ነው፡፡

4. እንዴት እንደሚከፍሉ

4.1 ሁሉም በድረ-ገፅ (ፖርታል) የሚሰጡ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርቶች ዋጋ በዚያው በፖርታሉ ላይ ይገለፃል (ወይም በአካል ለመጡ ይነገራል - እንደሁኔታው)፡፡ ሁሉም የተጠቀሱ ዋጋዎች ተቀናሽ የሚሆኑ የግብር ክፍያዎችንና የዴቢት/ክሬዲት ካርድ ለሚጠቀሙ ደግሞ ለዚሁ አገልግሎት ብሪቲሽ ካውንስል መክፈል ያለበትን ዋጋ ይጨምራል (የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር)፡፡ በሌላ አካል በኩል የሚከፍሉ ከሆነም ያ አካል ለዴቢት/ክሬዲት አገልግሎት አስከፍሎዎ ከሆነ ይህ ብሪቲሽ ካውንስል ከሚጠይቀው ውጪ ነው፡፡ የክፍያው መጠኖች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለያዩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህ ቀደም ብሎ በምዝገባ ማረጋገጫ የተረጋገጠን የምዝገባ ማመልከቻ አይመለከትም፡፡

4.2 በክሬዲት/ዴቢት ካርድ እንዴት እንደሚከፍሉ 4.2.1 በምዝገባ ማመልከቻ ሂደቱ ላይ እንደተገለፀው ክፍያዎን በክሬዲት/ዴቢት ካርድ መፈፀም ይችላሉ፡፡ ብሪቲሽ ካውንስል በሁሉም መንገድ የሚፈፀሙ ክፍያዎችን በተመለከተ ከፋዩ በክሬዲት/በዴቢት ካርድ የመክፈል ህጋዊ ስልጣን ያለውና ከ18 ዓመት በላይ እንደሆነ አድርጎ ይቆጥራል፡፡ 4.2.2 በክሬዲት/ዴቢት ካርድ የሚፈፀሙ ክፍያዎች በሶስተኛ ወገን አሳላጭነትና በአስተማማኝ የድረ-ገፅ ግንኙነት መስመር ወዲያውኑ ያልቃሉ፡፡ የካርዱ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ በብሪቲሽ ካውንስል አይያዝም፡፡ ክፍያው በድረ-ገፅ በሚደረግበት ጊዜ የክሬዲት/ዴቢት ካርድ ክፍያው መፈፀሙን የሚያሳይ በኢሜል ወይም በፖርታል አድራሻዎ ወዲያውኑ በሚታይ መልዕክት ወይም በሌላ ኤሌክትሮኒክ ማስታወቂያ (እንደሁኔታዉ) ደረሰኝ ይደርስዎታል፤ ይህም ጥርጣሬን ለማስወገድ እንደ ምዝገባ ማረጋገጫ ይቆጠራል፡፡

4.3 ከባንክ ወደ ባንክ በማስተላለፍ የሚፈፀም ክፍያ 4.3.1 ለአንዳንድ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርቶች ብሪቲሽ ካውንስል በቀጥታ ከባንክ የሚደረግን ክፍያ ሊቀበል ይችላል፡፡ ብሪቲሽ ካውንስል ይህንን የክፍያ መንገድ ሲፈቅድ በፖርታሉ ላይ ይገልፃል፤ ወይም ለእርስዎ በቀጥታ ይነገርዎታል፤ ወይም እንዳስፈላጊነቱ በልዩ ደንብና ሁኔታዎች እና/ወይም በተጨማሪ ደንብና ሁኔታዎች ውስጥ ይካተታል፡፡ 4.3.2 በቀጥታ በባንክዎ በኩል ክፍያ ሲፈፅሙ ብሪቲሽ ካውንስል እርስዎ ክፍያውን ለመፈፀም ህጋዊ ስልጣን ያለዎት እንደሆኑ አድርጎ ይቆጥራል፡፡ 4.3.3 ክፍያው በባንክ በኩል ሲፈፀም በተቻለ መጠን በ72 ሰዓታት ውስጥ የክፍያ ሂደቱ ይጠናቀቃል፡፡ 4.3.4 በባንክዎ በኩል አስፈላጊውን ክፍያ ሲፈፅሙ ባንክዎ የአገልግሎት ዋጋ ተጨማሪ ሊያስከፍልዎ እንደሚችል እንዲገነዘቡ በትህትና እንገልፃለን፡፡ በባንክዎ በኩል ሂሳቡ ወደ ብሪቲሽ ካውንስል ባንክ ቁጥር ገቢ ሲሆን የምዝገባ ማረጋገጫ ሆኖ ይቆጠራል።

4.4 በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ ስለሚፈፀም ክፍያ 4.4.1 በአካል ቀርበው የምዝገባ ማመልከቻ ሲያቀርቡ ብሪቲሽ ካውንስል የተመደበውን የክፍያ መጠን በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ ሊቀበል ይችላል፡፡ በዚህ መንገድ የተከፈለበት ደረሰኝ (በንዑስ አንቀጽ 3.1 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ) አንደ ምዝገባ ማረጋገጫ ያገለግላል፡፡

4.5 ብሪቲሽ ካውንስል ላቀረበው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርት ክፍያ ሳይፈፅሙ በአካል ቀርበው ወይም በድረ-ገፃችን ትምህርቱን ሊከታተሉ አይችሉም፡፡ ብሪቲሽ ካውንስል ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ሳይከፍሉ ትምህርቱን በሙሉም ይሁን በከፊል እንዳይከታተሉ (በአካልም ይሁን በድረ-ገፅ) ሊያደርግ ይችላል - እርስዎን ባለዕዳ ሳያደርግ፡፡

5. በብሪቲሽ ካውንስል ስለሚደረግ ስረዛ

5.1 ብሪቲሽ ካውንስል በማንኛውም ምክንያትና ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት ባለ በየትኛውም ጊዜ የፅሑፍ መልዕክት በኢሜል ወይም በሌላ መንገድ ሰጥቶ ትምህርቱን መሰረዝ ይችላል፡፡ (ይህ በድረ-ገፅ ብቻ ወይም በፊት-ለፊትና በድረ-ገፅ ድብልቅ ዘዴዎች ሊሰጡ ታስበው የነበሩ ትምህርቶች ለተጠቃሚው ክፍት ከመደረጋቸው በፊት ያለውንም ጊዜ ይጨምራል፡፡) ብሪቲሽ ካውንስል ትምህርቱን የሚሰርዘው በዚሁ ንዑስ አንቀፅ (5.1) መሰረት ከሆነ ታቅዶ ለነበረው ትምህርት የፈፀሙት ክፍያ ይመለስልዎታል፡፡

5.2 ከዚህ በተጨማሪ ብሪቲሽ ካውንስል እርስዎን ባለዕዳ ሳያደርግ በሚከተሉት ምክንያቶች ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፦ i. በዚህ ውል አንቀፅ 4 በተደነገገው መሰረት ለተመዘገቡት የትምህርት አይነት መክፈል ያለብዎትን ካልከፈሉ፤ ወይም ii.የሽያጭ ሁኔታዎችን ከጣሱ፤ ወይም iii. ከቁጥጥሩ ውጪ በሆነ ምክንያት ብሪቲሽ ካውንስል ሊሰጥ ያሰበውን አገልግሎት መስጠት ሲያቅተው

5.3 ብሪቲሽ ካውንስል በንዑስ አንቀጽ 5.2 (i) ወይም 5.2 (ii) መሰረት ውሉን የሰረዘ እንደሆነ የተቀበለውን ገንዘብ የራሱ የማድረግ፣ ያልተከፈለም ከነበረም ሙሉ ክፍያውን የማግኘት መብት አለው፡፡

5.4 ብሪቲሽ ካውንስል ውሉን የሰረዘው በንዑስ አንቀጽ 5.2 (iii) መሰረት ከሆነ ከሚከተሉት ሁለት አማራጮች አንዱን የመምረጥ መብት አለዎት፡- (i) የከፈሉትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እንዲመለስልዎ የማድረግ፣ (ii) (አገልግሎቱ ካለ) ተመጣጣኝ የሆነ ሌላ ትምህርት/ አገልግሎት የማግኘት፡፡ ሁለተኛውን አማራጭ ከመረጡና የዚህ አገልግሎት ዋጋ ከተሰረዘው አገልግሎት የበለጠ ከሆነ በአንቀፅ 4 መሰረት ልዩነቱን መክፈል ይኖርብዎታል፡፡ ሁለተኛውን አማራጭ ወስደው ዋጋው ከተዘረዘረው አገልገሎት ያነሰ እንደሆነ ብሪቲሽ ካውንስል ልዩነቱን ለእርስዎ ይመልሳል፡፡ አገልግሎቱ መሰረዙን ሲያውቁ በ14 ቀናት ውስጥ ምርጫዎን ለብሪቲሽ ካውንስል በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርብዎታል (የሚልኩት ኢሜል የድረ-ገፁን URL እና SOLAS ገፁን መጥቀስ አለበት)፡፡

 

6. በእርስዎ ስለሚደረግ ስረዛ

6.1 በመጀመሪያዎቹ 14 ቀናት ጊዜ ውስጥ ስለሚደረግ ስረዛ 6.1.1 የምዝገባ ማረጋገጫውን ካገኙበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ምንም ምክንያት መስጠት ሳያስፈልግዎ ውሉን መሰረዝ ይችላሉ፡፡ 6.1.2 የምዝገባ ማረጋገጫውን ካገኙ 14 ቀናት በኋላ የውል መሰረዣ ጊዜው ያበቃል፡፡ 6.1.3 የመሰረዝ መብትዎን ለመጠቀም ለመሰረዝ መወሰንዎን የሚገልፅ መልዕክት (በፖስታ ቤት በሚላክ ደብዳቤ ወይም በኢሜል) ለብሪቲሽ ካውንስል በንዑስ አንቀጽ 5.4 በተሰጠው የኢሜል አድራሻ መላክ አለብዎት፡፡ ከፈለጉ በዚህ ውል መጨረሻ ላይ አባሪ ሆኖ የተያያዘውን የውል መሰረዣ ቅፅ (Annex A) ሊጠቀሙበት ይችላሉ፤ ግዴታ ግን አይደለም፡፡ 6.1.4 የተሰጠውን የመሰረዣ ጊዜ ለመጠቀም ለመሰረዝ መወሰንዎን የሚገልፅ መልዕክት የመሰረዣ ጊዜው ሳያልቅ መላክ በቂ ነው፡፡

ከሰረዛ በሁዋላ ምን የይሆናል

6.1.5 ውሉን በንዑስ አንቀጽ 6.1.1 መሰረት በ14 ቀናት ውስጥ ከሰረዙ ብሪቲሽ ካውንስል አገልግሎት ለማግኘት የከፈሉትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ይመልስልዎታል። 6.1.6 ብሪቲሽ ካውንስል ገንዘብዎን ባልተራዘመ ጊዜ ውስጥ ይመልሳል፤ ይህም ውሉን የመሰረዝ ውሳኔዎ ከታወቀ በኋላ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡ 6.1.7 ብሪቲሽ ካወንስል በድረ-ገፅ የተፈፀሙ ክፍያዎችን ለመመለስ ክፍያው የተፈፀመትን የክፍያ ካርድ ይጠቀማል፡፡ በሌሎች ዘዴዎች የተፈፀሙ ክፍያዎች ሁሉ ተመላሽ የሚሆኑት በባንኮች አማካኝነት ነው፡፡ 6.1.8. (I) በድረ-ገፅ ብቻ የሚሰጡትንና በድረ-ገፅም በፊት-ለፊትም በጥምር የሚሰጡትን አገልግሎቶች ሳይጨምር፣ የምዝገባ ማመልከቻዎ ላይ የተገለፀው አገልግሎቱን መጀመር የሚፈልጉበት ቀን በስረዛ ጊዜው ውስጥ ከሆነና ይህንን አውቀው ከጀመሩ በኋላ ውሉን መሰረዝ ቢፈልጉ፣ የመሰረዝ ውሳኔዎን ለብሪቲሽ ካውንስል እስካሳወቁበት ጊዜ ድረስ ላገኙት አገልግሎት ተገቢውን ክፍያ ይፈፅማሉ፡፡ (II) በድረ-ገፅ ብቻ የሚሰጡትና በድረ-ገፅም በፊት-ለፊትም በጥምር ወይም በሌሎች ኤሌክትሮኒክ ዘዴዎች ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከተሉት ተፈፃሚ ይሆናሉ፦ i. ብሪቲሽ ካውንስል በድረ-ገፅ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የ14 ቀናቱ የስረዛ ጊዜ ሳይጠናቀቅ መስጠት እንደማይጀምር ለማሳወቅ እንደወዳለን፤ (ይህ የሚሆነው በእርስዎ ስምምነት ብቻ ሲሆን፣ በዚህ ሁኔታ ከተስማሙም ውሉን የመዘረዝ መብትዎን ያጣሉ)፤ ኮሚፒዩተር ቁልፍ ተጭነው አገልግሎቱን ማግኘት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ውሉን የመሰረዝ መብትዎን ያጣሉ። ii. በስረዛ ጊዜው ውስጥ አገልግሎቱን መጀመር የሚፈልጉ ከሆነ የድረ-ገፅ አገልግሎት አጠቃቀምን በተመለከተ በደንብና ሁኔታዎች ግርጌ ካሉት የምርጫ ሳጥኖች ውስጥ አንዱ ላይ ምልክት በማድረግና ይህንን ፍላጎትዎን በማሳየት በማሳየት፦ (a) የድረ-ገፅ አገልግሎቱ በፈለጉበት ጊዜ እንዲጀመርልዎ፣ እና (b) ውሉን የመሰረዝ መብትዎት እንደሚያጡ መገንዘብዎን በምርጫዎ ማሳየት ይችላሉ፤ እና iii. ከላይ በተጠቀሰው የምርጫ ሳጥን ላይ ምልክት ካደረጉ የድረ-ገፅ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስችለውን የ 6.1.9 አንድን የእንግሊዘኛ ቋንቋ አገልግሎት በሙሉ ወይም በከፊል መከታተል ወይም ማግኘት ከጀመሩ በኋላ የመሰረዝ መብት የለዎትም፡፡ ጥርጣሬን ለማስወገድ በድረ-ገጽ ወይም በድረ-ገፅና በፊት-ለፊት በጥምር የሚሰጡ የእንግሊዘኛ ቋንቋ አገልግሎቶችን በሚመለከት የመጀመያውን ሞዲውል (በአካል ቀርበውም ሆነ በድረ-ገፁ) ካገኙ በኋላ ምርቱን በአጠቃላይ እንዳገኙ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

6.2. ከ14ቱ ቀናት የስረዛ ጊዜ በኋላ ስለሚደረግ ስረዛ 6.2.1 ከላይ በንሁስ አንቀጽ 6.1 የተጠቀሰው የስረዛ ጊዜ ካለቀ በኋላ ውሉን የመሰረዝ ህጋዊ መብት የለዎትም፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ ውል ለመሰረዝ በአካባቢዎ ከሚገኝ የብሪቲሽ ካወንስል ማዕከል ፈቃድ ሊያገኙ ይገባል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውል የሚሰርዙ ከሆነ በአካባቢዎ ወደሚገኝ የብሪቲሽ ካውንስል ማዕከል ቀርበው መሰረዝ የፈለጉበትን ምክንያት ካሰረዱ በኋላ ፈቃድ ማግኘት አለማግኘትዎን ያረጋግጡ፡፡

7. የትምህርት አሰጣጥ

7.1 ብሪቲሽ ካውንስል እያንዳንዱ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምርት በድረ-ገፁ (ፖርታል) ወይም በሌላ ማዕከል ላይ በተገለፀው መሰረት ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ሆኖም ብሪቲሽ ካውንስል አገልግሎቱን ያሻሽላል ብሎ ሲያምን በአሰጣጡና በይዘቱ ላይ መሰረቱን ሳይለቅ ለውጦች የማድረግ መብት ይኖረዋል፡፡

7.2 ወደሌላ የትምህርት አይነት ስለመሸጋገር i. በፊት-ለፊት የሚሰጥ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትን የሚመለከት ሲሆን ብቻ በምዝገባ ማመለከቻዎ ላይ የጠቀሱት የትምህርት ደረጃ እርስዎ ካለዎት ደረጃ ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ ትምህርቱን ከጀመሩ በኋላ አቋርጠው ወደ ሌላ ደረጃ ለመሸጋገር ቢፈልጉ ይህንኑ ለብራቱሸ ካውንስል ያስረዱ። ብሪቲሽ ካውንስል ያለዎት ደረጃ ከተመዘገቡበት ደረጃ ጋር የማይጣጣም መሆኑን ሲያረጋግጥና የሚሸጋገሩበት ደረጃ ላይ ቦታ ካለ ያለተጨማሪ ክፍያ ሽግግሩን ለማድረግ የተቻለውን ጥረት ያደርጋል፡፡ ii. የትምህርቱ አይነት በድረ-ገፅ የሚሰጥ ከሆነ የሚስማማዎት ደረጃ ወደሚሰጥባቸው ቀናት መሸጋገር ይችላሉ።

8. ብዝሃነትና አካታችነት

8.1. ብሪቲሽ ካውንስል ለሁሉም ሰዎች እኩል ዕድል እና ተጠቃሚነት ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል ።

8.2. የተለየ የአካል ጉዳት ወይም ልዩ ፍላጎት ካለዎት ብሪቲሽ ካውንስል ሌሎች ምንም አይነት ልዩ ፍላጎት ካላቸው ተማሪዎች እኩል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶችን በተመሳሳይ ደረጃ እንዲያገኙ አስፈላጊውን ማስተካከያ ያደርጋል ።

8.3. ለብሪቲሽ ካውንስል ስለ አካል ጉዳትዎ ወይም ስለሚፈልጉት ማስተካከያ በግልጽ በቅድሚያ ያሳውቁ። ይህም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርቱ ከመጀመሩ ቢያንስ ከስምንት ሳምንት በፊት መሆን አለበት።

9. የልጆች ጥበቃ ደንብ

9.1. ብሪቲሽ ካውንስል በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ሁሉም ህጻናት አቅም እንዳላቸውና ለዓለም አስፈላጊ እንደሆኑ ያምናል። በተባበሩት መንግስታት ድንጋጌ (UNCRC 1989) አንቀጽ 19 ላይ እንደተገለጸው ሁሉም ህጻናት ከማንኛውም አይነት ጥቃት መጠበቅ እንዳለባቸው ብሪቲሽ ካውንስል በጥብቅ ያምናል።

10. የእርስዎ ግዴታዎች

10.1. እርስዎ: ሀ) በማንኛውም ሰዓት ታማኝ፣ ግልጽና ትሁት፣ አክባሪና መልካም አቀባበል ያለው በመሆንና ይህንንም ለሌሎች በማሳየት የእንግሊዝኛ ትምህርትዎን መከታተል አለብዎት ለ) ብሪቲሽ ካውንስል በሚጠይቀው መሰረት ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት ስልጠናው መዘጋጀት አለብዎት ሐ) ሁሉንም የስልጠና መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ተግባራት እንዲሁም አስፈላጊ የቡድን ስራዎችን መከታተል ይኖርብዎታል ይህ በስምምነት ወይም በህክምና ምክንያት የሚፈጠሩ ከትምህርት ገበታ መቅረቶችን የማያካትት ነው መ) በብሪቲሽ ካውንስል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት ውስት በመሳተፍ የሚያገኙዋቸውን መረጃዎች በሚስጥር የመያዝ ግዴታ አለብዎት።

10.2 ብሪቲሽ ካውንስል በስልጠና ወቅት የሚያሳዩት ባህሪ ከደንቦች ውጪ የሆነ፣ አደጋ የሚያስከትል ወይም የሚረብሽ፣ ጥቃት ወይም ጉዳት የሚያደርስ ወይንም በድረ፡ገፅ ስለሚሰጡ አልግሎቶች አጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎችን የሚጥስ መሆኑን ካመነበት ለምርቱ ምዝገባ የመከልከል ወይም አገልግሎቱን የማቋረጥ ሙሉ መብት አለው። ብሪቲሽ ካውንስል በተለያዩ አጋጣሚዎች የተሳታፊዎችንና የስልጠና ቦታውን ደህንነት ለማረጋገጥ የደህንነት ጥንቃቄ ምርመራዎችን ሊያደርግ ይችላል ስለዚህም ለዚህ ትብብር ለማድረግ መስማማት አለብዎት። ፍቃድ ያልተሰጠው በፎቶግራፍ ወይም በሌላ መሳሪያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶቹን መቅዳት ወይም በማንኛውም መልክ በኢንተርኔት ላይ በቅጂ መልክ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

11. የአዕምሯዊ መብት ባለቤትነት

11.1 ብሪቲሽ ካውንስል እና ፈቃድ የሰጡ ድርጅቶች በሁሉም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶች ላይ ባለሙሉ የባለቤትነትና ሌሎች የአዕምሯዊ መብቶች አሏቸው። የብሪቲሽ ካውንስል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶችን በመቅዳት ወይም በቅጂ መልክ እንዲቀመጡ እንዲሁም በማንኛውም መልክ በኢንተርኔት ወይም በተወሰነ የኢነተርኔት ክፍል እንዲሰራጩ ላለማድረግ ተስማምተዋል። በተጨማሪም ምርቶቹን ለመሸጥ ወይም ለማከራት ለሶስተኛ ወገን ፈቃድ ላለመስጠት ይገደዳሉ።

11.2. ብሪቲሽ ካውንስል የብቻዎ ያልሆነ ከፈቃድ ክፍያ ነጻ ለስልጠናዎ አገልግሎት ወይም በተመዘገቡብት የትምህርት መርሃ ግብር ላይ ጥናት ለማድረግ የእንግሊዝኛ ምርቶቹን ለሽያጭ ባልሆነ ሁኔታ የመጠቀም ፈቃድ ይሰጥዎታል።

12. ማሳሰቢያ

12.1 በሽያጭ ሁኔታዎች ላይ የተገለጹ ማንኛውም ደንብ በብሪቲሽ ካውንስል ወይም በሰራተኞቹ ወይም በወኪሎችና በስራ ተቋራጮች የጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰት የሞት ወይም የአካል ጉዳት ብሪቲሽ ካውንስልን ተጠያቂ የማያደርግ መሆን የለበትም። እንዲሁም በእነዚህ አካላት የሚፈጸም የማጭበርበር ወይም በህግ ሊወሰኑ ወይም ሊቀሩ የማይችሉ ተጠያቂነቶች ብሪቲሽ ካውንስልን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

12.2. በክፍል 12.1 ላይ የተገለጸው እንዳለ ሆኖ ብሪቲሽ ካውንስል በአካል ወይም በደረገጽ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶችን ሲከታተሉ በግል ንብረትዎ ላይ ለሚደርስ የመጥፋት ወይም የመጎዳት ችግር ሃላፊነት የማይወስድና ተጠያቂ የማይሆን መሆኑን በግልጽ ያሳውቃል። የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶችን በአካል በመከታተል ላይ ከሆኑ የግል ስልክዎን፣ ታብሌትዎን ወይል ላፕቶፕ ትተው መሄድ የለብዎትም። በተጨማሪም ብሪቲሽ ካውንስል በማንኛውም ሁኔታ ከዚህ ስምምነት ጋር በተያያዘ ወይም በስምምነቱ የተነሳ የሚነሳ በሚፈጠርብዎ የትርፍ ማጣት፣ የንግድ መክሰር ወይም ማንኛውም የፍይናንስ ማጣት በስምምነቱ መሰረት ተጠያቂ አይሆንም።

12.3 በ12.1 እና በ12.2 የተጠቀሱትን ሀረጋት መሰረት በማድረግ የብሪቲሽ ካውንስል ከስምምነቱ ጋር የተያያዘ ተጠያቂነት ለምርቱ ከተከፈለው አጠቃላይ ክፍያ ጋር እኩሌታ ያለው ይሆናል።

13. አጠቃላይ ስምምነት

13.1 እነዚህ አጠቃላይ ደንቦችና ሁኔታዎች፣ ልዩ ደንቦችና ሁኔታዎች፣ ተጨማሪ ደንቦችና ሁኔታዎች፣ የምዝገባ ማመልከቻና ማረጋገጫ ሰነዶች እና በሽያጭ ሁኔታዎች ላይ የተገለጹት ሰነዶች እንዲሁም በብሪቲሽ ካውንስል የግል መረጃ ጥበቃ ህግ ድረ ገጽ https://www.britishcouncil.org/privacy-cookies/data-protection ላይ ያሉ ህግጋት እና በድረ ገፅ ስለሚሰጡ አልግሎቶች አጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎች ላይ ያሉት መመሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቱን በሚመለከት የሚፈጸመው ስምምነት አካል ናቸው።

13.2 በክፍል 13.2 ላይ የተገለጹት የሽያጭ ሁኔታዎች እና ሌሎች ሰነዶች በንግድ ሁኔታዎች በተለመደው የአሰራር ሂደት የሚካተቱ መመሪያዎችን ሳይጨምር ነው

13.3 በ13.1 እና በ13.2 የተጠቀሱትን ሀረጋት መሰረት በማድረግ የብሪቲሽ ካውንስል ከስምምነቱ ጋር የተያያዘ ተጠያቂነት ለምርቱ ከተከፈለው አጠቃላይ ክፍያ ጋር እኩሌታ ያለው ይሆናል።

14. መብትንና ግዴታን መተው

14.1. በዚህ ውል የተቀመጡት መብቶችንና ግዴታዎችን ለመተው (ዌይቭ ማድረግ) የሚቻለው በጽሁፍ የተደገፈ ሲሆን እና የሚመለከተውም ወገን እንዲሁም ተፈጻሚ ሁኔታዎች ይህ መብትንና ግዴታን የመተው አንቀጽ (ዌይቨር) በቀጥታ የሚመለከተው /የሚመለከታቸው ሲሆን ነው፡፡

15. ውል ማቋረጥ

15.1. በዚህ ኮንትራት ውስጥ ያሉ ማናቸውም አንቀጽ (ወይም የአንቀጹ ክፍል) በማንኛውም ፍርድ ቤት ወይም የሚመለከተው ብቃት ያለው ባለስልጣን መስሪያ ቤት መርምሮ ዋጋ የሌለው፤ ህጋዊ ያልሆነ፤ ወይም እንዲፈጸም ማስገደድ የማይቻል ሆኖ/ሆነው ካገኘ፤ ይህ አንቀጽ ወይም የአንቀጹ ክፍል እንደአስፈላጊነቱ የዚህ ውል ክፍል እንዳልሆነ የሚቆጠር ይሆናል፡፡ ይህ ሲሆን ይህ ግን በውሉ ውስጥ ያሉት ሌሎች አንቀጾች ህጋዊነት እና ተፈጻሚነት እንደተጠበቀ ይቀራል፡፡

16. የሚተገበሩ ህጎች እና የግጭት አፈታት

16.1. የእንግሉዝኛ ቋንቋ ምርት በተሰጠበት ክልል ውስጥ ለሚተገበሩ ማንኛውም የግዴታ ሕጎች ተገዥ ሲሆን በውሉ ላይ ወይም ከኮንትራቱ ወይም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ (ምንም ዓይነት ያልሆነን ጨምሮ) የውል ክርክር ወይም የይገባኛል ጥያቄ) ፡፡ ጥርጣሬን ለማስወገድ ልዩ ውሎች እና ሁኔታዎች እስካልተገለፁ ድረስ በኤሌክትሮኒክ መንገድ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከተጠናቀቀ ይህ ውል በእንግሊዝ ውስጥ እንደተቋቋመ ተቆጥሯል ፡፡

16.2 ብሪቲሽ ካውንስል ከድርጅቱ ጋር የሚኖርዎትን ቆይታ ወይም ተሞክሮ እጅግ በጣም ጥሩ ለማድረግ ይፈልጋል፡፡ እናም አስተያየትዎን እና ምን ያህል በአግልግሎታችን እንደረኩ ወይም እንዳልረኩ የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ ከእርስዎ በደስታ ይቀበላል ፡፡ ከኮንትራቱ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት እባክዎን የብሪቲሽ ካውንስል ድረ ገጽ (http://www.britishcouncil.org/contact/about-customer-services) ውሰጥ የሚገኙትን አስተያየቶች እና ቅሬታዎችን መግለጫ ገጾች ይመልከቱ እና የተገለጹትን የምዝገባ ሂደቶችን ይከተሉ፡፡

16.3 አቤቱታ፣ክርክር ወይም የይገባኛል ጥያቄ በእርስዎ እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል በተደረገው ውይይት ሊፈታ የማይችል ከሆነ የእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ከኮንትራቱ በሚነሱ ማናቸውም የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ (ብቸኛ ያልሆነ) ልዩ ስልጣን ይኖረዋል ፡፡ ይህ ማለት ከኮንትራቱ ጋር የሚዛመዱ ሁሉም የይገባኛል ጥያቄዎች በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ዳኛ (ወይም በበርካታ ዳኞች) በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ሊፈቱ ይችላሉ ማለት ነው ፡፡ ሆኖም የብሪቲሽ ካውንስል እርስዎ ይህንን ውል ቢጥሱ በእርስዎ ላይ እርስዎ በሚኖሩበት ሀገር ወይም በሌላ በማንኛውም ሀገር ውስጥ ክስ የመመስረት መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

17. ብሪቲሽ ካውንስልን ስለማግኘት

17.1. ስለዚህ ኮንትራት ወይም የብሪትሽ ካውንስል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት ዙሪያ ማንኛቸውም ጥያቄዎች ፣ አስተያየቶች ወይም መረጃ የማግኘት ፍላጎት ካሉዎት እባክዎን እኛን 251911512835 ላይ ወይም ድረ ገጻችን https://ethiopia.britishcouncil.org/ ላይ ያግኙን

18. ለእርስዎ ማሳሰቢያዎች

18.1 የብሪቲሽ ካውንስል በ ‹ፖርታል› በኩል ወይም በምዝገባ ማመልከቻዎ ውስጥ ባካተቱት ኢሜል አድራሻ በኩል በዚህ ውል የተጠቀሰውን ማሳሰቢያ ሊያገኝልዎ ይችላል ወይም ሊልክልዎ ይችላል፡፡

19. ሰለ ሽያጭ ሁኔታዎች ስምምነት

19.1 በድረ ገጽ ወይም በመረጃ መረብ

እንደሁኔታው “እስማማለሁ” ወይም “ተስማማ እና ክፈል” የሚለው በድረገጽ / በመረጃ መረብ የሚገኘው ማያያዣ ላይ ጠቅ በማድረግ ፣ እርስዎ በሽያጭ ሁኔታዎች እንደሚስማሙ ያረጋግጣሉ፡፡ የቦታ ማስያዣ ማረጋገጫዎን ወይም Booking Confirmation ሲቀበሉ (ከላይ ባለው አንቀጽ 3 እንደተመለከተው) ህጋዊ ና አስገዳጅ የሆነው ውሉ ወደመሆን ይመጣል ወይም ህጋዊነቱ ይረጋገጣል፡፡

19.2 በአካል

የሽያጭ ሁኔታዎችን የያዘ ወረቀት ኮፒ ላይ በመፈረም በውሉ እንደሚስማሙ ያረጋግጣሉ ፡፡ የብሪቲሽ ካውንስል ተወካይ ክፍያዎን መቀበሉን ሲያምን ውሉ ህጋዊ ና አስገዳጅ ወደመሆን ይመጣል ወይም ህጋዊነቱ ይረጋገጣል፡፡

ክፍል 2: - የዲጂታል አገልግሎት ደንብ እና ሁኔታዎች (ከመረጃ መረብ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶች ጋር በተያያዘ)

1. እርስዎ “እስማማለሁ” አመልካች ሳጥኑን ወይም ማያያዣውን ጠቅ በማድረግ፣ የሚከተሉትን ያረጋግጣሉ-

  • የ‹ዲጂታል› የአገልግሎት ውሎች እና ስምምነቶች አንብበው ተስማምተዋል
  • ኢ-ኮርስ ወይም በመረጃ መረብ የሚሰጥ ትምህርት ክፍለ-ጊዜ እየገዙ እንደሆነ (ለምሳሌ በመረጃ መረብ የሚሰጥ ምርት ወይም በመረጃ መረብና በአካል/በክፍል ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት) ይገንዘቡ፡፡ እናም እነዚህ የ‹ዲጂታል አገልግሎት› ደንብና ሁኔታዎች ብሪቲሽ ካውንስል በድረገጽ ከሚሰጠው አገልግሎት ውል ጋር ብቻ የሚዛመዱ መሆኑን ይገንዘቡ፡፡

2. ሌሎች አስፈላገ ደንቦች

2.1 በእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርት በሙሉ ወይም በከፊል በቨርችዋል ወይም በመረጃ መረብ የሚቀርብ ከሆነ የሚከተሉትን ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ ፡፡ (ሀ) ዲጂታል አገልግሎቱ በሶስተኛ ወገን የድር አሳሽ (እንደ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ፣ Chrome እና ፋየርፎክስ ባሉ) በኩል ስለሚቀርብ ፣ የደር አሳሾቹን ተገቢ የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት መመሪያን ማንበብ አለብዎት፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የድር አሳሽዎ ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ ፡፡ የብሪቲሽ ካውንስልም እንደ አንድ የግብይቱ ሂደት አካል ወደእነዚህ ውሎች እና የግላዊነት መመሪያ ማያያዣዎች (ሊንክ) እናቀርባለን። (ለ) የብሪቲሽ ካውንስል በዲጂታል አገልግሎቱ እና በዲዛይን ፣ አወቃቀር ፣ 'እይታ እና ስሜት' እና በዲጂታል አገልግሎት አደረጃጀት ውስጥ የሁሉም የአእምሮአዊ መብቶች ባለቤት ወይም ፈቃድ ሰጪ ነው ፡፡ ለዲጂታል አገልግሎት የሚመለከተውን ክፍያ በመክፈል የብሪቲሽ ካውንስል በእነዚህ ውሎች እና የአጠቃቀም ሁኔታዎች ብቻ መሠረት በማድተግ ዲጂታል አገልግሎቱን ለማግኘት እና ለመጠቀም ልዩ ያልሆነ ፣የማይተላለፍ ፈቃድን ይሰጥዎታል ፡፡ (ሐ) የሚቀጥሉትን ላለማድረግ ተስማምተዋል

  • የዲጂታል አገልግሎቶችን ለሌላ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ሕጋዊ አካል መስጠት ፣
  • የብሪቲሽ ካውንስል የሚሰጠውን አገልግሎት ማስተጓጎል፣ጣልቃ መግባት ወይም መገደብ ፤
  • በዲጂታል አገልግሎት ውስጥ የተሳሳቱ ፣ አፀያፊ ፣ ወሲባዊ ፣ ስም አጥፊ ፣ አስጊ ፣ አስጸያፊ ወይም ሕገ-ወጥ ወይም የአእምሮአዊ ንብረት መብትን የሚጥሱ ማንኛውንም አስተያየቶች ወይም ነገሮች መጫን ወይም ማሳየት፤
  • የዲጂታል አገልግሎቱን መመርመር፣ መፈተሽ ወይም ተጋላጭነቱን መፈተን ወይም ከዲጂታል አገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም የተጠቃሚ ማረጋገጫ ወይም የደኅንነት መቆጣጠሪያዎችን ለማለፍ ወይም ለመደበቅ መሞከር፣
  • በሕግ ከሚፈቀደው በስተቀር የዲጂታል አገልግሎት ክፍልን የሚመሰርቱ ማናቸውንም ሶፍትዌሮች ወይም ሌላ ኮድ ወይም ስክሪፕቶች በተቃራኒው (reverse ) ማጠናቀር ፣ ማሰራጨት ፣ በተቃራኒው (reverse ) ኢንጅነር ማድረግ፤ መበታተን፣ መገልበጥ፣ መቀየር፤ ወይም ማሻሻል ወይም ደግሞ ቫይረስ ፣ ዲጂታል ትል/ዎርም ፣ ትሮጃን ፈረስ ወይም ሌላ ጎጂ ወይም ረባሽ አካልን የያዘ ማንኛውም መረጃ ማሰተላለፍ፣
  • በግልጽ በዲጂታል አገልግሎቱ ደንብና ሁኔታዎች ላይ እስካልተቀመጠ ድረስ በብሪቲሽ ካውንስል ወይም በዲጂታል አገልግሎት ሰጪ ሶስተኛ አካል የቀረቡትን ማንኛውንም ፋይሎች ወይም ሌሎች ፋይሎች መለወጥ ፣መቀየር፣ ማሻሻል ፣ መሰረዝ ፣ ጣልቃ መግባት ወይም አለአግባብ መጠቀም
  • ማንኛውንም ተፈጻሚ የሆነ ህግ በመጣስ የዲጂታል አገልግሎቱን መጠቀም፡፡

 

ክፍል 2: - የዲጂታል አገልግሎት ደንብ እና ሁኔታዎች (ከመረጃ መረብ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምርቶች ጋር በተያያዘ) - የቀጠለ

(መ) በቀን ማስያዣ ማረጋገጫዎ (Booking Confirmation ) ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ዲጂታል አገልግሎቱን እንዲገኙ ለማድረግ እንጥራለን ፡፡ ሆኖም በመረጃ መረብ ሁኔታ ምክንያት የብሪቲሽ ካውንስል የዲጂታል አገልግሎቱን ያለማቋረጥ ወይም ከስህተት ነፃ እንደሚሆን ዋስትና አይሰጥም ወይም ዋስትና መስጠት አይችልም። መረጃ መረብን ጨምሮ በመገናኛ አውታሮች እና መገልገያዎች ላይ መረጃ በማስተላለፍ ወቅት ለሚከሰቱ ማናቸውም መዘግየቶች ፣ የአቅርቦት መቋረጦች ፣ ወይም ለሌላ ማንኛውም ኪሳራ ተጠያቂ አይደለንም፡፡ እናም የዲጂታል አገልግሎቱ እንደነዚህ ያሉ ተመሳሳይ የመረጃ አውታሮች አጠቃቀም ጋር የሚከሰቱ የመገደብ ፣ የመዘግየት እና ሌሎች ችግሮች ተጋላጭ (subject) ሊሆን እንደሚችል አምነዋል ፡፡ (ሠ) ዲጂታል አገልግሎቱን ለመጠቀም አስፈላጊ የሆኑትን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌሮች እና ቴሌኮሙኒኬሽኖች በሙሉ እንዲኖርዎ ማድረግ የእርስዎ ኃላፊነትዎ ሲሆን የመረጃ መረብ አገልግሎት ሰጭዎችን ክፍያን ጨምሮ ለሁሉም ተዛማጅ ወጪዎች ኃላፊነቱ የእርሰዎ ነው፡፡ (ረ) የኃላፊነት ማስተላለፊያዎች እና የኃላፊነት ገደቦች- (i) ምንም እንኳን የዲጂታል አገልግሎቱ ይዘት ትክክለኛ እና የተዘመነ መሆኑን ለማረጋገጥ በቂ ጥረት የምናደርግ ቢሆንም ይዘቱ እንዲህ እንደሆነ ምንም አይነት ዋስትና ወይም ማስተማመኛ አንሰጥም። (ii) ሕጉ እስከሚፈቅደው ድረስ፤ በግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በእኛ ድረገጽ ወይም በውስጡ ባለው ይዘት ላይ፤ ማንኛቸውንም ሁኔታዎችን (conditions) ፣ ዋስትናዎችን (warranties)፣ ውክልናዎችን ወይም ሌሎች ደንቦችን እናስወግዳለን። (iii) የብሪቲሽ ካውንስል የመናገርን ነጻነት ያበረታታል፡፡ ነገር ግን በዲጂታል አገልግሎት አማካይነት በግለሰቦች የተገለፁት አስተያየቶች የብሪትሽ ካውንስል ምክር ቤት እይታዎችን ላይወክል ይችላል ፡፡ (iv) ማንኛውም ወገን በግድየለሽነት (ብሪቲሽ ካውንስል ሰራተኞቹ ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ) የሞት ወይም የግል ጉዳትን ቢያስከትል ወይም የማጭበርበር ተግባር ወይም በማንኛውም ሕግ ተጠያቂነት ውስን በማይሆንበት በሌላ ሁኔታ ውስጥ እነኝህ ደንብ እና ሁኔታዎች ጉዳት አስፈጻሚውን ነጻ አያደርጉትም፡፡ (v) በማንኛውም ሁኔታ የብሪቲሽ ካውንስል ለማንኛውም የተፈጸመ ወይም ተፈጸመ የተባለ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ወይም ተያያዥ ኪሳራ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ (vi) ከላይ በተጠቀሰው መሠረት፤ ከዚህ ደንብና ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ከውልም ሆነ ከውል ውጭ የሆነ፣ ከቸልተኝነት፣ የሕግ ግዴታን ከመጣስ ወይም ካለመጣጣም ጋር በተያያዘ የብሪቲሽ ካውንስል ተጠያቂ ቢሆን ከፍተኛው የተጠያቂነት መጠን ለዲጂታል አገልግሎት ከተከፈለው ወይም ከሚከፈለውን ክፍያ መጠን መብለጥ የለበትም። (ሰ) ከዲጂታል አገልግሎቶች የአገልግሎት ደንብ እና ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ

እነዚህን ደንብና ሁኔታዎች አንብቤ ተስማምቼያለሁ

በሽያጭ ውል መሠረት ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ ​​በብሪቲሽ ካውንስል የዲጂታል አገልግሎቱን ወዲያውኑ ለእኔ (ለሽያጭ ውሎች ከተጠቀሰው የ14 ቀን ስረዛ ጊዜ በፊት) እንደሚሰጠኝ እስማማለሁ እናም አረጋግጣለሁ ፡፡ የዲጂታል አገልግሎት መግቢያ ከተሰጠኝ በሁዋላ ውሉን የመሰረዝ መብት እንደማይኖረኝ እንደተረዳሁ አረጋግጣለሁ