የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ (UKVI) ለማግኘት ሲያመለክቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ደረጃዎትን ማሳየት ያስፈልግዎታል?

በUKVI ተቀባይነት ያላቸው አስተማማኝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተናዎች [Secure English Language Tests (SELT)] ዝርዝር ውስጥ IELTS ይገኛል። የIELTS የፈተና ውጤት ማግኘት የሚፈልጉት የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ (UKVI) እንዲሰጥዎት ለማመልከት ከሆነ UKVI በሚፈቅደው በተወሰነ የፈተና ማዕከል ፈተናውን መውሰድ ያስፈልጎታል።

ማሳሰቢያ፦ በዲግሪ ደረጃ ወይም ከዚያ በላይ በአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመማር፣ ደረጃ 4 የተማሪ ቪዛ ለማግኘት የሚያመለክቱ ከሆነ የመረጡት ተቋም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ረገድ ያወጣውን መሥፈርት አስቀድመው ማጣራት ይኖርብዎታል፤ ምክንያቱም አብዛኞቹ ተቋሞች ለዚህ ጉዳይ [Secure English Language Tests (SELT)] እንዲወስዱ አይጠብቁብዎትም።

IELTS ለመፈተን ይመዝገቡ።

የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚሰጥ IELTS Academic ፈተና

ይህ ፈተና የሚዘጋጀው ወደ ዩኬ ለመሄድ ለሚፈልጉ ተፈታኞች ወይም ከዲግሪ በታች በሆነ ደረጃ ለመሠልጠን ወይም ለመማር ለሚፈልጉና የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በቀጥታ ማመልከት ላለባቸው አመልካቾች ነው። ፈተናው መስማት፣ ማንበብ፣ መጻፍና መናገርን ያካተተ ነው።

አሁኑኑ ይመዝገቡ
ማሟላት ያለብዎትን ነጥብ ያጣሩ

የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚሰጥ IELTS General Training ፈተና

ይህ ፈተና የሚዘጋጀው ወደ ዩኬ ለመሄድ ለሚፈልጉ ተፈታኞች ወይም ከዲግሪ ባነሰ ደረጃ ለመሠልጠን ወይም ለመማር ለሚፈልጉ ነው። ፈተናው መስማት፣ ማንበብ፣ መጻፍና መናገርን ያካተተ ነው።

አሁኑኑ ይመዝገቡ
ማሟላት ያለብዎትን ነጥብ ያጣሩ

IELTS Life Skills A1

ይህ ፈተና የተዘጋጀው ለቤተሰባቸው፣ ለትዳር ጓደኛቸው ወይም ለኑሮ አጋራቸው የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ለሚያመለክቱና እንግሊዝኛ የመናገር እና የመስማት ችሎታቸውን እንዲያሳዩ ለሚጠበቅባቸው ነው።

●      ደረጃ A1Common European Framework of Reference for Languages (CEFR)] ውስጥ የተካተተ ሲሆን National Qualification Framework (NQF)] ውስጥ ከሚገኘው ESOL Entry 1 ጋ አቻ ነው።

●      ፈተናው መናገርን እና መስማትን ያካትታል

አሁኑኑ ይመዝገቡ
ማሟላት ያለብዎትን ነጥብ ያጣሩ

IELTS Life Skills B1

ይህ ፈተና የተዘጋጀው፣ የዩኬ ቪዛ እና የዜግነት/የመኖሪያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አመልክተው ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ እንግሊዝኛ የመናገር እና የመስማት ችሎታ እንደመስፈርት ለሚፈለግባቸውና ይህንን ማሳየት ለሚፈልጉ ሰዎች ነው።

●      ደረጃ B1 በ Common European Framework of Reference for Languages (CEFR)] ውስጥ የተካተተ ሲሆን National Qualification Framework (NQF)] ውስጥ ከሚገኘው ESOL Entry 3 ጋ አቻ ነው።

●      ፈተናው መናገርን እና መስማትን ያካትታል

አሁኑኑ ይመዝገቡ
ማሟላት ያለብዎትን ነጥብ ያጣሩ

እርስዎ የሚፈልጉት ይህን ካልሆነ እባክዎ ለሌሎች ዓላማዎች የተዘጋጁትን ስለ IELTS የሚገልጹትን ገጾች ይጎብኙ።

በዚህ ክፍል ውስጥ