75 years in Ethiopia
British Council 75 years in Ethiopia  ©

British Council 

75 ዓመታት በኢትዮጵያ

 

ብሪቲሽ ካውንስል እና ጄነራል ዊንጌት

በ ሚያዚያ ፩፱፫፰ ዓ ም በንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በተበረከተ ቦታ ላይ ብሪቲሽ ካውንስል ጄነራል ዊንጌት የተባለውን ራሱን የቻለ የወንዶች ትምህርት ቤት አቋቋመ። ብሪቲሽ ካውንስል የትምህርት ቤቱን ዋና ሃላፊና ብዙ ሰራተኞችን በማቅረብ እንዲሁም የአመት የጥገና ወጪውን በመሸፈንም ድጋፍ አድርጓል ። በ ፩፱፭፫ ብሪቲሽ ካውንስል ና የ ኢትዮጵያ መንግስት በተፈራረሙት የዊንጌት ስምምነት መሰረት ለጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት እድሳት የሚውል ሃምሳ ሺ ፓውንድ በስራ ላይ ውሏል ። ጄኔራል ዊንጌት በ ፩፱፮፱ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ እስኪሆን ድረስ በብሪቲሽ ካውንስል ድጋፍ ይሰጠው ነበር ።

Emperor Haile Silassie Laying a foundation for a new section in General Wingate School
Emperor Haile Selassie I, laying the foundation for a new section of the General Wingate School in Addis Ababa, Ethiopia, 1949 ©

British Council

Ato Tamrat Kebede
Ato Tamrat Kebede - Former student of the General Wingate School ©

Nebiyou Worku

ከቀድሞ የጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት  ተማሪ 

" ብሪቲሽ ካውንስል ለጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት መምህራንን እና መማሪያ መጽሃፍትን በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጸኦ አድርጓል:: ትምህርት ቤቱ ለሀገሪቱ ያገለገሉ ወጣቶችን ኮትኩቶ ያሳደገ ነበር :: የብሪቲሽ ካውንስል ላይብረሪም ለአንባቢያን ትልቅ እድል የከፈተ ነበር:: "

" ዊንጌት ለየት ያለ ትምህርት ቤት ነበር:: ለስነ ጽሁፍ እና ለማንበብ አመቺ ቦታ ነበር :: ውስጡ ለአስተዳደር ቀላል የነበረ ሲሆን መጠነኛ የሆነች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የማየትና የመማር እድል ሰጥቶናል ማለት እችላለሁ::"

"ጥራት ላይ ያተኮረ ትምህርት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚደገፍ ሳይሆን ለዘለቄታው የሚደገፍበት ሁኔታ ኖሮ ይቺ ሀገር የሚያስፈልጋትን የሰው ኃይል የሚያመርት ጥራት ተኮር የትምህርት ስርዓት ቢዘረጋ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ:: "

አቶ ታምራት ከበደ 
የጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪ 
የኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ