የዩኒቨርስቲ ተማሪም ይሁኑ ቅጥር ሰራተኛ፣ አስተማሪም ይሁኑ በሥልጠና ላይ ያሉ ሥራ አስኪያጅ፣ ወይም በቀጣይ ምን እንደሚሠሩ ዕቅድ እያወጡ ያሉ ግለሰብ በአዲስ አበባ የሚገኘው የብሪቲሽ ካውንስል የሥልጠና ማዕከላችን እጅግ በርካታ የመማሪያ ቁሳቁሶችና የትምህርት አማራጮች ያቀርብልዎታል። እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመማር ያለዎትን ጉጉት እንዲያሳኩ የመርዳት ብቃት ያለው ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንሰጣለን። የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርቶችን፣ ለፈተና የሚደረጉ ዝግጅቶችን፣ ሙያዊ ክህሎቶች ለማዳበር የሚረዱ አጫጭር ኮርሶችንና የዩናይትድ ኪንግደም ፈተናዎችን እንሰጣለን፤ ይህም እርስዎ ወይም ከእርስዎ ጋር የሚሠሩ ሰዎች በሥራና በትምህርቱ ዓለም እንዲሁም በግል ሕይወታችሁ ስኬታማ የመሆን አጋጣሚያችሁን ያሳድግላችኋል።
ድረ ገጻችንን መጐብኘትዎን ይቀጥሉ ወይም ዛሬውኑ ይደውሉልን።