ሥራ ቦታ ላይ የሚያስፈልገው የመጻፍ ክህሎት
በጣም ብዙ ኢሜይል ይደርስዎታል? ባለፈው ሳምንት የጠየቁትን አስፈላጊ መረጃ ለማግኘት አሁንም መልስ እየጠበቁ ነው? ይህ እውቀት የሚጨምር የትምህርት ክፍለ ጊዜ በየዕለቱ ማከናወን ያለብዎትን ብዛት ያለው ሥራ በሚገባ ለማደራጀትና ከሙያ ጋር የተያያዙ የረጅም ጊዜ ግቦችዎን ለማሳካት የሚያስፈልጉዎትን ኢሜይል የመጻፍ ክህሎቶች እንዲያዳብሩ ይረዳዎታል።
የሥራ ዕቅድ በጽሑፍ ማስፈር
ይህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተለያዩ የሥራ ሐሳቦችን በጽሑፍ አስፍረው ለገበያ እንዲያቀርቡ ይረዳዎታል። በዚህ ሥልጠና፣ የአንባቢዎችዎን ፍላጎት የሚያሟላና ቅድም ተከተሉን የጠበቀ የሥራ ዕቅድ ማዘጋጀት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች የሚያሳምን አነጋገር መጠቀም የሚያስችል ለተግባር የሚያነሳሳ ጽሑፍ የመጻፍ ክህሎት ማዳበር ይችላሉ።
ጠቃሚ ሪፖርት መጻፍ
ይህ ጠቃሚ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚያዘጋጇቸውን ሪፖርቶች ለማቀድ፣ ለማዋቀር፣ ለመጻፍና ለማጣራት የሚያስፈልጉትን መሠረታዊ ክህሎቶች በተመለከተ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖርዎት ያደርጋል።
የተሻለ ይዘት ያላቸው ኢሜይሎችና ደብዳቤዎች
በጣም ብዙ ኢሜይል ይደርስዎታል? ባለፈው ሳምንት የጠየቁትን አስፈላጊ መረጃ ለማግኘት አሁንም መልስ እየጠበቁ ነው? ይህ እውቀት የሚጨምር የትምህርት ክፍለ ጊዜ በየዕለቱ ማከናወን ያለብዎትን ብዛት ያለው ሥራ በሚገባ ለማደራጀትና ከሙያ ጋር የተያያዙ የረጅም ጊዜ ግቦችዎን ለማሳካት የሚያስፈልጉዎትን ኢሜይል የመጻፍ ክህሎቶች እንዲያዳብሩ ይረዳዎታል።
ለተሰበሰቡ ሰዎች ንግግር የማቅረብ ክህሎት
ይህ ግንዛቤ የሚያሰፋ ዎርክሾፕ ንግግር የማቅረብ ድፍረትና ጥበብ እንዲያዳብሩ ይረዳዎታል። ንግግር ማዘጋጀትና ማቅረብ የሚቻልባቸውን ዘዴዎች በዝርዝር ይመለከታሉ፤ ከዚህም ሌላ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የአድማጮችን ቀልብ መቆጣጠር ስለሚችሉባቸው መንገዶች በሰፊው ይማራሉ።
ትክክለኛ የቃላት አጠራር
ይህ እውቀት የሚጨምር የትምህርት ክፍለ ጊዜ በተለይ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ያልሆነ ሰዎች ላሉባቸው ችግሮች ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን የቃላት አጠራርዎን፣ የድምፅ ቃናዎትን፣ የንግግር ፍጥነትዎትንና ቆም እያሉ የመናገር ችሎታዎትን እንዲያሻሽሉ ይረዳዎታል። ሥልጠናው አመራር ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች፣ በእነርሱ ሥር ያሉ ሠራተኞች ይህን እንዲያሳኩ ማድረግ የሚችሉበትን መንገድ ይጠቁማቸዋል።
አሠልጣኞችን ማሠልጠን
ይህ ጠቃሚ የትምህርት ክፍለ ጊዜ አሠልጣኞች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ ተቆጣጣሪዎችና የሰው ኃይል ክፍል ሠራተኞች እውቅ አሠልጣኞች የሚጠቀሙባቸውን ምርጥ የሆኑ ሥራ የሚያቀልሉ ዘዴዎች እንዲቀስሙ ያስችላቸዋል።
ሰፊ የሥራ ግንኙነት
ይህ የአስተሳሰብ አድማስን የሚያሰፋ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ከማንኛውም ሰው ጋር፣ በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ የሥራ ግንኙነት እንዲመሠርቱ ያስችልዎታል! ጥሩ ልምድ ያለው አሠልጣኝ የመተማመን ስሜትዎ እንዲያድግ የሚረዱ ዘዴዎችን እና ሐሳቦችን በማሳወቅ፣ አስደሳች የሆነ ሰፊ የሥራ ግንኙነት እንዲመሠርቱ እና ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆኑ ይረዳዎታል።