የንግድ ድርጅትም ሆኑ የትምህርት ተቋም፣ የእርዳታ ድርጅትም ሆኑ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት፣ በምትፈልጉት መልኩ እንድናስተናግዳችሁ የሚያስችለን እንደ ሁኔታው የሚስተካከል አሠራር እና ሰፊ ልምድ አለን።
ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሕይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ፕሮጀክቶችን ከሚያካሂዱ የመንግሥት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የግል ንግድ ድርጅቶች እና ዓለም አቀፋዊ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሥራት ረገድ ጠንካራ ታሪክ አስመዝግቧል።
እሴቶቻችን
- እ. ኤ. አ. በ1934 የተቋቋመው ብሪቲሽ ካውንስል በ110 አገሮች እና ክልሎች ውስጥ ከ200 የሚበልጡ ቢሮዎች አሉት።
- በኢትዮጵያ ሥራ የጀመርነው እ. ኤ. አ. ከ1943 ጀምሮ ሲሆን ቢሯችን በአዲስ አበባ ይገኛል።
- ስለ ባህላዊ ግንኙነቶች፣ ስለ ቋንቋዎች እና ስለ ማኅበረሰቦች ጥሩ ግንዛቤ አለን።
- ስለ ማስተማር እና የቋንቋ ስልጠና ስለ መስጠት፣ ስለ በርካታ የሥነ ጥበብ ዘርፎች፣ ስለ ፈጠራ ኢንዱስትሪዎች፣ ወጣቶችን እና ማኅበረሰብን ስለ ማሳተፍ እንዲሁም ስለ አስተዳደር እና ለውጥ ጥልቅ እውቀት አለን።
- ከወጣት ተማሪዎች አንስቶ እስከ መንግሥት ሚኒስቴሮች ድረስ ግንኙነት አለን።
- ከዩናይትድ ኪንግደም መንግሥታዊ ተቋማት፣ ከብሪቲሽ ኤምባሲ፣ ከብሔራዊ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር ተቀራርበን እንሠራለን።
በዓለም ዙሪያ በ2012 (እ. ኤ. አ.) ያከናወንናቸው ነገሮች
- ከ12.5 ሚሊዮን ሰዎች ጋር በቀጥታ አብረን ሠርተናል።
- ባዘጋጀናቸው የሥነ ጥበብ አውደ ርእዮች፣ በአላት እና ዝግጅቶች ላይ 9.5 ሚሊዮን ሰዎች ተገኝተዋል።
- በእንግሊዝኛ ቋንቋ የትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ 308,000 ተማሪዎች ሰልጥነዋል።
- የዩናይትድ ኪንግደምን 2.7 ሚሊዮን ፈተናዎች ፈትነናል።
- በኢንተርኔት ላይ በሚገኙ ፕሮግራሞች አማካኝነት 4 ሚሊዮን የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪዎችን እና 41 ሚሊዮን ተማሪዎችን ረድተናል።
- 73.3 ሚሊዮን ሰዎች በዲጂታል ጣቢያዎቻችን ተጠቅመዋል፣ 485 ሚሊዮን ሰዎች የራዲዮ እና የቲቪ ፕሮግራሞቻችንን ተከታትለዋል፣ የህትመት ውጤቶቻችንንም አንብበዋል።
- የድረ ገጽ መረጃችን እንዳሳየው ያገኘው ነጥብ 58 በመቶ ነበር።
- በ50 አገራት የሚገኙ እና በአመታዊው የ Ipsos MORI ጥናት ላይ የተካፈሉ በፕሮግራሞቻችን ተጠቃሚ ከነበሩ 4,000 ታላላቅ ሰዎች መካከል 92 በመቶ የሚሆኑት ከእኛ ጋር መሥራታቸው በሥራው ዓለም ሕይወታቸው ላይ ለውጥ እንዳመጣ ገልፀዋል።
- 81 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከእኛ ጋር መሥራታቸው ለሚሠሩበት ድርጅትም ለውጥ እንዳመጣ ገልፀዋል።