Photo: Hendri Lombard
በየዓመቱ ከ90 አገሮች የተውጣጡ ሁለት ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች በብሪቲሽ ካውንስል በኩል ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ይወስዳሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የብቃት ደረጃችን ተማሪዎች አሉ በተባሉ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ፣ ግሩም የሆኑ የሥራ እድሎችን እንዲያገኙና ይበልጥ አርኪ ለሆነ ሕይወት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
በአስተማሪዎች፣ በመንግሥታት፣ በአሠሪዎችና በተማሪዎች ዘንድ አመኔታ ያተረፈው ብሪቲሽ ካውንስል አስፈላጊውን ድጋፍና ምክር ይሰጣል፤ እንዲሁም የፈተና ሥርዓቱ በየደረጃው የተሟላ እንዲሆን ተገቢውን ክትትል ያደርጋል።
ተማሪም ይሁኑ ወላጅ አሊያም ደግሞ የትምህርት ቤት ፈተናዎች አስተባባሪ የሚፈልጉትን መረጃ ከዚህ በታች ማግኘት ይችላሉ።