ፎቶ፦ አላ ኬይር
በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ዋና ዋና የሚባሉ ፈተና የሚያዘጋጁ የተለያዩ አካላትንና ዩኒቨርሲቲዎችን ወክለን ዓለም አቀፍ የሥራ ሙያ ፈተናዎች እንሰጣለን፦
- የብሪታንያ የሥራ ሙያ ብቃት ማረጋገጫዎች፤ ለምሳሌ፣ የሒሳብ ሥራ እና ሕግ።
- የዩኒቨርሲቲ ፈተናዎች፣ ለምሳሌ፣ ከተልእኮ ትምህርት ፕሮግራሞች ጋር የተያያዙትን ጨምሮ MBAs እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ፈተናዎች።
ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የፈተና ማዕከሎቻችን መጥተው ሊፈተኗቸው የሚችሏቸውን የዩኒቨርሲቲ እና የሙያ ፈተናዎችን እንፈትናለን። የፈተና አሰጣጣችን ከፍ ያሉ የጥራት መሥፈርቶችን የተከተሉ እንደሆኑ እንዲሁም የተማሪዎች የፈተና ወረቀቶችና ውጤቶች በሚስጥርና በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚያዙ ልናረጋግጥልዎት እንወዳለን።