ፎቶ፦ አላ ኬይር
የዩናይትድ ኪንግደምን የሥራ ሙያ ብቃት ማረጋገጫዎች በመያዝ ከፍ ወዳለ ደረጃ ይድረሱ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደጉን በቀጠለ መጠን ብዙ የሥራ መስኮች ይከፈታሉ። በእነዚህ እድሎች የመጠቀም ጥሩ አጋጣሚ የሚያገኙት ደግሞ ተፈላጊ ብቃቶች ያሏቸው ሰዎች ናቸው።
በዩናይትድ ኪንግደም ከሚሰጡ እጅግ ተፈላጊ ከሆኑ የሙያ ብቃት ማረጋገጫዎች ውስጥ አንዳንዶቹን እንዲያገኙ ማድረግ የምንችል ሲሆን ይህም በተሰማሩበት የሙያ መስክ እያደጉ እንዲሄዱ ያስችልዎታል። እነዚህን የብቃት ማረጋገጫዎች ለማግኘት ከአገር ውጪ መሄድ አያስፈልግዎትም።
የመሥሪያ ቤታችን ሠራተኞች፣ የሥራ ሙያ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡበት ጊዜ አንስቶ ውጤትዎን እስከሚቀበሉበት ቀን ድረስ ያልተወሳሰበና ከሙያው ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ልምድ እንዲያዳብሩ ለመርዳት በትጋት ይሠራሉ።
መፈተኛ ቦታ ከማዘጋጀት ጀምሮ የፈተና ቦርዱ የሠሩትን ፈተና የሚያይበትን ሂደት የሚቆጣጠሩ ሙያውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ተቆጣጣሪዎች እስከ መመደብ ድረስ ያለውን አጠቃላዩን የሥራ ሂደት የምንከታተለው እኛ ነን።
ከእርስዎ የሚጠበቀው ነገር ቢኖር ለፈተናው ተዘጋጅተው በእለቱ በቦታው መገኘት ብቻ ነው።
አብረውን የሚሠሩት እነማን ናቸው?
የሥራ ሙያ ሥልጠና በመስጠት በታወቁ በርካታ ተቋሞች መማርና ፈተናውን ኢትዮጵያ ውስጥ መፈተን ይችላሉ። ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ጋር አብረን እንሠራለን፦
- Association of Chartered Certified Accountants (ACCA)
- LCCI International Qualifications
- Chartered Institute of Purchasing and Supplies (CIPS)
- Chartered Insurance Institute (CII)
- Chartered Institute of Management Accountants (CIMA)
- City and Guilds
ምዝገባው የሚካሄደው እንዴት ነው?
የሥራ ሙያ ፈተና ለመፈተን መመዝገብ በጣም ቀላል ነው።
- በመጀመሪያ ከመረጡት የትምህርት ተቋም ጋር ይገናኙ፤ በመቀጠልም ለፈተናው በቀጥታ እነርሱ ዘንድ ይመዝገቡ።
- ከፈተናው ቀን ቢያንስ ከአንድ ወር በፊት ይህን ማድረግ ይኖርብዎታል።
ስንት ይከፈላል?
እኛ የምንጠይቀው ክፍያ የፈተና ቦርድ ለተለያዩ ወጪዎች የሚጠይቀውን ክፍያ አይጨምርም። እባክዎ ክፍያን በተመለከተ የፈተና ቦርዱን ያነጋግሩ።
የእኛ ዋጋ ለእያንዳንዱ ፈተና 75 የእንግሊዝ ፓውንድ ወይም ከእዚህ ጋር የሚመጣጠን የኢትዮጵያ ብር ነው።
በኃላፊነት የማንጠየቅባቸው ሁኔታዎች
ብሪቲሽ ካውንስልም ሆነ የፈተና ቦርዶች የሚሰጡት አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ። በመሆኑም ከቁጥጥራችሁ በላይ በሆኑ ምክንያቶች የተነሳ ምንም ዓይነት መስተጓጎል ቢፈጠር በኃላፊነት እንደማንጠየቅ ማስገንዘብ እንወዳለን።. ፈተናዎች ወይም የፈተና ውጤቶች ቢስተጓጎሉ፣ ቢሰረዙ ወይም ቢዘገዩ በተቻለ ፍጥነት ሁሉም ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ ማንኛውም ዓይነት ጥረት ይደረጋል። በዚህ ረገድ ብሪቲሽ ካውንስል የሚኖርበት ኃላፊነት የምዝገባ ክፍያውን ገንዘብ መመለስ ወይም በሌላ ጊዜ ፈተናውን በድጋሚ መስጠት ብቻ ነው።
ተጨማሪ መረጃ
ፈተናውን መፈተን እንዲችሉ እንዴት ልንረዳዎት እንደምንችል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን።