በትምህርት፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እና በሥነ ጥበብ ረገድ በምናከናውነው ሥራ አማካኝነት በዩናትድ ኪንግደምም ሆነ በዓለም ዙሪያ በሚኖሩ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ አምጥተናል።
ዓለም አቀፍ የግንኙነት መስመሮቻችንን፣ ልምዳችንንና በእኛ ላይ የጣሉትን እምነት በጥሩ ሁኔታ በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የተለያዩ ድርጅቶች ጋር አብረን በመሥራት ግቦቻቸውን እንዲያሳኩ እንረዳቸዋለን። ከእኛ ጋር በአጋርነት የሚሠሩትን በተመለከተ እንደ ሕጋዊ አካል ያለባቸውን ማኅበረሰባዊ ኃላፊነትና የንግድ ስልቶቻቸውን በሚገባ እናውቃለን። ከዚህ ባልተናነሰ ሕዝባዊና ሦስተኛ ወገን አጋሮቻችን ከእድገት፣ ከትምህርትና ከሥነ ጥበብ ጋር በተያያዘ ያሏቸውን ግቦች እናደንቃለን።
ከሌሎች ጋር በአጋርነት ስንሠራ ያገኘናቸው ስኬቶች ከእኛ ጋር መሥራት ያሏቸውን ጥቅሞች ያጎላሉ። ለምን ከእኛ ጋር አይሠሩም?