English language teachers

የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪ ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ባለሙያ(ELT)ከሆኑ፣ በሥራዎት ድጋፍ ሊሰጡዎት የሚችሉ በርካታ ነገሮችን በነፃ አቅርበንልዎታል።

እርስዎ በበኩልዎ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማድረግ ይችላሉ፦

  • በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮርሶችን ለመውሰድ ይመዝገቡ
  • የትምህርት ፕሮግራሞችንና መማሪያዎችን በነፃ ያውርዱ
  • ስለ ሥራ ሙያ ማሻሻያ፣ ስለ ትምህርታዊ ስብሰባዎች እና ስለ ብቃት ማሻሻያ የሚገልፁ ጠቃሚ ሃሳቦችን፣ ፅሁፎችን እና መረጃዎችን ያግኙ
  • የውይይት ቡድኖች አባል በመሆን የስልጠና መሣሪያዎችን ያግኙ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ቲቺንግ ኢንግሊሽ የሚለውን ድረገፃችንን ይጎብኙ፤ አሊያም ስለተለያዩ የስልጠና ክፍሎች የተሰጠውን አጭር ማብራሪያ ከዚህ በታች ይመልከቱ።

የመምህራን ስልጠና

ስለ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ማስተማሪያ፣ ስለ ማስተማሪያ ቴክኖሎጂዎች እና ስለ ሌሎች በርካታ ርእሰ ጉዳዮች የሚያስተምሩ ብዛት ያላቸው የመምህራን ማሰልጠኛ ኮርሶችን እንሰጣለን። ስለ መምህራን ስልጠና ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።

ማስተማሪያዎች

በሥራዎት ድጋፍ እንዲደረግልዎት፣ ለተማሪዎችዎ ተጨማሪ ማሻሻያ መሣሪያዎችን የሚፈልጉ ከሆነና ሥራ የሚበዛብዎት የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪ ወይም አሰልጣኝ ከሆኑ፣ ለአስተማሪዎች ባዘጋጀነው የብሪቲሽ ካውንስል ድረገፅ ላይ በርካታ ማስተማሪያዎችን በነፃ በማቅረብ ልንረዳዎት እንችላለን። ስለማስተማሪያዎቻችን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።

የትምህርት ፕሮግራሞቻችን

በትምህርት ፕሮግራማችን ላይ ያዘጋጀናቸውን በመማሪያ ክፍል ውስጥ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን ተከታታይ ሥራዎች ጨምሮ የትምህርት ፕሮግራሙን አጠቃቀምና መልመጃዎችን ማውረድ ይችላሉ። ቋንቋ ማስተማሪያዎችን የሚፈልጉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪ ከሆኑ፣ ብሪቲሽ ካውንስል በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግባቸው የትምህርት ፕሮግራሞችንና ማስተማሪያዎችን በማቅረብ ሊረዳዎት ይችላል። ስለ ትምህርት ፕሮግራሞቻችን የበለጠ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

መማሪያ ክፍል ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎች

ቋንቋ ማስተማሪያዎችን የሚፈልጉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪ ከሆኑ፣ በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግባቸውን መማሪያ ክፍል ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎችን በማቅረብ ልንረዳዎት እንችላለን። መማሪያ ክፍል ውስጥ ስለሚሠሩ ሥራዎች የበለጠ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

የቲቺንግ ኢንግሊሽ ጽሑፎች

ስለ ማስተማር ዘዴዎች እና ትግበራዎች ያለዎትን ግንዛቤ ማሳደግ የሚፈልጉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪ ከሆኑ፣ ልምድ ባላቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪዎች እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ባለሙያዎች (ELT) በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግባቸውን የቲቺንግ ኢንግሊሽ ጽሑፎች በማቅረብ ልንረዳዎት እንችላለን።የኢንግሊሽቲቺንግጽሑፎቻችንንያንብቡ።

እንግሊዝኛ ቋንቋ ለማስተማር በስነ ጽሑፍ መጠቀም

በስነ ጽሑፍ ላይ የተመሰረቱ ማስተማሪያዎችን የሚፈልጉ ከሆነ፣ ጽሑፎችን፣ የሚሠሩ መልመጃዎችን እና የሚደመጡ ማስተማሪያዎችን በማቅረብ ልንረዳዎት እንችላለን። በስነ ጽሑፍ ተጠቅመው የሚያስተምሩ አስተማሪዎችን ለመርዳት ያዘጋጀናቸውን ማስተማሪያዎች በሚመለከት የበለጠ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

ለመማሪያክፍሎችየተዘጋጀየታብሌትፕሮግራም

ለርን ኢንግሊሽ ኪድስ፦ ፎኒክ ስቶሪስ (ስኩል ኤዲሽን) በፊደሎች አነባበብ ላይ የተመሰረተ ታሪክ የያዘ ፕሮግራም ሲሆን ልጆች እንግሊዝኛ ማንበብ እና መናገር እንዲችሉ ይረዳቸዋል። እያንዳንዱ ታሪክ የፊደላት አነባበብ መለማመጃ፣ ጨዋታ እና መዝገበ ቃላትን ይዟል። የመምህሩ መመሪያ፣ ፕሮግራሙን እንዴት በክፍል ውስጥ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሙያዊ ምክር ይሰጣል።

ከአፕል አፕስቶር ላይ ያውርዱ (ለአይፓድ ብቻ)።