ባልታሰበ ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት ለሐምሌ ሁሉም የምክር አገልግሎት ክፍሎቻችን በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተይዘዋል ፡፡ የክረምት የልጆች ስልጠና ከ70% በላይ ቦታዎች ተይዘዋል። ፡፡ ልጅዎ መስከረም ላይ በሚጀመረው የስልጠና መርሃ ግብር እንደሚሳተፍ ተስፋ እናደርጋለን: ስለ ትዕግስትዎ እናመሰግናለን ፡፡
ለልጅዎ መልካም ጅማሬን ይስጡ – የሚወደድ ኢንግሊዝኛ ለህጻናት!
Primary Plus፣ የልጆች እንግሊዘኛ ኮርስ፣ እድሜያቸው ከ 8 እስከ 11 ያሉ ህጻናት ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ እና ለትምህርት በሚያነሳሳ ቦታ ራሳቸውን መግለጽ ይችሉ ዘንድ ያደረጋል።
እንግሊዘኛ ቋንቋ ለንግግር ጥቅም ላይ የሚውልበትን አካባቢ እንፈጥራለን። ልጆች በራሳቸው የትምህርት ማእከል ውስጥ እንዳሉ የእግሊዘኛ ችሎታቸውን በሚያሳድጉበት ጊዜ በራስ መተማመናቸው ይጨምራል።
ለትምህርት የሚያነሳሳ ፤ ተግባቦትን የሚያሳድግ ፤ የሚያዘጋጅ
ልጅዎ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛል:
- በአካባቢው ስለሚያውቃቸው ነገሮች ንግግር በማድረግ በራሳቸው ያላቸውን መተማመን እንዲያሳድጉ ያደርጋል ይህም ከመኝታ ቤታቸው እስከ ሰፈራቸው ድረስ ያካትታል
- በሚያስደስቱ ትግበራዎች እና የቡድን ፕሮጀክቶች ራሳቸውን መግለጽ – በገሀዱ አለም ውስጥ ያሉ አርእስቶችን ማሰስ ይህም ከባህር ጥልቀት እስከ ህዋ ድረስ ነው
- ከክፍል ውጪ ላላቸው የወደፊት ህይወታቸው ዝግጁ የሚያደርጋቸው ወሳኝ የህይወት ክህሎቶችን ማሳደግ