በኢንተርኔት እንግሊዝኛ ቋንቋ ይማሩ ©

British Council

ብሪቲሽ ካውንስል አዋቂዎች፣ ወጣቶችና ልጆች እንግሊዝኛ እንዲማሩ የሚያግዙ ኢንተርኔት ላይ በነፃ የሚገኙ ብዙ አማራጭ ያላቸው ዝግጅቶች አድርጓል። ዝግጅቶቹ ቪዲዮዎችን፣ የሞባይል አፕሊኬሽኖችን፣ አዝናኝ ጨዋታዎችን፣ ታሪኮችን፣ በመስማት የሚሠሩ ሥራዎችን እና የሰዋስው መልመጃዎችን ያካተቱ ናቸው።

በዚህ ክፍል ውስጥ

Learn English app

የለርን ኢንግሊሽ አፕሊኬሽኖች

አዝናኝና አስደሳች በሆኑ የመማሪያ አፕሊኬሽኖቻችን አማካኝነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን ያሻሽሉ! ሁሉንም የቤተሰብ አባላት ለመጥቀም ታስበው የተዘጋጁት አዝናኝ ጨዋታዎች፣ ፖድካስቶች፣ ቪዲዮዎችና አጫጭር ጥያቄዎች ቤትዎ ሆነው ወይም በጉዞ ላይ እያሉ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ ያግዙዎታል።