አዝናኝና አስደሳች በሆኑ የመማሪያ አፕሊኬሽኖቻችን አማካኝነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን ያሻሽሉ! ሁሉንም የቤተሰብ አባላት ለመጥቀም ታስበው የተዘጋጁት አዝናኝ ጨዋታዎች፣ ፖድካስቶች፣ ቪዲዮዎችና አጫጭር ጥያቄዎች ቤትዎ ሆነው ወይም በጉዞ ላይ እያሉ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ ያግዙዎታል።

የሚጠቀሙበትን የኮምፒውተር ፕሮግራም ይምረጡ፦

የእንግሊዝኛ ሰዋስው ይማሩ (የዩናትድ ኪንግደም እትም)

የእንግሊዝኛ ሰዋስው ይማሩ (የዩናትድ ኪንግደም እትም)

በሺዎች የሚቆጠሩ ጥያቄዎችን በያዘውና አመራማሪ በሆነው የሰዋስው መልመጃ መጽሐፍ ተጠቅመው የሰዋስው እውቀትዎን ያሳድጉ። ጥያቄዎቹ ለጀማሪዎችም ሆነ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የተዘጋጁ ናቸው።

ይህን ያውርዱ (Download)፦ iOS| Android| WP8

ይህን የዩናይትድ ስቴትስ እትም ያውርዱ (Download)፦ iOS| Android

በድምፅና በቪዲዮ እንግሊዝኛ ይማሩ

አድምጦ የመረዳት ችሎታዎን ለማሻሻል፣ ሰዎች በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው የሚግባቡበትን ትክክለኛ እንግሊዝኛ ለማወቅ ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እንዲሁም ያዳምጡ። እያንዳንዱ ቪዲዮና ፖድካስት የራሱ የሆነ የንግግሩ ጽሑፍና የመረዳት ችሎታ የሚፈትኑ መልመጃዎች አሉት።

ይህን ያውርዱ (Download)፦iOS| Android|Windows Phone 8

የቃላት ትክክለኛ አጠራር

አሳታፊ የሆነው የቃላት አጠራር ሰንጠረዥ ተነባቢና አናባቢ ፊደላትን እንዲሁም ሁለት አናባቢ ፊደላት ወይም ሁለት አናባቢ ድምፆችን (diphthongs) ለይቶ ያሳያል። በተጨማሪም ደጋግሞ መስማት የሚቻል የቃላት አጠራር (phonemes) ቅጂና የናሙና ቃላቱን ድምፅ ይዟል።

ይህን ያውርዱ (Download)፦iOS (ለአይፓድ ብቻ)

የልጆች እንግሊዝኛ መማሪያ፦ ንባብ መማሪያ ታሪኮች

በሕዋ ላይ ስለሚገኙ ሰላዮች የሚናገሩ አዝናኝ ተረቶችን ያንብቡ፤ ሌሎች ታሪኮችንም በያዘው በዚህ የኮምፒውተር ፕሮግራም የፊደላትን አጠራር ይማሩ። እያንዳንዱ ታሪክ የፊደል አጠራር መልመጃ የያዘ ከመሆኑም ሌላ ጨዋታና መዝገበ ቃላት አለው። ለወላጆች የቀረበው መመሪያ እንዴት ልጆችን እንግሊዝኛ ማስተማር እንደሚቻል እጅግ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል።

ይህን ያውርዱ (Download)፦ iOS (ለአይፓድ ብቻ)

የልጆች እንግሊዝኛ መማሪያ፦ ቪዲዮዎች

በዚህ የቪዲዮ ታሪኮችን በያዘው የኮምፒውተር ፕሮግራም አማካኝነት ልጆች የሚወዷቸውን እንደ ሊትል ሬድ ራይዲንግ ሁድ የመሳሰሉ ታሪኮችን ይመልከቱ። ቪዲዮው ንግግርም ያለው ሲሆን የትረካውን ጽሑፍ ይዟል፤ እንዲሁም ለወላጆች የቀረበው መመሪያ እንዴት ልጆችን እንግሊዝኛ ማስተማር እንደሚቻል እጅግ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል።

ይህን ያውርዱ (Download)፦Android (ጉግል ፕሌይ) | Android (አማዞን አፕ ስቶር)

በፖድካስት ቀላል እንግሊዝኛ ይማሩ

በፖድካስት ላይ የቀረቡት እንግዶቻችን በእንግሊዝ ኑሮ ምን እንደሚመስል ሲነጋገሩ በማዳመጥ የመስማት ችሎታዎንና የቃላት እውቀትዎን ያሻሽሉ። እያንዳንዱ ክፍል የንግግሩን ጽሑፍ የያዘ ከመሆኑም ሌላ የመረዳት ችሎታ የሚፈትኑ መልመጃዎች አሉት።

ይህን ያውርዱ (Download)፦ iOS| Android

Learning Time with Timmy

ለርኒንግ ታይም ዊዝ ቲሚ

ስድስት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ስለ ቁጥር፣ ቀለም፣ ቅርጽና ምግብ ለመማር ከቲሚና ከጓደኞቹ ጋር አስደሳች ጨዋታዎችን መጫወትና የእንግሊዝኛ ቃላትን መስማት ይችላሉ። ብሪቲሽ ካውንስል ከአርድማን አኒሜሽንስ ጋር በመተባበር ይህንን የኮምፒውተር ፕሮግራም አዘጋጅቷል። አርድማን አኒሜሽንስ፣ የሾን ዘ ሺፕ እና የቲሚ ታይም አዘጋጆች ናቸው።

ይህን ያውርዱ (Download)፦ iOS | Android (ጉግል ፕሌይ) | Android (አማዞን)

Learning Time with Timmy 2

ለርኒንግ ታይም ዊዝ ቲሚ 2

በዚህ አዝናኝ የኮምፒውተር ፕሮግራም አማካኝነት የልጆች የቋንቋ፣ የመረዳትና የማሰብ ችሎታ በፍጥነት እንዲያድግ ያድርጉ። የኮምፒውተር ጨዋታዎች ልጆች ቃላትን እንዲማሩና እንዲጠሩ እንዲሁም ቃላትን አሳክተው ቀላል ሐረጎችን እንዲመሠርቱ ይረዳቸዋል። በተከታታይ ከሚወጡ የቲሚ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ውስጥ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ቲሚ ታይም ልጆች በጣም የሚወዱት ተከታታይ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ነው።

ይህን ያውርዱ (Download)፦iOS | Android (ጉግል ፕሌይ) | Android (አማዞን)

Learning Time with Timmy 3

ለርኒንግ ታይም ዊዝ ቲሚ 3

በዚህ ፕሮግራም አማካኝነት ልጆች ከ60 በላይ አዳዲስ የእንግሊዝኛ ቃላትን ይማራሉ፣ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ‘Learning Time with Timmy’ ፕሮግራሞች ላይ የተማሯቸውን ቃላት ይከልሳሉ እንዲሁም ትኩረትን ሰብስቦ የመማርና የማስታወስ ችሎታቸውን ያሳድጋሉ። ሕፃናት ከቲሚና ከጓደኞቹ ጋር ሦስት አዝናኝ ጨዋታዎችን መጫወት የሚችሉ ከመሆኑም ሌላ በተከታታይ ከሚወጡት ከቲሚ ጋር የመማሪያ ጊዜ ፕሮግራሞች መካከል የመጀመሪያውን የማንበብ ጨዋታ ይጫወታሉ።

ይህን ያውርዱ (Download)፦iOS | Android (ጉግል ፕሌይ) | Android (አማዞን)

 

LearnEnglish GREAT videos

ምርጥ በሆኑ ቪዲዮዎች እንግሊዝኛ መማር

ስለ እንግሊዝ ባሕል የሚናገሩ 24 አጫጭር ቪዲዮዎች በማየት እንግሊዝኛ የማዳመጥ ችሎታዎን ያሻሽሉ። ስለ እንግሊዝኛ ቋንቋ አመጣጥ ይማሩ፤ የለንደን ቤተ መዘክሮችንና ሌሎች በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚገኙ የታወቁ ቦታዎችን ይጎብኙ።

ይህን ያውርዱ (Download)፦iOS | Android