Study in the UK

በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጅ፣ ትምህርት ቤት ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማዕከል ትምህርትዎን መከታተል ይፈልጋሉ?

በዩናይትድ ኪንግደም ቢማሩ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት፣ በመላው ዓለም ተቀባይነት ያላቸው የብቃት ማረጋገጫዎች እና ግሩም የሆኑ የሥራ እድሎች ያገኛሉ።

ኤጁኬሽን ዩኬ ድረ ገጽ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ በዩናይትድ ኪንግደም የሚሰጡ የነፃ ትምህርት እድሎችና የትምህርት ዓይነቶች ተዘርዝረዋል። 

ከዚህ በተጨማሪ የሚፈልጉትን የትምህርት ዓይነት ከመምረጥና የጉዞ እቅድ ከማውጣት ጀምሮ፣ ወዳጆች እስከ ማፍራትና ከዩናይትድ ኪንግደም የአየር ጸባይ ጋር እስከ መላመድ ድረስ ያሉትን ጉዳዮች ያካትታል።

የዩናይትድ ኪንግደም ትምህርት ለምን ይመረጣል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

  • በዓለም ላይ ካሉት ስድስት ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አራቱ የሚገኙት በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ነው። (ዎርልድ ራንኪንግስ፣ ኪውኤስ)
  • ዩናይትድ ኪንግደም ጥናታዊ ምርምሮችን በማድረግ ረገድ በዓለም ላይ ቁጥር አንድ አገር ናት። (ኢንተርናሽናል ኮምፓራቲቭ ፐርፎርማንስ ኦፍ ዘ ዩኬ ሪሰርች ቤዝ፣ ቢአይኤስ)
  • ዩናይትድ ኪንግደም እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመማር በዓለም ላይ እጅግ ተመራጭ አገር ናት።
  • በዩኬ የተማሩ ዓለም አቀፍ ተመራቂዎች፣ አገራቸው ውስጥ ከተማሩት አንጻር ሲታይ አማካይ ደሞዛቸው በጣም ከፍ ያለ ነው። (ትራኪንግ ኢንተርናሽናል ግራጅዌት አውትካምስ፣ ቢ አይ ኤስ፣ 2011)

የዩናይትድ ኪንግደም ትምህርት ትኩረት የሚያደርገው ያለዎትን እውቀትና ክህሎት የማሳደግ ጉጉት እንዲያድርብዎት፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመፍጠር ነፃነት እንዲሰማዎትና ከፍተኛ ውጤት እንዲያገኙ የሚያስፈልግዎትን ድጋፍ መስጠት ላይ ነው።

በዩናይትድ ኪንግደም የሚማሩት የትምህርት ዓይነት በመረጡት ሙያ ስኬታማ እንዲሆኑ የሚረዳዎትን ችሎታና ብቃት ያስገኝልዎታል።

ከመማሪያ ክፍል ውስጥ ሲወጡ ደግሞ በዓይነታቸው ልዩ የሆኑትን የዩናይትድ ኪንግደም ገጠሮች፣ ከተሞችና ባሕሎች የማየት አጋጣሚ ይኖርዎታል!

ሪዝንስ ቱ ቹዝ ኤ ዩኬ ኤጁኬሽንስ በሚለው ሊንክ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በዩናይትድ ኪንግደም ለመማር የሚያስችሉ አማራጮች

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት ወይም የነፃ ትምህርት እድል ማግኘት ይፈልጋሉ? ምን አይነት ትምህርት እና የት ልማር የሚል ውሳኔ ለማድረግ እርዳታ ማግኘት ይፈልጉ ይሆን። እርስዎን ለመርዳት ዝግጁ ነን።

ያዘጋጀናቸውን የመፈለጊያ ዘዴዎችና መርጃዎች ተጠቅመው ኤጁኬሽን ዩኬ ድረ ገጽ ላይ የሚገኙትን በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትምህርት ዓይነቶችንና የነፃ ትምህርት እድሎችን ማግኘት ይችላሉ። እዚያ ላይ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች፣ ለምሳሌ የመጀመሪያ ደረጃ ዲግሪዎች፣ ኤችኤንዲዎችና የሁለተኛ ዲግሪዎች፣ ኤምቢኤዎችና ዶክትሬቶች ተዘርዝረዋል። ከዚህም ሌላ የምንሰጣቸውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኮርሶች በተመለከተ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ለወጣት ተማሪዎች ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም ካሉት አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ለልጆችና ለወጣቶች ከተዘጋጁት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርቶች መካከል የሚፈልጉትን መምረጥ ይችላሉ።

ዩር ስተዲ ኦፕሽንስ በሚለው ሊንክ ላይ በእንግሊዝ፣ በሰሜን አየርላንድ፣ በስኮትላንድና በዌልስ ስለሚሰጡት የትምህርት ዓይነቶች፣ የብቃት ማረጋገጫዎችና ስላሉት የተለያዩ ሥርዓተ ትምህርቶች መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በዩናይትድ ኪንግደም ለመማር ከመሄድዎ በፊት ጠቃሚ ምክሮች

በዩናይትድ ኪንግደም ለመማር እቅድ እያወጡ ከሆነ ልንረዳዎት ዝግጁ ነን! የዩናይትድ ኪንግደም ቪዛዎችን፣ ነፃ የትምህርት እድሎችን፣ ገንዘብን፣ ማረፊያን፣ ጤናን፣ ደኅንነትን፣ ጉዞንና ሌሎች በርካታ ነገሮችን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች አሰባስበናል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በኤጁኬሽን ዩኬ ድረ ገጽ ላይ የሚገኘውን ፕራክቲካል አድቫይዝ ቢፎር ዩ ጎ ሊንክ ያንብቡ።

በዩናይትድ ኪንግደም መማርና መኖር

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መኖርና መማር በእርግጥ ምን ይመስላል?

ከተማሪዎች ማኅበራት፣ ከምሽት መዝናኛዎችና ከማኅበራዊ ሕይወት ጀምሮ ምግብን፣ መጠጥን፣ ሃይማኖትን እና የአየር ጸባይ እስከሚመለከት መረጃ ድረስ ለማግኘት በኤጁኬሽን ዩኬ ድረ ገጽ ላይ የሚገኘውን ሊቪንግ ኤንድ ስተዲዪንግ ኢን ዘ ዩኬ የሚለው ሊንክ ይጠቀሙ። 

በተጨማሪም የተለያዩ ፊልሞችን ማየትና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተማሪዎች ኢንተርኔት ላይ የጻፏቸውን ማስታወሻዎች ማንበብ ይችላሉ።

ይህን ደግሞ ይመልከቱ

ውጫዊ ማያዣዣዎች