British Council office
ስለ ብሪትሽ ካውንስል ኢትዮጵያ

በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኘው ቢሯችን እ.ኤ.አ. በ 1943 ተመሰረተ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ትምህርታዊ እና ባህላዊ ፕሮግራሞች ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑ ወጣቶች ጋር ተገናኝተናል።

በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ አጋሮቻችን ጋር በመሆን በጥራት፣ በዘመናዊነት እና በፈጠራ ሥራ ረገድ ምሳሌ የሚሆኑ ሥራዎችን አከናውነናል። ለሁለቱም አገሮች የተናጠል እና የጋራ ጥቅም የሚያመጡ ነገሮችን እንሠራለን።

ከዩናይትድ ኪንግደም ምርጥ ተሞክሮ እንዲያገኙ ሊረዱዎት የሚችሉ በእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ በትምህርት፣ በሥነ ማህበረሰብ እና በሥነ ጥበብ ሙያዎች የተዋጣላቸው ታታሪ ሠራተኞች አሉን። በአዲስ አበባ በሚገኘው ብሪትሽ ካውንስል እርስዎን ለማገልገል የተዘጋጀ 80 ባለሙያዎችን ያቀፈ ቡድን አለን።

ይህን ደግሞ ይመልከቱ