ግባችን በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሕዝቦች መካከል የመተማመንና የመግባባት ድልድይ መገንባት ነው። በፕሮግራሞቻችን አማካኝነት በመላው ዓለም የሚገኙ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ ብሪታኒያ ባሕልና የፈጠራ ሃሳቦች የማወቅ አጋጣሚ እንዲያገኙ እናደርጋለን።
በሥነ ጥበብ ዙሪያ የምናከናውነው ሥራ
በኢትዮጵያ፣ በዩናይትድ ኪንግደምና በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የሥነ ጥበብ ባለሙያዎችና ከሥራ ፈጣሪዎች ጋር በአጋርነት የምንሠራባቸውን አዳዲስ መስኮች ለመመሥረት ጥረት እናደርጋለን።