ፎቶ:- አላ ኬይር
በዓለም አንቱ የተባልን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች እንደመሆናችን መጠን ለእንግሊዝኛ ቋንቋ አድናቆት ያለን መሆኑ ምንም አያስገርምም። እንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ ሰዎችንም እንዲሁ እናደንቃለን።
በምንሰጣቸው ኮርሶች፣ ሙያዊ ምክሮች፣ የማስተማሪያ መሣሪያዎች እና በግንኙነት መረቦቻችን በምንሰጠው ድጋፍ አማካኝነት ይበልጥ ውጤታማ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪ እንዲሆኑ ልንረዳዎት ዝግጁ ነን። ስለሆነም አዲስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪም ሆኑ ወደ ሌላ የሥራ እና የእድገት ምእራፍ እየተሸጋገሩ ያሉ ግለሰብ፣ ዋጋ የማይተመንለት ድጋፍ እና አጋጣሚ እኛ ዘንድ ያገኛሉ። ከዚህ በታች ያሉት ሊንኮች ለአስተማሪዎች ስለተዘጋጁት ድጋፍ መስጫ ፕሮግራሞች ጠቃሚ መረጃ ይዘዋል።