ይህ ክፍል ሁሉንም የብሪትሽ ካውንስል ድረ ገጾች አጠቃቀም በተመለከተ መረጃ የያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ ድርጅቱ የሚመራባቸውን ደንቦች ይዘረዝራል።
ይህ ክፍል ስለሚከተሉት ጉዳዮች መረጃ ይዟል፦
- የግል መረጃ፣ ኩኪዎችን እና ሰነድን የመጠበቅ እንዲሁም መረጃ የማግኘት ነፃነት፣
- ስለ ሁሉም የብሪቲሽ ካውንስል ድረ ገጾች አጠቃቀም ደንብ፣ ስለ ተደራሽነታቸው እና እንዴት አቤቱታ ማቅረብ እንደሚቻል የሚገልጽ መረጃ፣
- ብሪቲሽ ካውንስል የሚመራባቸውን ደንቦች ዝርዝር።
ይህ መረጃ በየጊዜው ማሻሻያ ይደረግበታል። ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው እ. ኤ. አ. ታኅሣሥ 22 ቀን 2014 ነው።
የግል መረጃ ጥበቃ እና ኩኪዎች
የግል መረጃ ጥበቃ
የሌሎች ሰዎች የግል መረጃዎች ሕጋዊና ትክክለኛ በሆነ መንገድ መያዛቸው፣ ሥራችንን በተሳካ መንገድ ለማከናወንና ከእኛ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የመተማመን ስሜታቸውን ይዘው እንዲቀጥሉ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን። በመሆኑም በየትኛውም ቦታ በሚገኙ ቢሮዎቻችን ይህ መመሪያ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።
የግል መረጃ ጥበቃን በሚመለከት የድርጅታችንንሙሉ መመሪያ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full Policy on Privacy (English Version)
ሰነድን ስለመጠበቅ
ለእርስዎ መረጃ እንዴት ጥበቃ እንደምናደርግና እኛ ዘንድ የሚገኘውን መረጃዎትን ለማግኘት ጥያቄ የሚያቀርቡት እንዴት እንደሆነ ይመልከቱ።
ሰነድ አጠባበቅን የሚመለከት የድርጅታችንንሙሉ መመሪያ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full policy on data protection (English Version)
መረጃ የማግኘት ነፃነት
ብሪቲሽ ካውንስል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር የሚገናኝባቸውን አዳዲስና ክፍት የሆኑ መንገዶች የሚያፈላልግ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል። ሐቀኝነትን እና የመተማመን ስሜትን መገንባት እንዲቻል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ድርጅታችንን ለዓለም ክፍት በማድረግ ረገድ ፈር ቀዳጅ ሆነን መገኘታችን አስፈላጊ ነው።
መረጃ የማግኘት ነፃነትን የሚመለከት የድርጅታችንንሙሉ መመሪያ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full policy on freedom of information (English Version)
የዚህን ድረ ገጽ አጠቃቀም በተመለተከ የወጡ ደንቦች
ብሪቲሽ ካውንስል ይህን ድረ ገጽ መጠቀም የሚችሉበትን መንገድ በተመለከተ ዝርዝር መመሪያዎች አውጥቷል። ይህን ድረ ገጽ እንዴት ሁሉም ሰው በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ተደርጎ እንደተዘጋጀ የሚገልጽ አስፈላጊ መረጃ በመመሪያው ላይ ያገኛሉ። በተጨማሪም ቅሬታዎትን እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የአጠቃቀም ደንብ
ብሪቲሽ ካውንስል ይህን ድረ ገጽ እንዲሁም ይህንን እና ሌሎች ድረ ገጾችን የሚያገናኙ ሊንኮችን አጠቃቀም የሚመለከቱ ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች አሉት።
ደንቦችን እና ቅድመ ሁኔታዎችን የሚመለከቱ የድርጅታችንንሙሉ መመሪያዎች በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full terms and conditions (English Version)
ተደራሽነት
ድረ ገጹን ለማግኘት ጥቅም ላይ የዋለው መፈለጊያ ምንም ቢሆን እና ወደ ድረ ገጹ ለመግባት ልዩ መሣሪያ ጥቅም ላይ ዋለም አልዋለም፣ ማንኛውም ሰው ወደ http://ethiopia.britishcouncil.org/ በቀላሉ መግባት እንዲችል የሚቻለውን ሁሉ አድርገናል።
የብሪቲሽ ካውንስል ድረ ገጽ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የተወሰዱትን እርምጃዎች በሚመለከት በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። accessibility measures (English Version)
ቅሬታ ማሰማት
እርስዎ ለሚሰጡን አስተያየት ትልቅ ግምት እንሰጣለን። ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር ያለዎት ግንኙነት በጣም አስደሳች እንዲሆን ምኞት አለን፤ በተጨማሪም ከእኛ ጋር በተገናኙበት ወቅት እንዲሁም በምናቀርባቸው መጠቀሚያዎችና በአገልግሎታችን ሲጠቀሙ የተሰማዎትን እርካታ ወይም ያዩትን ጉድለት በተመለከተ የሚሰጡትን ሐሳብና አስተያየት በዝርዝር መስማት ያስደስተናል። ከዚህ በተጨማሪ አንድ የድርጅታችን ባልደረባ ለየት ያለ አገልግሎት ሰጥቶዎት ከሆነ ይህን መስማት እንፈልጋለን።
ቅሬታ ማሰማትን የሚመለከት የድርጅታችንንሙሉ መመሪያ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full policy on making a complaint (English Version)
ደንቦች
ብሪቲሽ ካውንስል ለባሕላዊ ግንኙነቶች ትኩረት የሚሰጥ ድርጅት በመሆኑ የሚመራባቸው ደንቦች አሉ፦
ለሕፃናት ጥበቃ የማድረግ መመሪያ
ብሪቲሽ ካውንስል እኛ ጋ ለሚማሩ ልጆች በሙሉ እንክብካቤ የማድረግ ከባድ ኃላፊነት ብሎም ከጥቃት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለብን ይገነዘባል። ይህን የምናሳካው ከዩናይትድ ኪንግደም የሕፃናት ጥበቃ ሕግና በምንሠራባቸው በእያንዳንዳቸው አገሮች ካሉ ተዛማጅ ሕጎች ጋር ተስማምተን በመሥራት እንዲሁም እ. ኤ. አ. በ1989 የወጣውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መብቶች ድንጋጌን (UNCRC) በጥብቅ በመከተል ነው።
ለሕፃናት ጥበቃ ማድረግን የሚመለከት የድርጅታችንንሙሉ መመሪያ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full policy on child protection (English Version)
የአካባቢ ጥበቃ መመሪያ
ብሪቲሽ ካውንስል በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቆጣጠር የዩናይትድ ኪንግደምም ሆነ ዓለም አቀፋዊ መሥፈርቶችን ለመጠበቅ ቁርጥ አቋም አለው። የምናከናውነው ሥራና እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ እንገነዘባለን። ከዚህ በተጨማሪ የአየር ባሕርይ ለውጥ በሀብት፣ በማኅበራዊ ፍትህና በሰዎች አኗኗር ላይ የሚፈጥረውን ስጋት እንገነዘባለን። በመሆኑም በአካባቢ ላይ የምናደርሰውን ተጽእኖ ለመቆጣጠርና ለመቀነስ ቁርጥ አቋም አለን።
የአካባቢ ጥበቃን የሚመለከት የድርጅታችንንሙሉ መመሪያ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full environmental policy (English Version)
እኩል ተጠቃሚነት እና ብዝሐነት
ብሪቲሽ ካውንስል ለዩናትድ ኪንግደምም ሆነ ለሌሎች አገራት ነዋሪዎች ዓለም አቀፋዊ የሆኑ አጋጣሚዎችን የሚፈጥር ከመሆኑም ሌላ በመካከላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የመተማመን ስሜትን ይገነባል። ሥራችን በጣም የተለያየ አኗኗርና ባሕል ካላቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት መመሥረትን ያካትታል። በመሆኑም ከብዝሐነት ጋር በተያያዘ ውጤታማ ሥራ ማከናወን እና ሁሉም እኩል አጋጣሚ እንዲያገኝ ማድረግ የሥራችን ዓቢይ ክፍል ነው።
ፕሮግራሞቻችን እና ፕሮጀክቶቻችን ተደራሽነትንና ብዝሐነትን እንዲያካትቱ የምናደርገው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማንን ማነጋገር እንዳለብዎት ለማወቅ በዚህ ድረገጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማንበብ ይችላሉ። full policy (English Version)