Learn English student
እንግሊዝኛ ይማሩ ©

ማት ራይት

በተለያየ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን የማስተማር የበርካታ አሥርተ ዓመታት ልምድ ስላለን ወደ ብሪቲሽ ካውንስል ከመጡ መጠነ ሰፊ እውቀት እናጎናጽፎታለን።

ከ75 ዓመታት በላይ እንግሊዝኛ ቋንቋ ስናስተምር ቆይተናል፤ ከ100 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የእንግሊዝኛ ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉና የመናገር ድፍረት እንዲያዳብሩ ረድተናል።

በቋንቋ ትምህርት ቤቶቻችን በአካል ተገኝተው አሊያም ደግሞ ቤትዎ ሆነው ኢንተርኔት ላይ በምናቀርባቸው ኮርሶችና መማሪያዎች አማካኝነት እንግሊዝኛ ቋንቋ መማር ይችላሉ። ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የብቃት መመዘኛ ፈተናዎችን በመስጠት ያደረጉትን እድገት እና ለውጥ ማወቅ እንዲችሉ እንረዳዎታለን። 

የመማር ፍላጎትዎን በትክክል በማሳካት ረገድ አቻ የማይገኝላቸውን ዘርፈ ብዙ ኮርሶችና ድጋፍ የሚያገኙባቸውን ዝግጅቶች ይመልከቱ። 

እንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር።  የማስተማር ሂደቱን መደገፍ።   የብቃት መመዘኛ ፈተና መስጠት።

ለእርስዎ የሚሆን

Interior of teaching centre

የአዲስ አበባ የቋንቋ ትምህርት ቤት

የመማር ማስተማር ሂደት ስኬታማ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መሟላት ይኖርበታል። እኛ ደግሞ በማስተማር ሂደት የተዋጣልን ባለሙያዎች ስለሆንን በአዲስ አበባ የሚገኘው የቋንቋ ትምህርት ቤታችን አስተማሪዎች ለማስተማር፣ ተማሪዎች ደግሞ ለመማር እንዲመቻቸው ታስቦ የተዘጋጀ ማዕከል ነው።