የእኩልነት፣ የብዝሀነት እና የማካተት አካሄዳችን

በብሪቲሽ ካውንስል፣ ዓላማችን በድርጅታችን ውስጥ ያሉትን መሰናክሎችን ለማስወገድ እና አካታች እና ወካይ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመገንባት ነው። አላማችን ብዝሀነትን መቀበል፣ዘረኝነትን እና ሁሉንም አይነት አድሎን መቃወም እና እኩልነትን የድርጅቱ ማእከል ማድረግ ነው። 

ዕድሜን፣ አካል ጉዳተኝነትን፣ ጾታን፣ ሃይማኖትን፣ እምነትን፣ ዘርን፣ ብሔርን፣ ባህልን እና ጾታዊ ዝንባሌን የማይለይ አካታች ድርጅታዊ ባህልን እናበረታታለን፣ እናም ለስራ ባልደረቦቻችን፣ ለተማሪዎቻችን እና ለምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ አቅማቸውን እንዲያሳኩ እድል መስጠት እንፈልጋለን።

የአስተማሪ ቡድኖቻች ብዝሀነት

በዓለም ዙሪያ ያሉ ሁሉም የብሪቲሽ ካውንስል የማስተማሪያ ማዕከላት የተለያየ የአስተማሪ ቡድን እንዲኖራቸው ለማድረግ ቁርጠኛ ናቸው። መምህራኖቻችን የተለያየ የኋላ ታሪክ ፣ ማንነት፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሃይማኖቶች ያላቸው ናቸው። የብሪቲሽ ካውንስል መምህራኖች እጅግ በጣም ጥሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ደረጃ ያላቸው ሲሆኑ ሁሉም ከፍተኛውን የእንግሊዝኛ መደብ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ለተማሪዎቻችን የማቅረብ የጋራ ግብ አላቸው። 

ብዝሀነት፣ አካታችነት እና እኩል እድሎች ለተማሪዎቻችን

ተማሪዎቻችን ብዙና የተለያዩ ፍላጎቶች አሏቸው። በብዝሃነት በብቃት መስራት በብሪትሽ ካውንስል የስራ ሂደት አስፈላጊ አካል ነው፣ እናም ይህ ማለት ለሁሉም ተማሪዎቻችን የተለያዩ ፍላጎቶች አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ማለት ነው። ሁሉም ተማሪዎች የግል ስኬትን ከፍ የሚያደርግ ከፍተኛ ጥራት ያለው የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመማር ልምድ ይገባቸዋል ብለን እናምናለን።

ለእኩልነት፣ ለብዝሀነት እና ለአካታችነት ያለን ቁርጠኝነት 

እንደ አለም አቀፋዊ የባህል ድርጅት ፣ ሰዎችን አንድ ላይ ለማገናኘት፣ አለምአቀፋዊ ግንኙነቶችን ለመመስረት እና ደህንነቱን በጠበቀ፣ በታማኝነት እና በሚጋብዝ ሁሄታ የሀሳቦችን ልውውጥ ለመደገፍ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅተናል። የእኛ ስራ በተለያዩ ባህሎች ውስጥ ትርጉም ያለው፣ ዘላቂ እና አክብሮት የተሞላበት ግንኙነትን በመገንባት ላይ የተመሰረተ ነው። የሥራ ባልደረቦቻችን እና ተማሪዎቻችን ጨምሮ አብረውን በሚሰሩት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት አድልዎ እና ዘረኝነት አጥብቀን እንቃወማለን።

ለእኩልነት፣ ለብዝሀነት እና ለአካታችነት ያለን ቁርጠኝነት ከፍተኛ ነው። አድልዎን እንቃወማለን እና በሁሉም ፍትሃዊ አያያዝ ላይ እናተኩራለን።