Learn English student
በብሪቲሽ ካውንስል መማር ምን ጥቅም አለው? ©

Credit Ala Kheir

እጅግ በጣም ውጤታማ እና አስደሳች በሆነ መንገድ የእንግሊዝኛ ቋንቋን እኛ ጋር መጥተው በመማር ፈጣን ለውጥ ያድርጉ። ባካበትነው የ75 ዓመታት ልምድ፣ በምንጠቀምባቸው እጅግ ዘመናዊ የማስተማሪያ ዘዴዎች እና ላቅ ያለ ብቃት ባላቸው አስተማሪዎቻችን እየታገዝን በቋንቋ ረገድ መድረስ ወደሚፈልጉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ልንረዳዎት እንችላለን።

እያንዳንዱ ኮርስ የተዘጋጀው አሳታፊ እና ተማሪዎች ሃሳባቸውን እንዲገልፁ በሚያበረታቱ እጅግ ወቅታዊ በሆኑ የማስተማሪያ ዘዴዎች ነው። ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ ተደርጎ የተዘጋጁት ትምህርቶች ያለዎትን የመናገር ድፍረት፣ ችሎታ እና ተነሳሽነት ያሻሽሉልዎታል።

ግባችን፣ እንግሊዝኛን ደስ ብሎዎት እንዲማሩ እና ቋንቋውን በገሃዱ ዓለም ላይ በፍጥነት መጠቀም እንዲጀምሩ ማበረታታት ነው።