Teacher and students
ለማስተማርእናሥልጠናለመስጠትየምንጠቀምባቸውዘዴዎች

ቀልብ የሚስቡ፣ አሳታፊና ተማሪዎች ሃሳባቸውን እንዲገልፁ የሚያበረታቱ የማስተማር ዘዴዎች በትምህርት ክፍሎቻችን ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ይህ ዘዴ በዛሬው ጊዜ ተማሪዎቻችን ከዓለም ጋር በተሳካ ሁኔታ በእንግሊዝኛ መግባባት እንዲችሉ ለማዘጋጀት የሚረዳ ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ከተሞክሯችን ተገንዝበናል።

ተማሪዎቻችን የሚፈልጉት የእውቀት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ፣ አስተማሪዎቻችን እጅግ ዘመናዊ በሆኑ የማስተማሪያ መሳሪያዎችና በመጠቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ ውጤታማነታቸው በተረጋገጠ ልዩ ልዩ የማስተማሪያ ዘዴዎች ይጠቀማሉ።

አስተማሪዎቻችን ሁሉም ተማሪዎች በግለሰብ ደረጃ የሚያስፈልጋቸውን ትኩረት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ ጠንክረው ይሠራሉ። ተማሪዎች መሻሻል ማድረጋቸውም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ አስተማሪዎች ተማሪዎቹ ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለእያንዳንዳቸው አዘውትረው ሃሳብ ይሰጧቸዋል።

የሚወስዷቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኮርሶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች ማሟላት እንዳለባቸው እናምናለን፦

  • ሕይወትዎ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱዎት መሆን እንዳለባቸው፣
  • የሚያነቃቁ፣ ጠንከር ያሉና አስደሳች መሆን እንዳለባቸው፣
  • ከሌሎች ተማሪዎች እና ሰዎች ጋር ወዳጅነት እንዲመሰርቱ የሚያስችሉዎት መሆን እንዳለባቸው።

ከዚህ በተጨማሪ አስተማሪዎች የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት እንዳለባቸው እናምናለን፦

  • ጥሩ እውቀት ያላቸው፣ ተግባቢና ለመርዳት ፈቃደኞች መሆን እንዳለባቸው፣
  • ትምህርቱን ከተማሪዎች ፍላጎት ጋር አጣጥሞ ማቅረብ እንዳለባቸው፣
  • ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ መማርዎትን እንዲቀጥሉ የማጥኛ ዘዴዎችን ሊያስተምሩዎት እንደሚገባ።