Corporate English Solutions

ከንግድ ፣ከመንግስት እና የትምህርት ተቋማት ጋር ከ80 ዓመታት በላይ በመስራት ተግባራዊ እና አሳታፊ ስልጠናዎችን እና ግምገማዎችን መስጠት

 

ድርጅቶች ለስኬት እንዲሰለጥኑ መርዳት

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ኮርሶችን፣ ሙያዊ የግንኙነት ክህሎት ፕሮግራሞችን እና ግምገማዎችን ለመፍጠር እና ለማቅረብ ከአንዳንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሆኑ ድርጅቶች ጋር እንሰራለን። የኛን በስፋት ሊሰጡ ሰፋ የሚችሉ የሥልጠና መፍትሔዎች በገጽ ለገጽ ወይም በበየይነ መረብ በብቁ ባለሙያዎች ይቀርባሉ።

የእኛ ኮርሶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች እና የስራ ደረጃዎች ላይ ላሉ ባለሙያዎች እንዲሁም ተማሪዎች፣ የቅርብ ተመራቂዎች፣ አስተማሪዎች እና ከፍተኛ አመራሮች ተስማሚ ናቸው።

ድርጅታዊ ግቦችዎን በመረዳት የክህሎት ክፍተቶችዎን ለመለየት እና ለጊዜ ሰሌዳዎ፣ በጀትዎ እና የግዥ ሂደቶችዎ የሚስማማ የትምህርት ፕሮግራም ለመንደፍ ከእርስዎ ጋር እንሰራለን።

ለእርስዎ የተበጁ ፕሮግራም ይፍጠሩ

ደረጃ 1 - ምክክር፦ ለድርጅትዎ የክህሎት ክፍተቶችን እና የመማር ግቦችን ለመለየት ከእኛ ጋር ይስሩ። ምክክርዎ ከተቻለ በእንግሊዝኛ አለዚያም በመረጡት ቋንቋ ይሆናል።

ደረጃ 2 - ንድፍ፦ ለሠራተኞቻችሁ ተዛማጅ፣ መሳጭ፣ ሊሰፉ የሚችሉ፣ እና እንደ ደረጃቸው የተበጁ የትምህርት ፕሮግራሞችን እንፈጥራለን።

ደረጃ 3 - መተግበር፦ ልምድ ያካበቱ አሰልጣኞቻችን ኮርስዎን በሚፈልጉት ጊዜ እና እርስዎ በሚፈልጉበት መንገድ (ገጽ ለገጽ፣ በበይነ መረብ ወይም በሁለቱም ድብልቅ ) ያቀርባሉ።

ደረጃ 4 - ግምገማ፡- ዳሽቦርድ እና ሪፖርቶች በመጠቀም ስለ ሰራተኛ እድገት፣ የስልጠና ተፅእኖ እና ROI ሪፖርት እንዲያደርጉ እንረዳዎታለን።

ነፃ ምክክር በቅድሚያ ያስይዙ

የእኛ የእንግሊዝኛ እና ሙያዊ ክህሎቶች ስልጠና ኮርሶች

የሚታይ ስኬት እና በስራ ቦታ ላይ የባህሪ ለውጥ ለማየት በአለም ዙሪያ ያሉትን ከ 80 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ይቀላቀሉ። እንደ ደረጃዎ የተቀረጹ ኮርሶቻችን የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ገጽ ለገጽ፣ በበይነ መረብ ወይም በሁለቱም/ድብልቅ የማድረስ አማራጮች
  • ከሥራ ቦታ ጋር የሚዛመዱ ልዩ ክህሎቶች ላይ የሚያተኩር ስልጠና
  • የስልጠና ተፅእኖ እና ROI ለመከታተል የሚረዱ ዘዴዎችን ያካተተ።

የእኛ የስልጠና መፍትሔዎች፦

  • ሙያዊ የመግባቢያ የክህሎቶች ስልጠና፦ የንግግር እና የጽሁፍ ግንኙነት ክህሎቶችን በማሻሻል ላይ የሚያተኩሩ የተለያዩ ኮርሶችን እናቀርባለን። የእርስዎን ድርጅታዊ ፍላጎቶች የሚያሟላ እና ምርታማነትን ከፍ እንዲያደርግ የታለመ የመማሪያ ፕሮግራም ለመፍጠር ከእርስዎ ጋር እንሰራለን።
  • እንግሊዘኛ በበይነ መረብ፦ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች፣ በአለም ውስጥ በማንኛውም ቦታ በቀን 24 ሰአት፣ በሳምንት 7 ቀን ከሚገኙ፣ በግል-ጥናት እና ከቀጥታ የበይነ መረብ ላይ ትምህርቶች አንዱን መምረጥ ይችላሉ።
  • እንግሊዝኛ በአካል፦ በብጁ እና በመሳጭ በሆኑ ኮርሶቻን በመካተት በቡድንዎ ውስጥ በራስ መተማመንን እና ችሎታን ይገንቡ። ኮርስዎ ለእርስዎ በሚመች ጊዜ በእኛ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ በቢሮዎ ወይም በመረጡት ቦታ ሊሰጥ ይችላል። የሰራተኞችዎን የእንግሊዘኛ ብቃት ለመገምገም እና ለእነርሱ የሚስማማ የመማሪያ መንገዶችን ለመፍጠር ከእርስዎ ጋር እንሰራለን።

ስለ እኛ የእንግሊዝኛ እና የሙያዊ ግንኙነት ክህሎቶች ኮርሶች (በእንግሊዝኛ) ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።

ፈተናዎች እና ግምገማዎች

ሊሰፉ በሚችሉ፣ በቴክኖሎጂ በታገዙ ፈተናዎች እና ግምገማዎች ደንበኞቻችን ትክክለኛውን ሰራተኛ እንዲቀጠሩ እና የይዘወው እንዲያስቀሩ እንረዳቸዋለን፣ ተማሪዎች በአለም ዙሪያ ባሉ የትምህርት ተቋማት እንዲገቡ  እና የንግድ ድርጅቶች  የስልጠና ነክ ውሳኔዎች እና ውጤቱንም እንዲለኩ እናግዛለን።

ስለ እንግሊዝኛ እና ሙያዊ የግንኙነት ችሎታ ኮርሶች (በእንግሊዝኛ) ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።