Photo: Ala Kheir
ኢንተርኔት ላይ መርጠን ያወጣናቸውን በነፃ ማግኘት የሚችሏቸውን የብሪቲሽ ካውንስል እንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያዎች ይመልከቱ።
በተለያየ መንገድ እንግሊዝኛ ቋንቋ ይማሩ
ብሪቲሽ ካውንስል ለአዋቂ ተማሪዎች ባዘጋጀው ድረ ገጽ አማካኝነት በነፃ እንግሊዝኛ ቋንቋ በኢንተርኔት መማር ይችላሉ። ድረ ገጹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ገጾች ያሉት ሲሆን በድምፅ፣ በጽሑፍ፣ በቪዲዮ የተዘጋጁ መማሪያዎችን እንዲሁም ከ2,000 በላይ አሳታፊ የሆኑ መልመጃዎችን ይዟል። አባል መሆን የሚችሉ ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ነገሮችን ለድረ ገጹ ማበርከት፣ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር ሐሳብ መለዋወጥ እንዲሁም ክፍያ የማይጠየቅባቸው መረጃዎችን ማውረድ ይችላሉ።
በቀላሉ እና በሚያዝናና መልኩ እንግሊዝኛ ይማሩ
በጨዋታዎችና በቀልዶች እየተዝናኑ እንግሊዝኛ መማር ይችላሉ። እንግሊዝኛ መለማመድ እንዲችሉ የሚረዱዎትን ወይም ለመዝናናት ያህል ብቻ የተለያዩ ዓይነት ጨዋታዎችን ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም መጫወት፣ መደሰትና መማር የሚያስችሉዎት በስዕል የቀረቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቀልዶች አሉ።
እንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ድረገጽ - መዝናኛ እና ጨዋታዎች
በድምፅና በቪዲዮ እንግሊዝኛ ይማሩ
ቋንቋ መለማመድ የሚያስችሉ በድምፅና በቪዲዮ የተዘጋጁ እጅግ በርካታ መማሪዎች አሉን። መማሪያዎቹ የሚከተሉትን ያካተቱ ናቸው፦ የፖድካስት ታሪኮች፣ በድምፅ የሚቀርብ ተከታታይ ታሪክ፣ ከቢቢሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀናቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ተከታታይ የቲቪ ፕሮግራሞች እንዲሁም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሐሳብን እንዴት በትክክል መግለጽ እንደሚቻል የሚያሳዩ ቪዲዮዎች።
እንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ድረገጽ፦ መስማት እና ማየት
እንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ለልጆች
እንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ለልጆች የተባለው ፕሮግራም፣ ዕድሜያቸው ከ5-12 ዓመት ለሆኑ ልጆች የተዘጋጀ አዝናኝና አስተማሪ ድረ ገጽ ነው። የማንበብና የመጻፍ ችሎታን በማዳበር ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የቃላትና የሰዋስው ጨዋታዎች፣ መዝሙሮች፣ ታሪኮች፣ ቪዲዮዎችና የተለያዩ ሥራዎች ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ። የልጆች እንግሊዝኛ መማሪያ ለአስተማሪዎችና ለወላጆች የተዘጋጀ ሲሆን በነፃ ሊታተሙ የሚችሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ መሣሪያዎችን እንዲሁም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ሳይልኩ እንግሊዝኛ ማስተማር የሚፈልጉ ወላጆችን ለመርዳት የተዘጋጀ ክፍል ይዟል።
የወጣቶች እንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ
እንግሊዝኛ በመማር ላይ ያለህ እና ከ18 አመት በታች ባለ ዕድሜ ላይ የምትገኝ ወጣት ነህ? ወይንስ እንግሊዝኛ የሚማሩ ከ18 አመት በታች ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆች አሉዎት? የወጣቶች እንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ የተባለው ድረገጽ የተዘጋጀው በተለይ ከ13 እስከ 17 ዓመት የሆናቸውን ልጆች ታሳቢ በማድረግ ነው። በዚህ ድረገጽ ላይ የቋንቋ መለማመጃዎችን፣ ለፈተናዎች የሚረዱ ምክሮችን እንዲሁም ከሰዋስውና ከቃላት ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መርጃዎችን አልፎ ተርፎም አዝናኝ ጨዋታዎች፣ ቪዲዮዎችና እንቆቅልሾችን ያገኛሉ።
እንግሊዝኛ ቋንቋ ለሥራ ቦታ
እንግሊዝኛ መናገር የሚችሉ ቢሆኑም ለሥራ የሚጠቀሙበትን እንግሊዝኛ ማሻሻል ይፈልጋሉ? ለሥራ የሚጠቀሙበት እንግሊዝኛ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ጥያቄ ተፈጥሮቦት ያውቃል? እንግሊዝኛ የሥራ ቋንቋ በሆነባቸው ዓለም አቀፍ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ መቀጠር ይፈልጋሉ? ለሥራ የሚጠቅምዎትን እንግሊዝኛ ለማሻሻል የሚረዱዎት ትክክለኛዎቹ መሣሪያዎች አሉን።
እንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ድረገጽ፦ ንግድ እና ሥራ
በኳስ ጨዋታ አማካኝነት እንግሊዝኛ መማር
እንግሊዝኛ እየተማሩ ከሆነና እግር ኳስ የሚወዱ ከሆነ ፕሪሚየር ስኪልስ ኢንግሊሽ፣ በፕሪሚየር ሊግ ስለሚሳተፉ ቡድኖችና ተጫዋቾች ያለዎትን ግንዛቤ እያሰፉ እግረ መንገዱንም እንግሊዝኛዎትን እንዲያሻሽሉ ሊረዳዎት ይችላል። ከዚህም ሌላ ስለ ግጥሚያዎችና የፕሪሚየር ሊግ ደንቦች መረጃ የሚያገኙ ከመሆኑም ሌላ ጨዋታዎችን መጫወትና ጥያቄዎችን መሥራት ይችላሉ።