University students

በአገርዎት ሆነው የሚከታተሉት የዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ትምህርት

የዩናይትድ ኪንግደም ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የማግኘት ጉጉታቸውን ለማሳካት ወደዚያ መጓዝ የሚችሉት ሁሉም ሰዎች አይደሉም። በመሆኑም እውቅ ከሆኑ የብሪታንያ ዩኒቨርሲቲዎች ያንን ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የትምህርት ማረጋገጫ ከአገርዎ ሳይወጡ እንዲያገኙ ለመርዳት እነሆ ዝግጁ ነን።

የዩኒቨርሲቲ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡበት ጊዜ አንስቶ ውጤትዎን እስከሚቀበሉበት ቀን ድረስ ሂደቱ ቀላልና ያልተወሳሰበ እንዲሆን ለጉዳዩ ትኩረት እንሰጣለን።

ፈተናው የሚሰጥበትን ቦታ ከማዘጋጀትም ሆነ በሙያው በሚገባ የሠለጠኑ ተቆጣጣሪዎችን ከመመደብ አንስቶ የሠሩት ፈተና በፈተና ቦርድ እስከሚታይበት ሂደት ድረስ ያለውን መላውን አሠራር የምንከታተለው እኛ ነን።

ከእርስዎ የሚጠበቀው ነገር ቢኖር ዝግጅትዎን አጠናቅቀው ለፈተናው ቀን በቦታው መገኘት ብቻ ነው። 

የሥራ አጋሮቻችን እነማን ናቸው?

ምርጥ በሆኑ በርካታ ተቋሞች ውስጥ ትምህርትዎን መከታተልና ኢትዮጵያ ውስጥ ፈተናዎቹን መውሰድ ይችላሉ። አብረናቸው የምንሠራው ተቋሞች የሚከተሉት ናቸው፦

ምዝገባው የሚካሄደው እንዴት ነው?

ለዩኒቨርሲቲ ፈተናዎች መመዝገብ በጣም ቀላል ነው። 

  1. በመጀመሪያ ከመረጡት የትምህርት ተቋም ጋር ይገናኙና ለፈተናው በቀጥታ እነርሱ ዘንድ ይመዝገቡ።
  2. ፈተናውን የሚፈተኑበት ቦታ በእርግጠኝነት ከታወቀ በኋላ እባክዎመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይፃፉልን፤ እንዲሁም የማመልከቻ ቅጹን መልሰው ያስረክቡን።
  3. ከፈተናው ቀን ቢያንስ ከአንድ ወር በፊት ይህን ማድረግ ይኖርብዎታል። 

ስንት ይከፈላል?

እኛ የምንጠይቀው ክፍያ የፈተና ቦርድ ለተለያዩ ወጪዎች የሚጠይቀውን ክፍያ አይጨምርም። እባክዎ ክፍያን በተመለከተ የፈተና ቦርዱን ያነጋግሩ። 

የእኛ ዋጋ ለእያንዳንዱ ፈተና 75 የእንግሊዝ ፓውንድ ወይም ከእዚህ ጋር የሚመጣጠን የኢትዮጵያ ብር ነው።

በኃላፊነት የማንጠየቅባቸው ሁኔታዎች

ብሪቲሽ ካውንስልም ሆነ የፈተና ቦርዶች የሚሰጡት አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ። በመሆኑም ከቁጥጥራችሁ በላይ በሆኑ ምክንያቶች የተነሳ ምንም ዓይነት መስተጓጎል ቢፈጠር በኃላፊነት እንደማንጠየቅ ማስገንዘብ እንወዳለን። ፈተናዎች ወይም የፈተና ውጤቶች ቢስተጓጎሉ፣ ቢሰረዙ ወይም ቢዘገዩ በተቻለ ፍጥነት ሁሉም ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ ማንኛውም ዓይነት ጥረት ይደረጋል። በዚህ ረገድ ብሪቲሽ ካውንስል የሚኖርበት ኃላፊነት የምዝገባ ክፍያውን ገንዘብ መመለስ ወይም በሌላ ጊዜ ፈተናውን በድጋሚ መስጠት ብቻ ነው።

ተጨማሪ መረጃ

ፈተናውን መፈተን እንዲችሉ እንዴት ልንረዳዎት እንደምንችል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን።