ምዝገባው የሚካሄደው እንዴት ነው? ለፈተና ለመመዝገብ ዝግጁ ነዎት? ብዙ አጋጣሚዎች እንዲከፈቱልዎት የሚያስችሉዎትን የተለያዩ ብቃቶች ለማግኘት የሚረዳዎት የመጀመሪያ እርምጃ ይህ ነው።
በዚህ ክፍል ውስጥ ለIGCSEs/International GCSEs እንዲሁም ለA- እና AS-ደረጃዎች እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል፣ የፈተና ክፍያውን እንዴት መፈጸም እንደሚቻል እንዲሁም ልዩ ዝግጅቶች እንዴት ማድረግ እንደሚቻል የቀረበውን መረጃ መመልከት ይችላሉ።
በቅደም ተከተል የቀረበውን ቀላል መመሪያ በመከተል፦
- ተማሪ ከሆኑ እንዴት መመዝገብ እንዳለብዎት፣
- የግል ተፈታኝ ከሆኑ እንዴት መመዝገብ እንዳለብዎት ማወቅ ይችላሉ።
IGCSEs ለመፈተን ሲመዘገቡ ልዩ ዝግጅት እንዲደረግልዎት የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን ከስድስት ሳምንት በፊት ፈተናውን የሚያደራጀውን ግለሰብ ወይም በኢትዮጵያ የሚገኘውን የብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ያነጋግሩ። ልዩ ዝግጅት እንዲደረግልዎት ጥያቄ ሲያቀርቡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተሰጠዎትን የሕክምና መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይኖርብዎታል።.እንዲደረጉልዎት ከሚፈልጓቸውልዩ ዝግጅቶች ጋር በተያያዘ እንዴት ልንረዳዎት እንደምንችል የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ።