ተማሪ ተፈታኝ ከሆኑ የምዝገባ ቅፅዎትን የሚያገኙት በትምህርት ቤትዎ በኩል ነው። ቅፁን ይሙሉ እና ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያስረክቡ። ትምህርት ቤትዎ የማስመዝገቡንም ሆነ የክፍያውን ሂደት በብሪቲሽ ካውንስል ያከናውናል። መፈተን እንደተፈቀደልዎት እና ስለ መፈተኛ ቦታዎት የሚገልፅ መረጃ ከፈተናው ቀን ሶስት ሳምንታት ገደማ አስቀድሞ ሊደርስዎት ይገባል።

እንዴትልዩ ዝግጅቶች ማድረግ እንደሚችሉ እዚህ ይመልከቱ።