የግል ተፈታኞች እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ከዚህ በታች ይመልከቱ፦

1ኛ ደረጃ፦ የምዝገባ ቅፅዎን ይሙሉ

የምፈተነው ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) ነው

የምዝገባ ቅፅዎትን በአዲስ አበባ በሚገኘው ብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ መሙላት ይችላሉ። ቡድናችን፣ ሁሉንም ቅደም ተከተሎች ጠብቀው ማመልከቻ እንዲሞሉ ሊረዳዎት ምን ጊዜም ዝግጁ ነው። 

መቼ ልመዝገብ?

የካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛምስ (CIE) ምዝገባ ስለሚያበቃበትን ቀን እዚህ ይመልከቱ። 

ልዩ ዝግጅቶች ማድረግ ያስፈልገኛል? 

ስለ ልዩ ዝግጅቶች እዚህ ይመልከቱ። 

የምፈተነው ፒርሰን ኤዴክሴል ነው

የምዝገባ ቅፅዎትን በአዲስ አበባ በሚገኘው ብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ መሙላት ይችላሉ። ቡድናችን፣ ሁሉንም ቅደም ተከተሎች ጠብቀው ማመልከቻ እንዲሞሉ ሊረዳዎት ምን ጊዜም ዝግጁ ነው።

መቼ ልመዝገብ?

PEARSON EDEXCEL ፈተናዎች ምዝገባ ስለሚያበቃበት ቀን እዚህ ይመልከቱ።

ልዩ ዝግጅቶች ማድረግ ያስፈልገኛል? 

ስለ ልዩ ዝግጅቶች እዚህ ይመልከቱ። 

2ኛ ደረጃ፦ የፈተና ክፍያ ይፈፅሙ

የሁሉንም ፈተናዎች የክፍያ ተመን በምዝገባ ቅፁ ላይ ያገኛሉ። አስፈላጊውን ክፍያ ካልፈፀሙ ማመልከቻዎ ተቀባይነት አያገኝም።

ከ500 ብር በላይ የሆነ ክፍያ በሙሉ የሚከናወነው በጥሬ ገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ሲሆን በየትኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በኩል ገንዘቡ ለብሪቲሽ ካውንስል እንዲከፈል ገቢ ማድረግ ይቻላል።

መቀጮዎች

የእያንዳንዱ ፈተና አዘጋጆች፣ ሁሉንም የፈተና ክፍለ ጊዜያት የሚመለከትመደበኛ የአመዘጋገብ ሥርዓት አላቸው። ለፈተና ምዝገባ ከተመደበው ጊዜ በኋላም ቢሆን መመዝገብ የሚችሉ ቢሆንም ትክክለኛው ቀን በማለፉ መቀጫ መክፈል ይጠበቅብዎታል። ዘግይቶ ለመመዝገብ የሚከፈለውን መቀጫ የሚመለከት ተጨማሪ መረጃ በፈተና ምዝገባ ቅፅዎት ላይ ማግኘት ይችላሉ።

3ኛ ደረጃ፦ የምዝገባ ቅፅዎን ያቅርቡ

አሁን የምዝገባ ቅፅዎትን ሞልተዋል፣ የፈተና ክፍያም ፈፅመዋል።

የመጨረሻው ደረጃ ደግሞ ማመልከቻዎትን ለብሪቲሽ ካውንስል ማቅረብ ነው።

ከዚህ በታች በተገለፀው መንገድ ማመልከቻዎን ማቅረብ ያስፈልግዎታል፦

  1. ሁሉም ነገር የተሞላበት እና የተፈረመበት የማመልከቻ ቅፅ። እባክዎ ይህንን ቅፅ ፎቶኮፒ አድርገው ለራስዎ ያስቀሩ።
  2. የፓስፖርት መጠን ያላቸው ሶስት ባለቀለም ፎቶግራፎች። እነዚህ ፎቶዎች አንድ አይነት መሆን አለባቸው፤ እንዲሁም ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የተነሷቸው ሊሆኑ ይገባል።
  3. ቀኑ ያላለፈበት የቀበሌ መታወቂያዎ ወይም የፓስፖርትዎ በግልፅ የሚታይ ፎቶኮፒ።
  4. ክፍያ የፈፀሙበት ደረሰኝ። እባክዎ የዚህን ደረሰኝ ፎቶኮፒ ለራስዎ ያስቀሩ።

4ኛ ደረጃ፦ ምዝገባ ማጠናቀቅ

አሁን የትምህርት ቤት ፈተናዎችን ለመውሰድ በብሪቲሽ ካውንስል በተሳካ ሁኔታ ተመዝግበዋል።

መፈተን እንደተፈቀደልዎት እና ስለ መፈተኛ ቦታዎት የሚገልፅ መረጃ ከፈተናው ቀን ሶስት ሳምንታት ገደማ በፊት ይደርስዎታል።

ማስተካከል የሚፈልጉት ነገር አለ?

በምዝገባ ወቅት ያቀረቡትን መረጃ መቀየር ከፈለጉ እባክዎ መጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን፤ እኛም በዚህ ረገድ የተለመደው አሠራር ምን እንደሆነ እናሳውቅዎታለን።