ብሪቲሽ ካውንስል እያንዳንዱ ተፈታኝ ያለ አድልዎና እንደ ፍላጎቱ እንዲስተናገድ እንዲሁም ፈተናውን ሲወስድ አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ የተመቻቹለት እንዲሆኑ ጥረት ያደርጋል። ተፈታኞች መፈተኛ ቦታውን እንዲያገኙ፣ ጥያቄዎቹን እንዲረዱና ለፈተናው መልስ እንዲሰጡ ለማስቻል ልዩ ሁኔታዎችን ወይም መሟላት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ማዘጋጀት እንችላለን።
ፈተናውን ለመውሰድ ልዩ ዝግጅት እንዲደረግልዎት መጠየቅ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ እያንዳንዱን ፈተና በተመለከተ ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች ይከተሉ። ልዩ ዝግጅቶች የማድረጉ ሁኔታ በፈተና ቦርዱ ላይ ነው፤ በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ ካለብዎት የአቅም ገደብ ወይም አስቸጋሪ ሁኔታ አንጻር አንዳንድ የፈተና ዓይነቶችን መተው ሊፈቀድልዎት ይችላል። የምዝገባው ጊዜ ካበቃ በኋላ ልዩ ዝግጅቶችን የሚመለከቱ ሰነዶችን እንደማንቀበል አባክዎ ያስታውሱ።
ልዩ ዝግጅት ማድረግ የሚቻልባቸው የፈተና ዓይነቶች፦
- IELTS
ተሻሽሎ የተዘጋጀውን የIELTS ፈተና መፈተን የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ ከፈተናው ቀን ቢያንስ ከሦስት ወር በፊትመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን። ይህን አስቀድመን ማወቃችን የተሻሻለውን ፈተናውን ለማዘጋጀት ያስችለናል።
እርስዎ ካሉበት ሁኔታ አንጻር ቢሮው ልዩ ዝግጅት እንዲያደርግልዎት የሚያስፈልግ ከሆነ ለምሳሌ፣ ተጨማሪ ሰዓት እንዲሰጥዎት የሚያስፈልግ ከሆነ ጉዳዩን ለማሳወቅ ቢያንስ ከስድስት ሳምንት በፊትመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን። ለምዝገባ ወደ ቢሮ በሚመጡበት ጊዜ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተሰጠዎትን የሕክምና ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይገባዎታል።
- የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ፈተናዎች
የአካል ጉዳተኛ ከሆኑ ወይም ልዩ ፍላጎት ካለዎት ከፈተናው ቀን ቢያንስ ከሦስት ወር በፊትመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን። ለፈተናው ሲመዘገቡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተሰጥዎትን የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርብዎታል።
ለካምብሪጅ ኢንግሊሽ ፈተናዎች ልዩ ዝግጅት እንዲደረግልዎት መጠየቅ የሚችሉት በወረቀት ለሚሰጡት ክፍሎች ብቻ ነው።
- IGCSE/ International GCSE እና የትምህርት ቤት ፈተናዎች
ቢሮው ልዩ ዝግጅት እንዲያደርግልዎት የሚፈልጉ ከሆነ ለምሳሌ፣ ተጨማሪ ሰዓት እንዲሰጥዎት ወይም ፈተናዎች በመደራረባቸው ልዩ የመፈተኛ ዝግጅት እንዲደረግልዎት ቢፈልጉ የመጀመሪያውን ፈተና ከሚወስዱበት ቢያንስ ከስድስት ሳምንት በፊትመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን።
ያሉበት ሁኔታ ልዩ የፈተና አይነት እንዲዘጋጅልዎት የሚያስገድድ ከሆነ ለፈተናው በሚመዘገቡበት ጊዜ በመጀመሪያ እኛንመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን። እንዲሟላልዎት ከሚፈልጉት ልዩ ዝግጅት ጋር የቅርብ ጊዜ የሕክምና ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ ይኖርብዎታል።
- የሥራ ሙያ እና የዩኒቨርሲቲ ፈተናዎች
ልዩ ዝግጅት እንዲደረግልዎት በሚፈልጉበት ጊዜ በአብዛኛው የፈተናውን ቦርድ ወይም ዩኒቨርሲቲውን በቀጥታ ማነጋገር ይኖርብዎታል። የፈተና ቦርዱ ስለ ተደረጉት ዝግጅቶች ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር የሚነጋገር ሲሆን ጥያቄዎት ተቀባይነት ስለማግኘቱ ለእርስዎ ያሳውቃል።
ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡት እኛ ዘንድ ከሆነ እንዲሟላልዎት የሚፈልጉት ልዩ ጥያቄ ቢኖር እባክዎ እኛንመጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን። ለምዝገባ በሚመጡበት ጊዜ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተሰጥዎትን የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርብዎታል።