ለሚወስዱት ፈተና እያጠኑ ያሉም ይሁኑ ተማሪዎችዎ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ የመርዳት ጉጉት ያለዎት አስተማሪ ድጋፍ ልናደርግልዎት እንችላለን። ብሪቲሽ ካውንስ የሚያስፈልግዎትን ድጋፍና ምክር ሁሉ ሊሰጥዎት ይችላል፤ ይህም በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ ለጥናት የሚጠቅሙ መረጃዎችን ጨምሮ በቤተ መጻሕፍታችን የሚገኙ ጽሑፎችን መጠቀም ይችላሉ።
ለፈተና የሚጠቅሙ ምክሮች፣ መማሪያዎች እና ድጋፍ
ፈተና በጣም የተረጋጉ በሚባሉ ተማሪዎችም ላይ ሳይቀር ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። ይሁንና የተወሰነ ዝግጅት በማድረግና የታሰበበት የጥናት ፕሮግራም አውጥሮ ትምህርቱን በመከለስ የሚገባዎትን ውጤት ማግኘት ይችላሉ።