የብሪቲሽ ካውንስል ተማሪዎች GCSEPod የተባለውን የኢንተርኔት ላይ መማሪያ በፈለጉት ጊዜ በነፃ መጠቀም ይችላሉ፤ ይህ መማሪያ የሚገባዎትን ውጤት እንዲያገኙ ሊረዳዎት የሚችል እጅግ ግሩም የሆነ ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ ዝግጅት ነው።

ድረ ገጹ ለመረዳት ቀላል የሆኑ በድምፅ የተቀዱ ጠቃሚ ሐሳቦችንና የጥናት መመሪያዎችን በትንሽ በትንሹ ያቀርባል። ፕሮግራሞቹን በቀጥታ ኢንተርኔት ላይ ሆነው በኮምፒውተር ማዳመጥ ይችላሉ ወይም ደግሞ የGCSEPod በድምፅ የሚተላለፍ ፕሮግራም በስማርትፎን ማዳመጥ ይችላሉ።

የሚከተሉትን ማግኘት ይችላሉ፦

  • ቁልፍ ለሆኑ የትምህርት ዓይነቶች እጥር ምጥን ያሉ የማጠቃለያ ሐሳቦች
  • ከዚህ በፊት የተሠሩ የጥናት ውጤቶችን ሊንኮች
  • አጫጭር መረጃዎችና ምክሮች
  • የሥርዓተ ትምህርት መረጃ።

GCSEpod ምን ነገሮችን እንደያዘ እዚህ ይመልከቱ።

GCSEpod ድረ ገጽ ለመጠቀም ትምህርት ቤቱ ወደ ድረ ገጹ ለመግባት የሚያስችሎትን ትክክለኛ መረጃዎች ይሰጥዎታል።

የብሪቲሽ ካውንስልን ተጨማሪለፈተና የሚጠቅሙ ሃሳቦች በነፃ ኢንተርኔት ላይ ማግኘት ይችላሉ።