ክብረት ከበደ ቱፋ፣ የቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ የሆነው ጠብታ የአምቡላንስ አገልግሎት መስራች እና ባለቤት ናቸው፤ ይህ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የአንቡላንስ አገልግሎት ሰጪ ማኅበራዊ ተቋም ነው።
አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የሕክምና ትምህርት ቤት እና ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ለ17 ዓመታት ሰመመን ሰጪ ነርስ ሆነው ሢሠሩ የቆዩት ክብረት፣ በርካታ ድንገተኛ ክስተቶችን ሲያስተናግዱ በአምቡላንስ አገልግሎት ችግር ምክንያት የበርካቶች ሕይወት በከንቱ ሲቀጠፍ በአይናቸው ተመልክተዋል።
ሕይወት ቀጣፊ የሆኑ መንገዶች ካሉባቸው ጥቂት አገሮች መካከል በአንዷ የሚኖሩት እኚህ ሰው፣ ሕይወት አድን አገልግሎት መስጫ አለመኖሩ በየእለቱ የሚያሳዝናቸው ጉዳይ ነበር። “ተጎጂዎችን ለመርዳት እነርሱ ዘንድ መሄድ ሲገባን፣ ምንም ዓይነት ሕይወት አድን ድጋፍ ሳይደረግላቸው እኛ ድረስ እስኪመጡ የምንጠብቀው እስከ መቼ ነው?” በማለት ባልደረቦቻቸውን ይጠይቁ ነበር።
ምንጭ፦ ዘ ጋርዲያን