የብሪቲሽ ካውንስል የተማሪዎቹን ጤና ከሁሉ በፊት ያስቀድማል፡፡ እናም በዚህ ጊዜ በኮቪድ-19 ቀውስ ሳቢያ ሁሉንም የማማከር አገልግሎቶቻችንን በመረጃ መረብ ላይ እንሰጣለን፡፡
በብሪቲሽ ካውንስል ውስጥ ለሚፈልጉት ኮርስ መመዝገብ ቀላል ነው፡-
እርምጃ 1 - የምክክር ጊዜ ለመወሰን
ምክክሩ ያሉዎትን አማራጭ ኮርሶች ዙሪያ ለመወያየት ጠቃሚ ነው፡፡
- ለምክርዎ ተስማሚ የሆነ ጊዜ እና ቀን ይምረጡ፡፡
- የ Zoom መተግበሪያን በመጠቀም ምክክሩ በመረጃ መረብ በመጠቀም ይካሄዳል፡፡
- የምክክሩን አገልግሎቱን በነጻ ነው የሚያገኙት
እርምጃ 2 - በመረጃ መረብ የሚሞላ አጭር እንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛ ይውሰዱ
አንዴ የምክክር ቀጠሮ ከያዙ በኋላ በመረጃ መረብ የሚሰጥ የእንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛ ጋር የሚያገናጭ ልዩ ማያያዣ ወይም ሊንክ ይላክልዎታል፡፡
- የእንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛው 30 የምርጫ ጥያቄዎችን የያዘ ነው።
- የእንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛው ለማጠናቀቅ 30 ደቂቃዎች ይኖርዎታል።
- እባክዎን የኢንተርኔት የመናገር ክህሎት መመዘኛ ፈተናን ከመውሰድዎና ከማማከር ቀጠሮዎ በፊት የእንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛውን ይውሰዱ፡፡
እርምጃ 3 - በመረጃ መረብ የሚሰጠውን የመናገር ክህሎት መመዘኛ ይውሰዱ
ከቀጠሮ ቀንዎ በፊት ከመምህሮቻችን አንዱ የመናገር ችሎታውን የሚመዝን ይሆናል
- ይህ አጭር ቃለ መጠይቅ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ የሚወስድ ይሆናል
- እባክዎ ከፈተናው ሰዓት ጥቂጥ ቀድመው ወደ መተግበሪያዎን ይክፈቱ
እርምጃ 4 - በመረጃ መረብ የሚሰጠውን የማማከር አገልግሎትን ይካፈሉ
- የሰለጠኑ አማካሪዎቻችን በመረጃ መረብ እርስዎ የወሰዱትን አጭር የእንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛ ፈተና ወጤት ከእርስዎ ጋር በመወያየት ለእርስዎ ተስማሚ የሆነ ኮርስ ያገኙልዎታል።
- ምክክሩ ከ10 እስከ 20 ደቂቃዎች ይወስዳል፡፡
እርምጃ 5 - ለኮርስ መመዝገብ
- ከምክክርዎ በኋላ ለተመረጠው ኮርስ መመዝገብ እና መክፈል ይችላሉ፡፡
- ለተመረጠው ኮርስለ መመዝገብ እና ለመክፈል 18 ዓመት ሊሆንዎ ይገባል፡፡
የምክክር አገልግሎት ቀጠሮ ለመያዝ ድጋፍ ከፈለጉ እባክዎ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ማዕከላችን በመደወል የደንበኞች አገልግሎት ተወካዮቻችንን ያግኙ፡፡