ፍላጎቶችዎን ለማሟላት መጠነ ሰፊ እና አመቺ ኮርሶችን እናቀርባለን። ዕድሜዎ፣ የእውቀት ደረጃዎ ወይም የትምህርት ግብዎ ምንም ይሁን ምን ፣ ለእርስዎ የሚሆን ኮርስ አለን ፡፡
በብሪቲሽ ካውንስል እንግሊዝኛን እንዴት እናስተምራለን?
- የመማርን ማስተማር ሂደቱን አነቃቂና አስደሳች በማድረግ ተማሪዎች ከመማር ባሻገር ደስ ብሏቸው እንዲማሩ እናደርጋለን
- የተለያዩ ተማሪዎች የተለያዩ የመማር ዘዴዎች ስላሏቸው የተለያዩ የማስተማር ቴክኒኮችን እንጠቀማለን ፡፡
- በቀን ተቀን ህይወቶቻቸው ግንኙታቸው የሚጠቅም የመግባቢያ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ተማሪዎችን በጥንድ እና በቡድን እንዲሠሩ እንጠይቃለን።
- ብዙ ልምድ እና የተፈተነ ችሎታ ባላቸው መጽሀፍ አሳታሚዎች የተዘጋጁ ልዩ መጽሃፍቶችን እና በአስተማሪዎቻችን የተቃኙ እና የተዘጋጁ ማቴሪያሎችን እንጠቀማለን ፡፡
- ተማሪዎችን የቋንቋ ግብዓት እንሰጣለን፤ በቂ ልምምድ እንዲያደርጉም እናደርጋለን ፡፡
- እንዲሁም በራስዎ ብቁ የቋንቋ ተማሪ ለመሆን የሚረድዎትን የጥናት ክህሎቶችን እናስተምራለን ፡፡
- በትምህርቱ ውስጥ ንቁ ሚና እንዲሚጫወቱ እንጠብቅብዎታለን።