እባክዎን ያስታውሱ እ.ኤ.አ. ከኤፕሪል 7 ፣ 2020 ለሚወሰዱ የIELTS ለUKVI ፈተናዎች የሚከተለው የUKVI ልዩ ስረዛዎች እና ማስተላለፍ መመሪያ ተግባራዊ ይሆናል። ፈተናዎን ከኤፕሪል 7 በፊት የሚወስዱ ከሆነ ወይም IELTS ለ UKVI የማይወስዱ ከሆነ እባክዎን አጠቃላይ ፖሊሲውን ይመልከቱ።
ማስታወሻ፥ ይህ መመሪያ የሚያገለግለው IELTS ለUKVI ለሚወስዱ ተፈታኞች ነው ለሌሎች የIELTS ፈተናዎች እባክዎን ይህን ገጽ ያንብቡ::
ሀ. ፈተናን ስለመሰረዝ
የIELTS ፈተና ምዝገባዎን በማንኛውም ሰአት ለመፈተኛ ማእከልዎ በማሳወቅ መሰረዝ ይችላሉ። ገንዘብዎ ተመላሽ የሚደረገው ስረዛውን የሚያደርጉት መቼ እንደሆነ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ሁኔታዎች ይተገበራሉ በሚለው መሰረት ነው።
1. የፈተና ቀን እና ሰአት
1.1. ከፈተናው 14 ቀናት በፊት፡
የ IELTS ፈተናዎን ለፈተናው 14 ቀናት ከመቅረቱ በፊት የሚሰርዙ እንደሆነ ከጠቅላላው የፈተና ክፍያ ላይ 75% ተመላሽ የሚያገኙ ይሆናል።
1.2. በ 14 ቀናት ውስጥ ነገር ግን ፈተናው ከመድረሱ 2 ቀናት በፊት፡
የ IELTS ፈተና ምዝገባን በ 14 ቀናት ውስጥ ነገር ግን ለፈተናው ከ 2 ቀን በላይ ሲቀር የሚሰርዙ ከሆነ ከጠቅላላው የፈተናው ክፍያ ውስጥ 50% ተመላሽ ይደረግልዎታል።
1.3. ፈተናው ከመድረሱ በ 2 ቀናት ውስጥ፡
የ IELTS ፈተና ምዝገባን ፈተናው ከመድረሱ በ 2 ቀናት ውስጥ የሚሰርዙ ከሆነ ከጠቅላላው የፈተናው ክፍያ ውስጥ 25% ተመላሽ ይደረግልዎታል።
1.4. በፈተናው ቀን ወይም ከፈተናው ቀን በኋላ፡
የ IELTS ፈተና ምዝገባን በፈተናው እለት ወይም ከፈተናው ቀን በኋላ የሚያደርጉ እንደሆነ ምንም አይነት ተመላሽ አይደረግልዎትም።
2. በተለየ መልኩ የሚታዩ ተፈታኞች
ከፈተናዎ ቀን በፊት ወይም ፈተናውን ያልወሰዱ እንደሆነ ከፈተናው ቀን በኋላ እስከ 5 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ይታይልዎ ዘንድ መጠየቅ ይችላል። ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ የፈተና ማእከልዎ በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ መልስ ይስጥዎታል። የፈተና ማእከልዎ ጉዳይዎ ልዩ ምርመራ የሚያስፈልገው ከሆነ ምርመራ ያደርጋል።
ከፈተናው ቀጠሮ ቀን በኋላ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ ሁሉም የልዩ እይታ ጉዳዮች እንዲሁም ድጋፍ የሚያደርጉ ዶክመንቶች ለፈተናው ማእከል መቅረብ ይኖርባቸዋል።
የፈተና ማእከልዎ ጥያቄዎን የሚያፀድቀው ከሆነ፣ እስከ የአገልግሎት ክፍያ ተቀናሽ ተደርጎ ቀሪው ክፍያ ተመላሽ ይሆንልዎታል::
የፈተና ማእከልዎ ጉዳይዎን ውድቅ የሚያደርገው እንደሆነ፣ በክፍል 1 ላይ ያሉት ደንቦች የሚተገበሩ ይሆናል።
ልዩ የሆኑ ሁኔታዎችን የምንተገብረው እንደሚከተለው ነው፡
የውትድርና አገልግሎት
3. የፈተና ማእከል ልዩ እይታዎች
በአንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ከፈተናው ማእከል ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ካሉ ፈተናውን ልንሰርዝ እንችላለን። እነዚህም ሁኔታዎች የሚከተሉትን የሚያካትቱ ሲሆን እነዚህ ብቻ ግን አይደሉም፤ ከባድ የአየር ሁኔታ፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የሀገር አለመረጋጋት እና የኢንዱስትሪያዊ ውሳኔ።
በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ፣ የፈተና ማእከልዎ የሚቻለውን ያክል ቀድሞ ማሳወቂያ የሚልክልዎ ሲሆን የሚከተለውን ምርጫ ይሰጥዎታል፡
-
ሙሉ የገንዘብ ተመላሽ፣ ወይም፣
-
ለእርሶ ወደሚመች ቀን ተቀያሪ የፈተና ቀን።
የፈተናው ማእከል በ ቁጥጥሩ ስር ባሉ ጉዳዮች ምክንያት ፈተናውን ቢሰርዝ ከሙሉ የገንዘብ ተመላሽ ወይም ተቀያሪ የፈተና ቀን በተጨማሪ ላወጡት ወጪ ገንዘብ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ምክንያትዎ ለዚህ የሚያበቃ መሆኑን መሆን አለመሆኑ በፈተናው ማእከል የሚወሰንበት ጉዳይ ሲሆን ማንኛውም ካሳ በሚከተሉት ሁኔታዎች መሰረት የሚሰጥ ይሆናል፡
-
የፈተናው ማእከሉ ስረዛውን ያደረገው በቁጥጥሩ ስር ባለ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም።
-
ማንኛውም ካሳ በጉዞ እና ማደሪያ ወጪዎች ላይ ሽፋን የሚያደርግ ሲሆን እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡
-
የፈተናዎን ቀን በማቀድ ሂደት ውስጥ በቀጥታ ያለ ወጪ፣
-
በክፍያ ደረሰኝ(ኞች) ማስረጃ የተረጋገጠ፣
-
የታቀዱ ጎዞዎች እና/ወይም በቆይታዎ የማደሪያ ወጪዎች ከአገልግሎት ሰጪው ምንም አይነት ተመላሽ የማይገኝላቸው ከሆኑ፣
-
የተጠየቀው ወጪ አሁን ባለው ገበያ ዝቅተኛ የክፍያ መጠን ጋር የተመሳከረ መሆን አለበት (ይህ የሚደረገው በፈተናው ማእከል ይሆናል)።
-
ቅርብ ከሆነው የፈተና ማእከል ወደ መደበኛ የመኖሪያ ስፍራዎ ተጨማሪ ጉዞ አድርገው ከሆነ የፈተናው ማእከል የተመላሽ ይገባኛል ጥያቄዎን ዋጋ አይሰጠውም ማለት ነው።
ለ. የፈተና ቀን ዝውውሮች
4.1. ከፈተናው 14 ቀናት በፊት፡
ፈተናው ከመድረሱ 14 ቀናት በፊት የፈተናዎን ቀን በማንኛውም ቀን ሊቀይሩ ይችላሉ።
ይህ አማራጭ መጀመሪያ ከተመዘገቡቡት የፈተና ቀን ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ የፈተና ቀን መምረጥ አለብዎት። የሚፈልጉት ቀን እርሶ መጀመሪያ ከመረጡት ቀን ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ የሌለ ከሆነ ዝውውርዎ እንደ ስረዛ የሚታይ ይሆናል።
አንድን የፈተና ቀን ማዛወር የሚችሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
የፈተና ማእከልዎ ከጠቅላላው ክፍያ መጠን ውስጥ እስከ 25% የሚሆን የአስተዳደር ክፍያ ሊያስከፍልዎ ይችላል።
4.2. ፈተናው ከመድረሱ በ 14 ቀናት ውስጥ፡
ለፈተናው 14 ቀን ሲቀር የሚደረግ ማንኛውም የዝውውር ጥያቄ እንደ ስረዛ ይታያል። እባክዎ ክፍል ሀ. ስረዛዎች የሚለውን የዚህን ፖሊሲ ክፍል ይመልከቱ።
ማስታወሻዎች
i. ተመላሽ ማድረግ እና የፈተና ቀን ዝውውሮችን ማደራጀት የፈተና ማእከልዎ ሃለፊነት ነው።
ii. በክፍል ሀ. 2. መሰረት ከፈተና ወሳጅ የልዩ ሁኔታ ይገባኛል ጥያቄ ጋር ውሳኔዎችን ማድረግ የፈተናው ማእከል ሃላፊነት ነው።
iii. በክፍል ሀ. 3. መሰረት ከካሳዎች፣ ይህም ብቁነት እና ምን ያክል ካሳ ነው የሚሰጠው የሚለውን ውሳኔ ጨምሮ የመወሰን ስልጣን ያላው የፈተናው ማእከል ነው።
iv. እርሶ የIELTS ፈተናን ለመውሰድ በተመዘገቡበት ሀገር ውስጥ የሸማቾች ጥበቃ ህግ ያለ ከሆነ እና እነዚህ ህጎች ከላይ ከተጠቀሱት ደንቦች ይልቅ ለፈተናው ወሳጅ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኙ ከሆነ፣ የሸማቾች ጥበቃ ህግ የሚተገበር ይሆናል ማለት ነው።