ከቤትዎ ወይም ከስራ ቦታዎ በምቾት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠናዎች ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው

እንደ እርስዎ ያሉ ተማሪዎች ይቀላቀሉ። የትምህርት ፋላጎትዎን የሚያሟላ ምርጫ በመምረጥ የትምህርት መንገድዎን መቆጣጠር ይችላሉ። አነስተኛ የተማሪዎች ቁጥር ባለባቸው ክፍሎች ስለሚማሩ የግል ፍላጎትዎ እና የሚያሳዩት ለውጥ በትክክል እንዲታወቅ ያደርጋል።

  • ከተማሪዎች ጋር በጥንድ እና በቡድን እንዲገናኙ ያደርጋል
  • ሙሉ በሙሉ በብሪቲሽ ካውንስል የትምህርት ባለሙያዎች የታገዘ ትምህርት ያገኛሉ
  • በጽሁፍ እና በንግ ግር ክህሎቶች ላይ በማተኮር የመገባባት ችሎታዎን አንዲያሳድጉ ይደረጋል

የስልጠና ይዘት 

የጊዜ ርዝመት - 6 ሳምንታት

የሚሰጥበት መንገድ – በኢንተርኔት ላይ የሚሰጡ ተከታታይ ስልጠናዎችን መከታተል አንዲሁም በግል ለመማር ምቹ በሆነው መተግበሪያችን በመተከም ማጥናት ይችላሉ 

ክፍለ ጊዜ - በሳምንት ሁለት ጊዜ ለ90 ደቂቃ የሚሰጡ የኢንተርኔት ክፍለ ጊዜዎች ሲሆኑ በተጨማሪም አንድ ሰዓት በ አጋዥ መምህር የታገዘ ትምህርት

ዋጋ - 2800 ብር በኮርስ

የትምህርት ክፍለ ጊዜ

ረቡዕ/አርብ ወይም ማክሰኞ/ ሃሙስ

ከጠዋቱ 3ሰዓት እስከ 4:30, ከጠዋቱ 5ሰዓት እስከ 6:30

ከሰዓት 8ሰዓት እስከ 9ሰዓት 

 ማታ 12ሰዓት እስከ 1:30


የስልጠና ቀናት

ተርም 2A የአዋቂዎች እንግሊዝኛ 

 ተርም 2B የአዋቂዎች እንግሊዝኛ 

 ተርም 3A የአዋቂዎች እንግሊዝኛ 

ተርም 3B የአዋቂዎች እንግሊዝኛ 

 በኢንተርኔት 

በኢንተርኔት 

በኢንተርኔት 

በኢንተርኔት 

ሰኔ 1 - ነሃሴ 1 2012

ነሃሴ 11 - 11 መስከረም 2013

መስከረም 18 - ጥቅምት 29

ጥቅምት 30 - ታህሳስ 26

የሚያገኟቸው ጥቅሞች

የትምህርት ክፍለ ጊዜው ሌሎች ስራዎችዎን ዕቅድ ውስጥ አስገብተው ለመምረጥ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው።

መምህርዎ እንደ በፊቱ በሁሉም የትምህርት ተግባራት - በማንበብ በመጻፍ በመናገር እና በማድመጥ - አብሮዎት ይሰራል። ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በቀጥታ መስመር ላይ ይካሄዳል። ትምህርቱ እንደበፊቱ ተግባቦታዊና አስደሳች ነው። ከትምህርት ክፈል ጊዜዎ በፊት እና በኋላ በግል የሚያደርጉት ጥናት በቀጥታ የሚሰጥዎን የትምህርት ክፍለ ጊዜ የበለጠ ቀላል ያደርግልዎታል።

መምህሮቻችን የተመረጡ ከፍተኛ ልምድና ተዓማኒነት ያላቸው ናቸው በዚህም ከእርስዎ ጋር ጠቃሚ ግብረ መልስና ክህሎት በመለዋወጥ ይሰራሉ

እርስዎ ስልጠናዎን ሙሉ በሙሉ የመከታተልና የመቆጣጠር አቅም አለዎት። Zoom መተግበሪያን ያውርዱ እኛ ስልጠናውን የሚከታተሉበትን መመሪያ እንልክልዎታለን። ፕሮግራሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባላቸው የመረጃ መጠበቂያ ፖሊሲዎችና ሂደቶች የሚመራ ነው። 

እንዴት ይማራሉ

  • መግባባትን በሚጨምሩ ተግባራት ላይ በሚያተኩር የትምህርት መዋቅር ከመምህርዎ እና ሌሎች ተማሪዎች ጋር ብዙ የንግግር ልምምዶችን ያደርጋሉ
  • ፍላጎት እና ተነሳሽነትን በሚያዳብሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ይማራሉ

በእያንዳንዱ ደረጃ ምን ይማራሉ

የመማሪያ ፕሮግራማችን ለእያንዳንዱ ደረጃ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ነው በሂደት አዲስ ነገሮችን በማስተዋወቅ በራስ መተማመንን ለማሳደግና የተማሪዎችን ለውጥ ለመመዘን ይረዳል። 

በጀማሪ ደረጃ ቀላል የቀን ከቀን ርእሶች ለተማሪዎች አዲስ ቃላትን ለመማርና ጠቃሚ ወደሆኑ ቃለ ምልልሶችና ጽሁፎች እንዲገቡ ያደርጋል። 

በቅድመ መካከለኛ እና በመካከለኛ ደረጃ ላይ ትምህርቱ በመስፋት በግል አስተያየትና በማህበራዊ ህይወት እንዲሁም በስራ ቦታ ባሉ ርዕሶች ላይ ያተኩራሉ።  ብዙ ከበድ ያሉ ሃሳብን መግለጫ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላሉ ይህም ክርክርን፣ መረጃ ልውውጥን፣ አጭር ጹሁፍና ኢሜይል መጻፍን ያካትታል።

ከፍተኛ መካከለኛ ደረጃዎች ሰፋ ያሉ ርዕሶችን የያዙ ናቸው። ተማሪዎች እንዴት ስለ ህይወትና ስራ ሀሳባቸውን መግለጽ እና ሀሳብን ከሌሎች ማግኘት እንደሚችሉ ይማራሉ እጅግ ከበድ ያሉ ሃሳቦች እና እይታዎች ይታያሉ

የምክክር አገልግሎት ቀጠሮ ይያዙ

ለእርስዎ ትክክለኛ የሆነውን ኮርስ እንዲመርጡ ለማገዝ፤ ከመመዝገብዎ በፊት ከእኛ ጋር የምክክር ቀጠሮ መያዝ ያስፈልግዎታል ፡፡. ስለዚህ ሂደት የበለጠ ለመረዳት ኮርስ ለመውሰድ ይመዝገቡ (ከ18 አመት በላይ ለሆኑ) የሚለውን ገጽ ያንብቡ፡፡.