የብሪቲሽ ካውንስል የተማሪዎቹን ጤና ከሁሉበፊትያስቀድማል፡፡እናም በዚህ ጊዜ ​​በኮቪድ-19 ቀውስ ሳቢያ ሁሉንም የማማከር አገልግሎቶቻችንን በመረጃ መረብ ላይ እንሰጣለን፡፡

በብሪቲሽ ካውንስል ውስጥ ለሚፈልጉት ኮርስ መመዝገብ ቀላል ነው፡፡

አርምጃ 1 - የምክክርቀጠሮ ለመያዝ

  • ምክክሩን በመረጃ መረብ / ድረገጻችንን በመጠቀም እኛን በማግኘት ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ፡፡
  • ልጅዎ በመረጃ መረብ በሚሰጠው የምክክር ጊዜ የቋንቋ ብቃቱ/ቷን ለመለካት ያስችለን ዘንድ መገኘት አለባቸው፡

አርምጃ 2፡ የምክክር ክፍለ ጊዜዎ ላይ መገኘት በመረጃ መረብ የሚሞላ አጭር እንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛ ይውሰዱ፡፡

  • የምክክሩ ክፍለ ጊዜዎ (በቀጠሮዎ መሰረት) ሲካፈሉ ልጅዎ በመረጃ መረብ የሚሞላ አጭር እንግሊዘኛ ብቃት መመዘኛ ይወስዳል/ትወስዳለች፡፡
  • ምክክሩ ከ 20 እስከ 30 ደቂቃዎች ይወስዳል፡፡
  • የZoom መተግበሪያ  በመጠቀም ምክክሩ በመረጃ መረብ በመጠቀም የሚካሄድ ሲሆን ለምክክሩ ምንም ብር አይከፍሉም
  • እባክዎ ከቀጠሮዎ ሰዓት ጥቂጥ ቀድመው መተግበሪያዎን ይክፈቱ

አርምጃ 3 - ለኮርሱ መመዝገብ

  • ልጅዎ የወሰደው/የወሰደችው አጭር የእንግሊዘኛቨብቃትቨመመዘኛ ፈተና ውጤት፤ ካሉን ለህጸናት የሚሰጡ ኮርሶች መካካል የትኛውን መውሰድ እንዳለበት/እንዳለባት እንድንወስን ይረዳናል፡፡
  • ለተመረጠው ኮርስ  ለመመዝገብ  እና  ለመክፈል 18 ዓመት ሊሆንዎ ይገባል፡፡

ድጋፍ ለማግኘት 

የምክክር አገልግሎት ቀጠሮ ድጋፍ ከፈለጉ እባክዎ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ማእከላችን በመደወል/ ኢሜል በማድረግ የደንበኞች አገልግሎት ተወካዮቻችንን ያግኙ፡፡