የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድህነት የማስወገድና ዘላቂ እድገት የማምጣት ሂደትን ያፋጥናሉ
DelPHE፣ ሃየር ኤጁኬሽን ሊንክስ (እ. ኤ. አ. ከ1981-2006) ከተባለው ፕሮግራም በተገኙ ተሞክሮዎች ላይ በመመሥረት የተዋቀረ የዚያ ፕሮግራም ቀጣይ ክፍል ነው።
DelPHE በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (HEIs) ተደጋግፈው በመሥራት የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲያሻሽሉ የሚረዳ አዲስ መንገድ ተደርጎ ተወስዷል፦
- የሥርዓተ ትምህርት ትክክለኛነት
- የምርምር ትምህርት ዘርፎችን አቅም እና በደንብም ሆነ በትግበራ ላይ ተፅዕኖ የማሳደር አጋጣሚያቸውን ማሳደግ
- የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻንና ተደራሽነትን ጥራት ማሻሻል
ይህ ሁኔታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ድህነትን በማስወገድና ዘላቂ እድገት በማምጣት ረገድ የሚያበረክቱት ሚና እንዲፋጠን ያስችላል።
የዩናትድ ኪንግደም ዲፓርትመንት ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት (DfID) መሥሪያ ቤት እ. ኤ. አ. ከ2006 እስከ 2013 ባሉት ዓመታት ለ DelPHE 15 ሚሊዮን ፓውንድ መዋእለ ነዋይ ፈሰስ አድርጓል። ለፕሮግራሙ የተመደበው በጀት እ. ኤ. አ. መስከረም 2009 ላይ በ3 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲያድግ ተደርጓል፤ ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት ኢራቅን ለመደገፍ ነው።
DelPHE በኢትዮጵያ
ዴልፍ (DelPHE) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አጋርነት እንዲኖር ድጋፍ የመስጠት ዓላማ አለው፤ ይህም የሆነው በኢትዮጵያ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አቅም ለመገንባትና ለማጠናከር ነው። ይህ የተደረገው የሚከተሉትን ነጥቦች ለማሳካት ነው፦
- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣቸውን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለማሳከት አስተዋጽኦ ለማበርከት
- ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተኮር የሆነ እውቀት እና ክህሎትን ለማበረታታት
- ተያያዥ በሆኑ ብሔራዊ ደንቦች እና ተግባሮች ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር
- በግለሰብም ሆነ በተቋም ደረጃ የትምህርትና የምርምር አቅምን መገንባት።
ፕሮግራሙ ይበልጥ በአፈጻጸም ላይ ያተኮረ እንዲሆን ለማድረግ ፕሮጀክቶቹ የሚከተሉትን ነጥቦችም ማሟላት ይኖርባቸዋል፦
- ከአጎራባች አገሮች የልማት ዕቅዶች ጋር የጠበቀ ትስስር መፍጠር፣
- ከማኅበረሰቡ ጋር መልካም ትስስር ለመፍጠር አጋር ተቋሞችና የአካባቢው ማኅበረሰብ ባላቸው ፍላጎት ላይ መመሥረት፣
- ዘላቂ እድገት እንዲኖር ጠንካራ አሠራር ማቋቋም፣
- ‘ከፍተኛ ትምህርት’ የሚለው ሐረግ ሰፋ ያለ ትርጉም እንዲኖረው በማድረግ ኮሌጆችንና ከሁለተኛ ደረጃ በኋላ ያሉ ሌሎች ተቋሞችን እንዲያካትት ማድረግ፣
- ምርጥ ልምዶችን በግንኙነት መረቦች፣ በትምህርታዊ ስብሰባዎችን እና በመረጃ ልውውጦች አማካኝነት ማሰራጨትና ማባዛት የሚቻልባቸውን እርምጃዎች መውሰድ፣
- በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አጋርነትና በሌሎች ዲፓርትመንት ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት (DfID) ፕሮግራሞች መካከል ላቅ ያለ መደጋገፍ እንዲኖር ማድረግ፣
- ከሌሎች የልማት ድርጅቶች ጋር ጥሩ ትብብርና መረጃ የመለዋወጥ አሠራር መከተል።
DelPHE ፕሮጀክቶች
ኢትዮጵያ ውስጥ DELPHE በድምሩ 1 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት በመመደብ ከትምህርት፣ ከጤና፣ ከግብርና፣ ከሰላም እና ከደህንነት፣ ከተፈጥሮ ሀብት፣ ከቱሪዝም እና ከኃይል ጋር ለተያያዙ 12 ለሚያክሉ አጋር ፕሮጀክቶች ድጋፍ አድርጓል።
ሁለቱን ፕሮጀክቶች በተመለከተ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ያንብቡ፦