ወርልድ ቮይስ የተባለው ፕሮግራም የተዘጋጀበት አላማ ወጣቶችን በማሰልጠን፣ ከእነርሱ ጋር አብሮ በመሥራት እና ድጋፍ በመስጠት በሙዚቃ አማካኝነት፣ የመዝፈን ችሎታቸውን ማዳበር እና ሰፊ ትምህርት ማግኘት እንዲችሉ ድጋፍ ማድረግ ነው።
በፕሮግራሙ አማካኝነት ልናደርግ ያቀድናቸው ነገሮች፦
- በመላው ዓለም በትምህርት ቤቶች ደረጃ ብሪታንያ በሙዚቃ ትምህርት ረገድ ያላትን ሙያ ማካፈል፤ በሁሉም ተሳታፊ አገሮች መካከል የችሎታ፣ የእውቀት እና የግንዛቤ ልምድ ልውውጥ እንዲኖር ማበረታታት።
- የተለያዩ ባህሎችን ዋጋማነት በማሳየት በቂ እውቀት እና ግንዛቤ ማስጨበጥ።
- በመላው ዓለም የሚገኙ ስለ ሙዚቃ ስልት ማወቅ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ።
- አገራት ዘላቂ የሥራ ግንኙነቶችን ለመመስረት እንዲጣጣሩ የሚረዳ ትስስር መፍጠር።
- አስተማሪዎች እና ወጣት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን ማስተማሪያዎች ማቅረብ።
- ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ የሆነ የሥነ ጥበብ ዓይነት መሆኑን ማሳወቅ።
ወርልድ ቮይስ ኢቲዮጵያን የሚደግፈው እና የሚመራው ስለሺ ደምሴ ነው።