ኢግናይት ካልቸር

ኢግናይት ካልቸር አዲሱ እና አስደሳቹ በምስራቅ አፍሪካ በ 14 ሀገሮች ውስጥ ለሚገኙ ባህላዊ እና የፈጠራ ዘርፎች የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ነው! ይህ የምስራቅ አፍሪካ ተኮር የገንዘብ ድጋፍ  የአለም ካሪቢያን እና ፓስፊክ የባህል ፕሮግራም አካል ነው የሚተገበረውም በሄቫ ፈንድ ተቅዋም  ከብሪቲሽ ካውንስል በኬንያ ጋር በመተባበር ነው። በገንዘብ ድጋፍ ደግሞ ከአውሮፓ አንድነት እና ከሌሎች አፍሪካ፡ከብሪቲሽ ካውንስል እና ፓስፊክ ሀገሮች ጋር በመተባበር ነው።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ ስኬታማ አመልካቾች የራሳቸውን ሥራ ለማሳደግ ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል ሌላው በታለመላቸው ማህበረሰብ ውስጥ ባህላዊ ስራን እና ድጋፍን ያካሂዳሉ። ጥረቶቻቸውን የበለጠ ዘላቂ ለማድረግም ትልቅ መንገድ ይወስዳል ፡፡ የንግድ ሥራዎቻቸውን ለማሳደግ የፈጠራ እና የባህል ሠራተኞችን ከመደገፍ ጎን ለጎን ወደተስፋፉ  ዲጂታል ገበያዎች ያስገባል እና የሥራ ቦታዎቻቸውን እና ትብብሮቻቸውን ያሻሽላሉ ። ተቋሙ ክህሎቶችን በመገንባት እና ለፈጠራ ንግዶች የተሻለ የሥራ አካባቢን ለመገንባት የሚያስችሉ መንገዶችን በማዘጋጀት ይደግፋል ፡፡

ለአንድ አመልካች እስከ 180,000 ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ይበረከታል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ ለሚከተሉት ተግባራት መዋል አለበት።

  • የተሻሻሉ እና ያደጉ  ምርቶች፣ የፈጠራ  ባህል፣ ሸቀጦች እና  አገልግሎቶች ክህሎቶች ግንባታ ።
  • የመሠረተ ልማት አውታሮችን ፣ ሃርድዌሮችን እና ሶፍትዌሮችን ማሻሻል፣
  • የተሻሻለ የፋይናንስ አቅርቦት እና ደጋፊ ፖሊሲ እና የንግድ አካባቢ ፣
  • የአካባቢያዊ ፣ የክልል እና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ተደራሽነት ማስፋት እንዲሁም
  • ለፈጠራ ፣ ለባህል ባለሙያዎች እና ለሥራዎቻቸው በመላው ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ታይነትን ማሻሻል ፡፡በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ ኢግናይት ካልቸር በቡሩንዲ ፣ በኮሞሮስ ደሴቶች ፣ በጅቡቲ ፣ በኤርትራ ፣ በኢትዮጵያ ፣ በኬንያ ፣ በማዳጋስካር ፣ በሞሪሺየስ ፣ በሩዋንዳ ፣ በሲሸልስ ፣ በሶማሊያ ፣ በሱዳን ፣ በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ ለአመልካቾች ክፍት ይሆናሉ ፡፡

የማመልከቻዎች ጥሪ ሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2013 ይከፈታል!

የመመረጫ መስፈርቶች

በቡሩንዲ ፣ በኮሞሮስ ደሴቶች ፣ በጅቡቲ ፣ በኤርትራ ፣ በኢትዮጵያ ፣ በኬንያ ፣ በማዳጋስካር ፣ በሞሪሺየስ ፣ በሩዋንዳ ፣ በሲሸልስ ፣ በሶማሊያ ፣ በሱዳን ፣ በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ የንግድ ሥራዎቻቸውን ያስመዘገቡ እና በፈጠራ ችሎታ ሥራቸው (ቢያንስ ለ 12 ወራት የሰሩ)  መሆን አለባቸው  ፡፡ አመልካቾች ቢበዛ እስከ 180,000 ዩሮ  እርዳታ ማመልከት ይችላሉ ። ብቁ የሆኑት  የሲ.ሲ.አይ እሴት ሰንሰለቶች የሚያካትቱት፣ ባህላዊ እና ተፈጥሮአዊ ቅርስ ፣ አፈፃፀም እና ክብረ በዓል ፣ የባህል መሠረተ ልማት  ፣ የእይታ ጥበባት እና የእጅ ሥራዎች ፣ መጽሐፍት እና መረጃዎች ፣ ኦዲዮ ቪዥዋል እና መስተጋብራዊ ሚዲያ ፣ ዲዛይን እና የፈጠራ አገልግሎቶች  ፣ የፈጠራ  የባህል ትምህርት እና የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ናቸው።

የማመልከቻ አፈጻጸም

ኢግናይት ካልቸር ሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2013 ለአመልካቾች ይከፈታል:: የማመልከቻ ቅጹን ያጠናቀቁ ሁሉም አመልካቾች ማመልከቻቸው እንደደረሰ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል፡፡ ስኬታማ ማመልከቻዎች በርካታ የግምገማ ደረጃዎችን ያልፋሉ የፍትህን ሂደት ጨምሮ። ከዚያም የድርጅቱን ወይም የተቋሙን አቅም የሚገመግም የገንዘብ ሞዴሊንግ ደረጃ ውስጥ ያልፋሉ እናም የታቀደው ፕሮጀክት ለተጠየቀው የእርዳታ መጠን እንዲውል ያመቻቻል። የመጨረሻው ደረጃ ኮንትራክተሩ እና ከዚያ በመጨረሻ የተመረጡትን ተወዳዳሪዎችን ማስተዋውቅ ይሆናል ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን በቅርቡ ይጠብቁ!

በራሪ ጽሁፎቻችንን ለማግኘት እዚህ ይመዝገቡ

የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ መገኛ: Twitter, Facebook, Instagram