“በፖፕ ሙዚቃ ከፍተኛ ተጽእኖ የምታሳድር ሴት ልትሆን ትችላለች” – ኢቭኒንግ ስታንዳርድ ጋዜጣ
ጎልዲሮክስ፣ እውነተኛ ስሟ ሳም ሆል በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነች ዲጄ እና የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ስትሆን እንደ ማዶና፣ ጆርጆ አርማኒ፣ ሪቻርድ ብራንድሰን እና ጄድ ጃገር የመሰሉ ታዋቂ ሰዎች የሚከታተሏት በመሆኗ ትታወቃለች (ከእነዚህ ሰዎች ጋር ብቻዋን ሆና በማጀብ ሥራዋን አቅርባለች)። በመላው ዓለም የሚተላለፈው ‘ዘ ሰሌክተር’ የተባለው ሳምንታዊ የራዲዮ ፕሮግራሟ በሚያውቁት ዘንድ እንደ ትንግርት ይወራለታል። በ37 አገሮች ውስጥ ከአራት ሚሊዮን በላይ ለሆኑ የፕሮግራሙ አፍቃሪ አድማጮች ይተላለፋል፤ በመሆኑም ዘ ሰንዴይ ታይምስ ጋዜጣ በቅርቡ ፕሮግራሙን “አለ የተባለ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የብሪታንያ የሙዚቃ ፕሮግራም” ሲል ገልጾታል።
ሳም በ2011 (እ. ኤ. አ.) ቢቢሲ ራዲዮ 1 ላይ ለበርካታ ጊዜያት ለዴቭ ፕሮግራም አቅርባ ነበር፤ በተጨማሪም በ2012 (እ. ኤ. አ.) በሙሉ ከማንቸስተር ዌርሃውስ ፕሮጀክት ሪቦክ ራዲዮን በዋና አዘጋጅነት አስተላልፋለች። በተጨማሪም ዓርብ ሌሊት የሚተላለፈውን ‘ሰሌክተር አፍተር ዳርክ’ የተባለውን ልዩ የዳንስ ፕሮግራም በሜክሲኮው ኢቤሮ ኤፍ ኤም፣ በቻይናው ሉፕ ኤፍ ኤም እና በዋርሶው ሮክሲ ኤፍ ኤም ፕሮግራሞቿን ስታቀርብ ቆይታለች።
ከራዲዮ ፕሮግራሙ በተጨማሪ ሳም በአምስት አህጉሮች ላይ በሺዎች ለሚቆጠሩ ታዳሚዎች በዓይነቱ ልዩና ለዝግጅቱ ተስማሚ በሆነ ቤት፣ በዓለም ላይ ያሉ ምርጥ ዘፈኖች እና የኤሌክትሮና ቤስ ሄቪ ሪሚክስ የሆነ ስልት በማጫወት በዓለም ዙሪያ በበርካታ መድረኮች ላይ ጨፍራለች፣ ተወዛውዛለች።
በዓለም ዙሪያ በብዙ በዓላት ላይ ዝግጅቷን ታቀርባለች፤ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ክሬምፊልድስ ላቲቲዩድ፣ ሊድስ፣ ዌክስቶክ፣ ሴክሬት ጋርደን ፓርቲ እና ግላስተንበሪ ይገኙበታል። ከዚያም ብዙም ባልተለመዱ ቦታዎች ዝግጅቷን አቅርባለች፦ በካዛክስታን የሚገኙ የሶቪየት ምሽጎች፣ የማላዊ ሐይቅ ዳርቻ፣ ሻይጋይ ውስጥ በሚገኝ መጋዘን የተካሄዱ ፓርቲዎች፣ በአልፕስ የሚገኙ ከበረዶ የተሠሩ የዲስኮ መጨፈሪያ ጎጆ ቤቶች፣ ከዚያም በሞናኮ እና በሲድኒ ወደቦች ላይ እጅግ በተቀናጡ ልዩ የመዝናኛ መርከቦች ናቸው። በተጨማሪም ለንደን ውስጥ በራሷ ስም የሚጠራ የምሽት ክለብ ያላት ከመሆኑም ሌላ በብሪት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የመድረክ አስተዋዋቂ ነበረች።
በቻናል4 የቴሌቪዥን ጣቢያ የተላለፈውን የ2012 (እ. ኤ. አ.) የለንደኑን የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት 90 ደቂቃ የፈጀ ፕሮግራም የማቅረብ ክብር አግኝታለች። በቦታው ከተገኙ 80,000 ተመልካቾች በተጨማሪ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በቤታቸው ሆነው ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሲሆን ሳም ካከናወነቻቸው ታላላቅ ሥራዎች መካከል አንዱ ነው።