Mark Wallinger’s White Horse (2013)
Our global work in arts

የፎቶ ምንጭ፦ የማርክ ዎሊንገር ነጭ ፈረስ (2013) ለንደን ውስጥ በስፕሪንግ ጋርደንስ በሚገኘው የብሪቲሽ ካውንስል ዋና መሥሪያ ቤት ለእይታ ቀርቦ የነበረ። ምስል © ፒተር ዋይት

በሥነ ጥበብ ዙሪያ የምናከናውነው ሥራ የዩናይትድ ኪንግደምን ልዩ ልዩ ባሕል፣ የፈጠራ ሃሳብና ግኝቶች ለሌሎች አገሮች የማስተዋወቅ አላማ አለው።

ልዩ ልዩ ዓይነት የሥነ ጥበብ ሥራዎችን የምናከናውን ሲሆን በብሪታንያ የሚገኙ ምርጥ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ተጠቅመን ሥነ ጥበባዊ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀትና ከሌሎች ጋር በጋራ የምንሠራባቸውን አጋጣሚዎች ለመፍጠር እንሠራለን።

የሥነ ሕንፃ፣ ንድፍና ፋሽን

የሥነ ሕንፃ፣ ንድፍና ፋሽን ቡድኑ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ንድፍ አውጪዎች እና የባሕል ተቋሞች ጋር በእነዚህ ሦስት ዘርፎች ዙሪያ በተለያዩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ግንኙነት ይፈጥራል። አሠራራቸውን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።

የፈጠራ ኢኮኖሚ

ከፈጠራ ባለሙያዎች፣ ከባሕል መሪዎችና ከደንብ አውጪዎች ጋር ያለንን ትስስር ለመደገፍና ተሳታፊ መሆን የሚቻልባቸውን አጋጣሚዎችን ለመፍጠር ብሪቲሽ ካውንስል ስለሚያከናውነው ሥራ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የፈጠራ ኢኮኖሚ የሚለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

ፊልም

ብሪቲሽ ካውንስል ፊልም የዩናይትድ ኪንግደም ፊልሞችንና ፊልም ሠሪዎችን በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አዳዲስ ታዳሚዎች ጋር በማገናኘት በመላው ዓለም አዳዲስ ፈጠራዎችን፣ ልዩ ልዩና ድንቅ የዩናይትድ ኪንግደም ፊልሞችንያስተዋውቃል፤ እንዲሁም የፈጠራ ሥራ የልምድ ልውውጥ የሚደረግባቸውን አጋጣሚዎች ያፈላልጋል።

ሥነ ጽሑፍ

ብሪቲሽ ካውንስል ሥነ ጽሑፍ ድረ ገጽ ስለምናከናውናቸው ሥራዎች፣ እየሠራናቸው ስላሉ ፕሮጀክቶችና ከዩናይትድ ኪንግደም የጽሑፍና የሕትመት ማኅበረሰቦች የተገኙ ዜናዎችን፣ በዓለም ዙሪያ የሚካሄዱ በአላት ማውጫ እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ ሊሠራባቸው የሚችሉ ወቅታዊ የብሪታንያ ጽሑፎችን በተመለከተ መረጃዎችን ይዞ ይወጣል።

ሙዚቃ

ከኤሌክትሮኒካ አንስቶ እስከ ጃዝ፣ ከባሕላዊ አንስቶ እስከ የገጠር ሕይወት ድረስ እንዲሁም ከክላሲካል አንስቶ እስከ ፖፕ ድረስ በሁሉም ዓይነት የሙዚቃ ስልቶች ዙሪያ እንሠራለን። በተጨማሪም የብሪትሽ ካውንስል ሙዚቃ ክፍልሰሌክተር የተባለ የራሱ ሳምንታዊ የራዲዮ ፕሮግራም አለው፤ ፕሮግራሙ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የተዘጋጁ አዳዲስ ምርጥ ሙዚቃዎችን ያቀርባል። ስለ ብሪቲሽ ካውንስል ሙዚቃ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማግኘት ይችላሉ።

ቲያትር እና ውዝዋዜ

የዩናይትድ ኪንግደም የኪነ ጥበብ ዘርፍ ያከናወናቸውን ምርጥ ሥራዎች እናስተዋውቃለን፤ ይህንም የምናደርገው አዳዲስ ሥራዎችን በተለያዩ ቦታዎች በማሳየት፣ ትምህርታዊ ስብሰባዎች በማዘጋጀት እና የሥነ ጥበብ ባለሙያዎችን በመላው አለም በማዟዟር፣ በማስታወቂያዎችና ውጭ አገር የሚኖሩ በዘርፉ ሥልጠና የሚወስዱ ሰዎች ለትምህርት ወደ ዩናትድ ኪንግደም እንዲመጡ ማድረግን ጨምሮ በተለያዩ እንቅስቃሴዎችና ዝግጅቶች ነው። ስለ ቲያትር እና ውዝዋዜ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ

የሚታዩ የጥበብ ሥራዎች

የብሪታንያን የሚታዩ የጥበብ ሥራዎች በተለያዩ ቦታዎች በሚካሄዱ አውደ ርእዮች እና ትምህርታዊ ስብሰባዎች ጨምሮ በተለያዩ እንቅስቃሴዎችና ዝግጅቶች አማካኝነት እናስተዋውቃለን። የብሪታንያ የሥነ ጥበብ ሥራ ውጤቶች ስለሆኑ 8,500 ገደማ ስብስቦች ጥናት ያካሂዱ እንዲሁም ያንብቡ።