ሲቪል ሶሳይቲ ሰፖርት ፕሮግራም (CSSP) የኢትዮጵያን ሲቪል ማኅበረሰብ አቅም ለመገንባት እንዲሁም መንግሥት ካወጣቸው ደንቦችና ከቀየሳቸው ስትራቴጂዎች ጋር በሚስማማ መንገድ በአገሪቱ ብሔራዊ እድገት በማምጣት፣ ድህነት በማስወገድና መልካም አስተዳደር በማስፈን ሥራ ላይ ማኅበረሰቡ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለመደገፍ የሚያስችል አቅም ለመገንባት የተቀረጸ ፕሮግራም ነው።
CSSP ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች፣ ለመድረስ አዳጋች ለሆኑ ማኅበረሰቦች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚችሉበን አቅም የመገንባት ሥራ ያከናውናል። CSSP 3 ሚሊዮን ለሚያህሉ ሰዎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ማዳረስ ለሚችሉ ከ600 ከሚበልጡ አጋር ድርጅቶች ጋር ሠርቷል። ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ችላ ለተባሉ ጉዳዮች ይኸውም ለእስር ቤቶች መሻሻል፣ ለሴቶች መብትና ለአእምሮ ጤና ትኩረት ይሰጣል። ከሚከናወኑት ሥራዎች ውስጥ ሰባ በመቶ የሚሆኑት ገቢ ማስገኛንና ሴቶች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ በፆታ እኩልነትና በሴቶች ላይ በሚፈጸም ጥቃት ላይ ትኩረት ያደርጋል።
ብዙዎች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉለት ለአምስት ዓመት የሚቆየው ፕሮግራም ከ2011-2016 (እ. ኤ. አ.) ባሉት ጊዜያት ውስጥ ከ35 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ችሏል። በአንድ ዓመት የማራዘሚያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮግራም፣ በተለይ ከማኅበረሰቡ ለተገለሉና የመኖሪያ አካባቢያቸው በጣም ለራቀ ሰዎች እንዲሁም በቂ የገንዘብ ድጋፍ ላልተደረገላቸውና ለተረሱ የእድገት አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለመድረስ አዳጋች ለሆኑ የሲቪል ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች ክልላዊ አመራር በሚሰጥባቸው ፕሮግራሞች አማካኝነት የአቅም ግንባታ ሥራ ለመሥራቱ ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት መንቀሳቀሱን ቀጥሏል።
የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአካባቢያዊ፣ በክልላዊና በብሔራዊ ደረጃ ወጪዎቹን መሸፈን አስችሏል። የገንዘብ ድጋፉ፣ አቅም ለመገንባት እንዲሁም መንግሥትን ጨምሮ በተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት መካከል መደጋገፍ መፍጠር ይቻል ዘንድ ከሲቪል ማኅበራዊ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ አዳዲስ ነገሮች እንዲፈለሰፉና የፈጠራ ሥራዎች እንዲጎለብቱ ለማበረታታት እንዲውል የታለመ ነው። CSSP በብሪቲሽ ካውንስል መሪነት INTRACን ጨምሮ በጣምራ የሚያካሄድ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ የሚመራው በአይሪሽ ኤይድ ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ደግሞ ከበርካታ ዓለም አቀፋዊ ለጋሾች ነው።
ዘ ሲቪል ሶሳይቲ ሰፖርት ፕሮግራምን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አባክዎመጥረው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይፃፉልን።