ፕሪሚየር ስኪልስ ምንድን ነው?
ፕሪሚየር ስኪልስ፣ በፕሪሚየር ሊግና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የተመሠረተ አጋርነት ሲሆን እግር ኳስን በመጠቀም ወጣቶችን ለማሳተፍና ችሎታቸውን እንዲያጎለብቱ ለማድረግ የተደረገ ዝግጅት ነው።
ፕሪሚየር ስኪልስ ፕሮጀክት የሚተገበረው እንዴት ነው?
● የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሰልጣኞች (እና በአካባቢው ያሉ አሰልጣኞችን የሚያስተምሩ) ለአዳዲስ አሰልጣኞችና ዳኞች በአካል ተገኝተው ሥልጠና በመስጠት አስፈላጊዎቹን ክህሎቶች እንዲያዳብሩና በአካባቢያቸው ያሉ የእግር ኳስ ፕሮጀክቶችን ለማሳደግ እገዛ እንዲያበረክቱ ይረዷቸዋል።
● ፕሮግራሙ የሚተገበረው በአካባቢው ካሉ አጋሮች ጋር ሲሆን የኅብረተሰቡን ፕሮጀክቶች ለማቋቋምና ለመደገፍ ይሠራል፤ ፕሮጀክቶቹ መሟላት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች እንዲሟሉ ያደርጋሉ እንዲሁም ቋሚ በሆኑ የእግር ኳስ ፕሮግራሞች አማካኝነት ከኅብረተሰቡ የተገለሉ ወይም ለአደጋ የተጋለጡ ወጣቶችን ያሳትፋሉ።
● የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪዎችና ተማሪዎች እነርሱን ታሳቢ በማድረግ በተዘጋጀው ፕሪሚየር ሊግ ድረ ገጽ እና በእግር ኳስ ላይ በተመሠረቱ በርካታ መማሪያዎች አማካኝነት በአካል በመቅረብም ሆነ በኮምፒውተር አማካኝነት ሥልጠና ማግኘት ይችላሉ።