የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥልጠና ትምህርታዊ ስብሰባ ተሳታፊዎች የብሪቲሽ ካውንስል ዳይሬክተር ከሆኑት ከፒተር ብራውን ጋር (በስተቀኝ የመጀመሪያው)

ፕሮግራሙን በተመለከተ

 ኢስት አፍሪካ ሶሻል ኢንተርፕራይዝ በቂ አገልግሎቶች የማያገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሥነ ማኅበራዊ ጥበቃ፣ ጤና፣ ትምህርት እና ሥራ እንዲያገኙ ለመደገፍ የተቀረጸ ፕሮጀክት ነው፤ ይህም ለሰው ልጆች እድገት ሁሉን አቀፍ የሆነና ዘላቂነት ያለውን እድገት ለማፈጠን ይረዳል።

በተለይ ደግሞ ፕሮጀክቱ በምሥራቅ አፍሪካ፣ ይልቁንም በኢትዮጵያና በኬንያ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገባ ለእነዚህ የእድገት አቅጣጫዎች መፍትሔ ለመስጠት በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ የማኅበራዊ ተቋም አሠራርን ለማሳደግና ለማጠናከር ጥረት ያደርጋል።

ፕሮጀክቱ፣ ብሪቲሽ ካውንስል በአሁኑ ጊዜ በአራት አሕጉሮች ውስጥ ባሉ 28 አገሮች የሚተገብረው የ ግሎባል ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ፕሮግራም ክፍል ነው። ፕሮግራሙ ማኅበራዊ ተቋሞች፣ ለማኅበራዊና አካባቢያዊ ተግዳሮቶች እንዲሁም የኅብረተሰቡንና የማኅበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ድጋፍ ያደርጋል። ከእድገትና በዘላቂነት ከመሻሻል በተጓዳኝ በዩናይትድ ኪንግደምና በሌሎች አገሮች እውቀት መጋራትንና የመተማመን መንፈስ ማዳበርን ጨምሮ አዎንታዊ የሆኑ ማኅበራዊ ለውጦችን ያበረታታል።

ሰፖርት ፎር ሶሻል ኢንተርፕራዝስ ኢን ኢስት አፍሪካ፣ በአውሮፓ ሕብረት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድና በብሪቲሽ ካውንስል ተግባራዊ የሚደረግ የሁለት ዓመት ፕሮጀክት ነው።

በዚህ ክፍል ውስጥ

Tebita Ambulance Service Paramedic Team, Ethiopia

የፕሮግራሙ ዜናዎችና ተግባራት

በምስራቅ አፍሪካ የሚካሄዱና ማህበራዊ ተቃማትን የሚመለከቱ የፕሮጀክት ስራዎችን እና ልዩ ልዩ ተግባራትን እናዘጋጃለን ፣  እንመራለን እንዲሁም እንሳተፋለን ።  እነዚህም የአቅም ግንባታ ፣  ጥናታዊ ጉዞዎች ፣ ስብሰባዎች እና ረቂቅ ሃሳቦችን  የገንዘብና የስልጠና አማራጮችን ለማህበራዊ ስራ ፈጣሪዎ