ሆርን ኦፍ አፍሪካ ሊደርሺፕ ኤንድ ለርኒንግ ፎር አክሽን (HOLLA) የተባለው ፕሮጀክት ለሙከራ በፕሮግራሙ በታቀፉ ሦስት አገሮች ውስጥ ይኸውም በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ወጣቶች በአገራዊ እና በአካባቢያዊ ልማት ተሳታፊ እንዲሆኑ ድጋፍ ይሰጣል።

ሱዳን በሚገኘው የአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት HOLLA ፕሮጀክት፣ በመላው የአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ወጣቶች፣ እነሱም ሆኑ የሚኖሩበት ማኅበረሰብ ለተጋረጡባቸው ችግሮች አዳዲስ መፍትሔዎች የሚያፈላልጉበትን መድረክ ያዘጋጃል።

HOLLA ከሲቪል ማኅበራዊ ድርጅቶች ጋር በጣምራ የሚሠራ ሲሆን ወጣቶች ቁልፍ የሆኑ የአመራር ሰጪነት ብቃቶችን እንዲያዳብሩና በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ የለውጥ አራማጆች እንዲሆኑ ያሠለጥናል።