የIELTS የመሰናዶ ኮርሶቻችን የተዘጋጁት የIELTS ፈተና ከመውሰዳቸው በፊት ፈተናውን ለመስራት የሚያስፈልገውን ችሎታና ዘዴ የማሻሻል ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ለመርዳት ነው። ይህን ኮርስ ሲወስዱ ውጤትዎ ከፍተኛ ይሆናል እንዲሁም ከትምህርትና ከሥራ ጋር በተያያዘ ያወጧቸው ግቦች ላይ መድረስ እንዲችሉ የሚያስፈልግዎትን ችሎታና እውቀት ይገበያሉ።
ይህን የብሪቲሽ ካውንስል ኮርስ መምረጥ የሚኖርብኝ ለምንድን ነው?
የIELTS ኮርሳችን የሚያስገኝልዎት ጥቅም፦
- IELTS ፈተና ለመውሰድ ብቁ እንዲሆኑ የሚያስችልዎትን የተሟላ የጥናት ፕሮግራም ያጠናቅቃሉ
- ከሚፈልጉት ቡድን ጋር መቀላቀል እንዲችሉ ልምምድ ያደርጋሉ፤ ምክርም ያገኛሉ
- ስለ አራቱም የIELTS ፈተናዎች ግልጽና ቅልብጭ ያለ አጠቃላይ ግንዛቤ ያገኛሉ
- በእያንዳንዱ የIELTS ፈተና ክፍል ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ሥራዎች ይለማመዳሉ
- ፈተና የመሥራት ችሎታና በራስ የመተማመን ስሜት እንዲያዳብሩ ጥቆማዎች፣ ጠቃሚ ሐሳቦችና ምክሮች ያገኛሉ
- የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን በሁሉም አቅጣጫ ማሳደግ የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ።
ለእርስዎየ ሚመጥነው ትክክለኛ ደረጃ
የIELTS ኮርስ የምንሰጠው በ Common European Framework of Reference for Languages (CEFR) (PDF, 50KB) መለኪያ መሠረት ዝቅተኛ ደረጃ የሆነው B1 እንግሊዝኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ነው።
የምንገመገመው እንዴት ነው?
አስተማሪዎ ያሉዎትን ጠንካራ ጎኖችና በምን መስኮች መሻሻል እንዳለብዎት እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል። ከዚህ በተጨማሪ የIELTS የሙከራ ፈተናዎችን በመውሰድ አቅምዎን መገምገም የሚችሉበት አጋጣሚ አለ።